TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SMN የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ አመራሮች ታሪኩ ለማና ጌታሁን ደጉዬን ጨምሮ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ በሐዋሳ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። በሲዳማ ዞን 935 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳኛቸው ደምሴ ተናግረዋል።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏷"የአማራ ሕዝብ የትግራይ ወንድም ሕዝብ ነው። እኛ ሕዝቡን #ትምክህተኛ አላልነውም። በየትኛውም አለም ሕዝብ እንደ ሕዝብ ትምክህተኛም ጠባብም ወይ ሌላም ሊሆን አይችልም» ... «ወደ 1968 ዓ.ም ተመልሰው ድሮም እንደዚህ ነበራችሁ ማለት አያስፈልግም ነበረ። እኛ ያልነው አጭርና ግልፅ ነው። በውስጣችሁ ምን ችግር ነው ያጋጠመው? አጥሩት ነው ያልነው፡፡ አንድ ድርጅትና ወንድም ህዝብ ነን እኮ» ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ዲያስፖራ ሲምፖዝየም (#ሕወሓት)

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፈናቃዮች ወደቄያቸው ተመልሰዋል...

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በነበረ #ኹከት የተፈናቀሉ 900 ሰዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ከረዩ ጌታሁን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። መኖሪያ ቤታቸው በመቃጠሉ በጊዜያዊ መጠለያ አርፈዋል፤ ዱቄትና ዘይት ጨምሮ የለት ርዳታ ተከፋፍሏል።

ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ከረዩ_ጌታሁን እንዳሉት በሁላ ወረዳ በገጠር 137 ቤቶች ተቃጥለው 81 በአካባቢው ነዋሪዎች እንደገና ተሰርተዋል። በከተማ 78 ቤቶች ሲዘረፉ ሁለት ቤቶች ተቃጥለዋል። 517 የቀንድ ከብቶች ተዘርፈው ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀብቴ አርዓያ የአዕምሮ ህመም ነበረበት...

መርማሪዎች የ40 አመቱ ኤርትራዊ ሐብቴ አርዓያ የአዕምሮ ሕመም እንደነበረበት የሚጠቁም ሰነድ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል። በፍራንክፈርት እናትና ልጅ ወደ ባቡር ሐዲድ ገፍቶ ጥሏል የተባለው ሐብቴ አንድ የግድያ እና 2 የግድያ ሙከራ ክሶች ይጠብቁታል።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፋና ብሮድካስቲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ ወልዱ ይመስል ከኃላፊነታቸው ተነስተው በአቶ በቀለ ሙለታ መተካታቸውን አዲስ ፎርቹን ዘግቧል። አቶ በቀለ የኢዜአ ዳይሬክተር ነበሩ።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia