#መቐለ
በመቐለ ዓድሓ በሚባል መንደር በሚገኝ ማረምያ ቤት ህዳር 1 እና 2 በተነሳ ግርግር የ4 ታራሚዎች ህይወት አለፈ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ግርግሩ ከተከሰተበት ሰአትና ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ ለማጣራት ጥረት አድርጓል።
የግርግሩ መነሻና ያስከተለው ጉዳት በማስመልከት የአከባቢው ነዋሪች በማነጋገርና 'ፈታዊ ለውጢ' የተባለ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ከማረምያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አገኘሁት ብሎ ያወጣውንና የማረምያ ቤቱ አስተባባሪ ለትግራይ ቴሌቪዥን የሰጡትን መረጃ በማጣመር የሚከተለው ዘገባ አቅርቧል።
ግርግሩ መቼ ጀመረ ?
የመቐለ ማረምያ ቤት አስተባባሪ ኮማንደር ኣማኑኤል ፍስሃ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንደገለፁት ግርግሩ ያጋጠመው ህዳር 1/2016 ዓ.ም 11:30 ከሰአት በኋላ ነው።
በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ የህግ ታራሚዎች፤ ታራሚዎችን ሲያረካክቡ የነበሩ 20 ፓሊስ አባላትን በመደብደብ የ3 ብሎክ በሮች በመስበር ለማምለጥ ሲሞክሩ ግጭቱ መጋጋሉን ገልጸዋል።
የአከባቢው ነዋሪዎችም ህዳር 1/2016 ዓ.ም ምሽት የምን አይነት መሳሪያ ጥይት እንደሆነ ያልለዩት የተኩስ ድምፅ በተደጋጋሚ ሰምተዋል።
የማረምያ ቤቱ አስተባባሪና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የክላሽ ጥይት ቶክስ እንደነበረ አረጋግጠው ግርግሩ ለማረጋጋት ወደ ላይ የተተኮሰ ነው ብለዋል።
የግርግሩ መነሻ ምንድን ነው ?
ግርግሩ በማረምያ ቤቱ ጠባቂዎችና ታራሚዎች መካከል የተፈጠረ ነው። #ነዋሪዎች እንደገለፁት በከባድ ወንጀል ተግባር ለረጅም አመታትና ለእድሜ ልክ የተፈረደባቸው ታራሚዎች ግርግሩ አስነስተዋል። እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሱት:-
- የተፈረደብን ፍርድ ረዝሞብናል
- የተፈረደብን ፍርድ ልክ አይደለም
- የምግብ፣ የውሃ፣ የመኝታ አገልግሎት ጥራት ጉድለትና እጥረት አለብን
- የሰብአዊ መብት ተያያዥ ጉድለት አለብን
የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ናቸው።
ግርግሩ በመጠቀም 125 ታራሚዎች ከማረምያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ለማምለጥ ሲሞክሩ በፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ማረምያ ቤቱ አረጋግጠዋል።
ምን አይነት ጉዳት ደረሰ ?
ታራሚዎች ግርግሩ በመጠቀም ከማረምያ ቤቱ የምግብ ቤት ሰራተኞች 12 ቢላዋና ሞባይል በመቀማት የጥበቃ አባላትን በሃይል በማጥቃት ሊያመልጡ ሲሞክሩ ተው መባሉና ጥይት ወደ ሰማይ መተኮሱ ተነግሯል።
ይህ ማስጠንቀቂያ ሳያቆማቸው ከሮጡት ታራሚዎች የፀጥታ ሃይል በመጨመር 112 በቁጥጥር ስር ሲውሉ፤ 4 ግን ሊያመልጡ ሲሉ በተወሰደባቸው እርምጃ መገደላቸውን ኮማንደር ኣማኑኤል ፍስሃ ገልፀዋል።
ለማምለጥ በሞከሩ ታራሚዎች ጥቃት ከደረሰባቸው 7 የፓሊስ አባላት 4 በከባድ 3 በቀላል ጉዳት በህክምና ላይ ይገኛሉ ይላል የማረምያ ቤቱ መረጃ።
ግርግሩ እንደተፈጠረ የማረምያ ቤቱ ጥበቃዎች ረዳት እንዲመጣላቸው ጥይቶች ወደ ላይ ተኩሰዋል። እንዲሁም ሃይል ተጠቅመዋል። የተጠቀሙት ሃይል ተመጣጣኝ ነው ወይስ አይደለም የሚለው በሶስተኛ ወገን አልተረጋገጠም ይላሉ የአከባቢው ነዋሪዎች።
አሁን ግርግሩ ተረጋግቷል ?
ህዳር 2/2016 ዓ.ም ግርግሩ ለማስቀጠል ቤት የማቃጠል ሙከራዎች ተደርገዋል። ይሁን እንጂ ሙከራው በተቀናጀ የፀጥታ ስራ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል። ግጭቱ በአስተማማኝነት ለማቆም መግባባት እየተደረገ ሲሆን ጎን ለጎን የግርግሩ መነሻ እየተጠና ነው ብለዋል ኮማንደር ኣማኒኤል ፍስሃ።
የተከሰተው ግርግር ለጊዜው ተረጋግተዋል ። ይሁን እንጂ እንዳያገረሽ የሚመለከታቸው አካላት ፣ታራሚዎችና የጥበቃ አባላት አስቸኳይ ውይይት በማካሄድ ሁኔታው በአስተማማኝ መልኩ ማረጋጋት እንዳለባቸው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia