TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የተመድ (UN) ከባድ ተሽከርካሪዎች ትላንት ትግራይ ክልል መግባታቸው ተገልጿል።

ትግራይ የገቡት ሰማንያ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ 579 ሜትሪክ ቶን እህል አቅርበዋል።

እርዳታውን የጫኑት የተመድ መኪኖች ያቀኑት #ኤርትራውያን ስደተኞች ወደሚገኙበት ኣዲ ሓሩሽ እና ማይ ኣይኒ መጠለያ ጣቢያዎች ነው።

ተመድ (UN) እርዳታው ለ35 ሺህ ገደማ ስደተኞች #ለአንድ ወር እንደሚበቃ መግለፁን ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia