TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና!

በሀድያ ዞን #ሾኔ ከተማ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው በከተማው ወርልድ ቪዥን በተባለው አካባቢ የተርጋ ቁጥሩ ኮድ 1-14316 ደ.ሕ  ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ከሻሸመኔ ወደ ወላይታ ሶዶ ይጓዝ ከነበረ ኮድ 3-05477 ደ.ሕ ከሆነ የጭነት አይሱዙ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡

የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ስራ ሂደት አስተባባሪ ዋና ሳጅን አዲሴ በርገኖ እንደገለጹት ባጃጁ መስመሩን ስቶ በፍጥነት በመጓዝ ላይ ከነበረው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪው ጋር በመላተሙ አደጋው ሊደርስ ችሏል። በአደጋውም በባጃጁ ውስጥ የነበሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።

#የሟቾቹ አስክሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ መደረጉንም አመልክተው የአይሱዙ አሽከርካሪ ለጊዜው ቢሰወርም ፖሊስ በክትትል ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና ሳጅን አዲሴ የሰው ህይወትና ንብረትን ከጥፋት ለመታደግ አሽከርካሪዎች ርቀታቸውንና ፍጥነታቸውን  በመቆጣጠር ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሾኔ

በሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የምግብ ዘይት ፣ ስኳር እና ቡና አከማችተዋል የተባሉ ሶስት ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ንብረቱ  የተገኘው  ትናንት  በከተማዋ  በሚኖሩ የግለሰቦቹ  ቤቶች  ውስጥ ተከማችቶ ነው፡፡ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በቤቶች ባደረገው  ፍተሻ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሁለት ሊትር ዘይት፣ ሰባት ኩንታል ቡና እና ሶስት ኩንታል ስኳር ማግኘታቸውን የከተማዋ አስተዳደር  ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ታረቀኝ ሶረቶ ገልጸዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
#ሾኔ

ከ500 በላይ የሾኔ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ ተሰማ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ሐዲያ ዞን ሾኔ ከተማ ፣ ላለፉት 3 ወራት የተቋረጠባቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የገለጹ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች በሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ ቪኦኤ አማርኛ ዘግቧል።

በጊዜያዊ ውል የተቀጠሩትን ጨምሮ ከ500 በላይ የሆስፒታሉ ጠቅላላ ሠራተኞች እንደተስማሙበት በጠቀሱት በዚሁ የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆን ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ ሥራ ከአቆመ 7 ቀን እንዳለፈው ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

አንድ ስማቸውን ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለፅ ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ሰራተኛ ፤ " የባጀት እጥረት እየተባለ፣ ከባጀቱም ከፍቶ አሁን ደግሞ የነሃሴ ፣ መስከረም ሙሉ ወር ደመወዝ አልተከፈለም። አምናም ደሞዝ ሳይከፈል ቀርቶ ብዙ ባለሞያዎች ስራ ለቀው ሲሄዱ ነበር። እኛ ያለነውም ደመወዝ ሳይከፈለን ስራ መስራት አንችልም ብለን ነው ለቀን የወጣነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለረሃብ እና ለአደጋ ተጋልጠናል፤ ደመወዝ ሳይከፈል እንዴት እንሰራለን ? እኛ እየተራብን ምንድነው የምንሰራው መጀመሪያ እኛ እራሱ መታከም አለብን ፣ እኛ መዳን አለብን ብለን ነው ያቆምነው፤ ከሁለት ዓመት በፊትም ያልተከፈለ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አለ የሁለት ወር ክፍያ የት እንደሄደም አይታወቅም። ማንም ባለሙያውን እንደ ባለሙያ እየቆጠረው አይደለም በሚል ነው በቁጣ ለቀን የወጣው " ሲሉ አክለዋል።

" በከተማው ሌላ ሆስፒታል የሌለ ሲሆን ያሉት የተወሰኑ ጤና ጣቢያዎች ነበሩ እነሱም ከተዘጉ ቆይተዋል። ለምን ተዘጋ ? የሚል አካልም የለም " ብለዋል።

የሆስፒታሉ የተኝቶ ታካሚዎች ክፍል አስተባባሪ ዶ/ር ፋብዩ አየለ ፤ " ከ7 ቀን በፊት የድንገተኛ ክፍል ብቻ የተወሰኑ ሰዎች ተመርጠው ይሰሩ ነበር ፤ ይከፈላችኃል ተባለ ዛሬ ነገ ሲባል 72 ሰዓት ሆነ የሚከፍል የለም ከዛ በኃላ ነው ሁሉንም ክፍሎች ለመዝጋት የወሰኑት። አብዛኛው ሰራተኛ ከሌላ ቦታ የመጣ አለ፤ የቤት ኪራይ፣ የሚበላ የሚጠጣ ያጣ አለ የሚከፍለውን ያጣው አብዛኛው ሰራተኛ ወደ ቤት ሄዷል ቤተሰቡ ጋር እዚህ ተወላጅ የሆነውም ቤት ኪራይ፣ መብላት መጠጣት አለ 3 ወር ሙሉ አልተከፈለንም። አሁንም እየጠየቅን ነው ልንከፍል አንችልም የተሰጠን ብር ጎሏል አይነት ነገር ነው የሚያወሩት " ብለዋል።

ዶ/ር ፋብዩ ፤ ከዚህ ቀደምም 2012 የሁለት ወር የትርፍ ሰዓት ክፍያ መበላቱን፣ በ2015 የጥቅምት ወር በተመሳሳይ እንዳልተከፈለ አስታውሰው አሁን በጣም ሲከፋ ሰራተኛው ስራ ማቆሙን ጠቁመዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ተድላ አካሉ፤ ሆስፒታሉ ሥራ ማቆሙን አረጋግጠዋል።

በተለይ የድንገተኛ ክፍልና ማዋለጃ ክፍል አገልግሎት ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ከ3 ቀን በፊት አንስቶ እሱም እንደተቋረጠ ገልጸዋል።

የአካባቢው ነዋሪ ሆስፒታሉ አገልግሎት እየሰጠ ባለመሆኑ ወደሌሎች አካባቢዎች ለመሄድ መገደዱን ጠቁመዋል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ተሰማ ሆስፒታሉ ሥራ ማቆሙን ባይክዱም መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

የሐዲያ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ኦልባሞ ከሬድዮ ጣቢያው ስልክ ሲደወልላቸው #ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ጠቅሰው " እዚያው ሆስፒታሉን ጠይቁ " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ ከ600 ሺህ በላይ ህዝብ ተደራሽ ያደርጋል፣ በቀንም እስከ 200 ታካሚ ያስተናግዳል የተባለለት ሆስፒታል ስራ በመቆሙ ህዝቡ እንግልት እየደረሰበት ይገኛል።

መረጃው የቪኦኤ ሬድዮ (ዮናታን ዘብዲዮስ) ነው።

@tikvahethiopia