TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
📸ኤርትራ የግዳጅ ብሄራዊ #ወታደራዊ_አግልግሎት የጀመረችበትን 25ኛ ዐመት የብር እዮቤልዩ በዓል ትላንት አክብራለች፡፡ በዓሉ #በሳዋ_ወታደራዊ ማሰልጠኛ ነው በወታደራዊ ስነ ሥርዓት የተከበረው፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በክብረ በዓሉ ተገኝተው ነበር።

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በከተማዋ ያለውን የጎዳና ላይ ልመና እና የወሲብ ንግድን በዘላቂነት ለመከላከል በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ካቢኔው በቀረበው ረቂቅ ላይ ውይይት አድርጎ አጀንዳው ለተሻለ ግብዓት ህዝቡ ውይይት እንዲያደርግበት መርቷል፡፡

የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ ውይይት እንዲያደርጉበት ወስኗል፡፡ በሌላ በኩል የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የአመራር እና የአስተዳደር ሰራተኞች አሰያየምን በተመለከተ የወጣ ረቂቅ ደንብን አጽድቋል፡፡

ከዚህ በፊት በሹመት የነበረውን የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አመራር አሰያየም አሁን ቦታው ለሁሉም ክፍት ሆኖ በውድድር እንዲሆን ካቢኔው ወስኗል፡፡ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የብዙሃን ትራንስፖርት [አንበሳ እና ሸገር ባስ] አገልግሎት በሚሻሻልበት ሁኔታ ዙሪያም ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህም ተጨማሪ አውቶቢሶችን ወደ ስራ በሚገቡበት እና የትራንስፖርት ስምሪቱ ዘመናዊ የሚያደርግ አሰራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠንቶ እንዲቀርብ ካቢኔው ወስኗል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታግተዋል!

45 #ኢትዮጵያውያን#ኤርትራውያን እና #ሶማሊያውያን ስደተኞች በሊቢያ ናስማ በተባለ ቦታ በሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ታግተው እንደሚገኙ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። ከታገቱ አንዱ «በተዘጋ ቤት ውስጥ ነው ያለንው። በጣም መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለንው» ብሏል። ስደተኞቹ እንደሚሉት የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ አውሮፓ ለመግባት ጉዞ የጀመሩት በአንድ ኤርትራዊ የሰው አሸጋጋሪ አማካኝነት ነበር።

ኤርትራዊው ለሊቢያዊ አስረክቧቸው መጥፋቱንም ይገልፃሉ፤ ከ45 ስደተኞች 7ቱ ሴቶች 38 ወንዶች ናቸው። አንዲት ኢትዮጵያዊት «ባሕር ልሻገር ብዬ ነው የመጣሁት። 6100 ዶላር ክፈይ ተብዬ ከፍያለሁ። ከዚያ በኋላ ስልኩን አጥፍቶ ለሊቢያዊ ትቶን ሔደ። ሊቢያዊው ደግሞ 3500 ዶላር ጨምሩና ከዚህ ቤት ላስወጣችሁ ብሎናል፤ አሁን አቅሙም ያለው ሰው የለም» ብላለች።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia


’እኛ ለእኛ’

#በትምህርት_ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የ’እኛ ለእኛ’ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ክረምት ጀምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግረኛ ተማሪዎችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ወራት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት ወጣቶቹንና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸውን አካላት አመስግኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ #ጽዮን_ተክሉ እንዳሉት የእኛ ለእኛ የወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣችን አቅፎ ላለፉት ሁለት ወራት በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

እስካሁን የማጠናከሪያ ትምህርቱን ሳይጨምር 25 ሺህ ደብተሮችና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች የተሰበሰቡ ሲሆን በርካታ ደብተርና እስክሪብቶ ቃል መገባቱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

በቁጥር ረገድ በደቡብ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚሀ ጎን ለጎን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሳይካትሪስቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለተፋናቃይ ተማሪዎች የስነ ልቦና የህክምና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። በቀጣይ ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባላቸው ሙያ ፕሮጀክቱን ተቀላቅለው ድጋፉን እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ፅዮን ጥሪ አቅርበዋል።

Via #ENA
ፎቶ፡ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የሱዳን ጦርና ተቃዋሚዎች የሽግግር መንግስት ለመመስረት #ከስምምነት ደረሱ። ከአልበሽር መውደቅ በኃላ በአፍሪካ ህብረት እና #በኢትዮጵያ አደራዳሪነት በሱዳን ወታደራዊ አመራሮችና ተቃዋሚዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር ዛሬ ላይ ህገ መንግስታዊ ስምምነት በመድረስ ተቋጭቷል።

የአፍሪካ ህብረት እንዳስታወቀው ከሆነ ሁለቱ አካላት ሱዳንን አዲስ ህገ መንግስታዊ የሽግግር መንግስት አቋቁመው ወደ አዲስ ምሽራፍ ለማሻገር ተስማምተዋል።

የህብረቱ አደራዳሪ #ሞሐመድ_ሀሰን ለመገናኛ ብዙሃን እንዳሉት ከሁለቱም ወገን በስምምነቱ ዝርዝር አፈፃፀሞች ላይም ወይይቱን ለመቀጠል ተስማምተዋል። የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ሰነድም የሽግግር መንግስቱና የመንግስት መዋቅሮች የስልጣን ግንኙነትና ክፍፍልንም ያማላከተ ነው ተብሏል።

ሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንቷ #ኦማር_አልበሽር በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከተወገዱ በኃላ ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ በከባድ ቀውስ ውስጥ ለመሰንበት ተገዳለች። ወታደራዊ ኃይሉና የተቃዋሚዎች ጎራ የሽግግር መንግስት መስርተው ወደፊት ለመራመድ ከስምመነት መድረሳቸውን ተከትሎ ሱዳናዊያን በዛሬው ዕለት በካርቱም አደባባዮች ወጥተው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ተዘግቧል።

ምንጭ፦ #አልጀዚራና #ቢቢሲ/#etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዩጋንዳ የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች፡፡ በዩጋንዳ የተጀመረው ክትባት በኢቦላ ምክንያት 1ሺህ 800 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡባት ኮንጎ ውስጥም እንደሚጀመር ታውቋል፡፡ ዩጋንዳ በተደጋጋሚ የኢቦላ ቫይረስ ሲከሰትባት፣ የዜጎቿን ህይወትም ስትነጠቅ ቆይታለች፡፡ ክትባቱ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል እስከ 8 መቶ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ ድጋፉ የተገኘውም በለንደን የስነ ንጽህና ትምህርት ቤት እና በድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

Via #CGTN/AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀብቴ አርዓያ የአዕምሮ ህመም ነበረበት...

መርማሪዎች የ40 አመቱ ኤርትራዊ ሐብቴ አርዓያ የአዕምሮ ሕመም እንደነበረበት የሚጠቁም ሰነድ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል። በፍራንክፈርት እናትና ልጅ ወደ ባቡር ሐዲድ ገፍቶ ጥሏል የተባለው ሐብቴ አንድ የግድያ እና 2 የግድያ ሙከራ ክሶች ይጠብቁታል።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ECX Press Release on 2011 FY Achivements - Aug 2 2019 (3).docx
74.8 KB
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለTIKVAH-ETH የላከው መግለጫ፦
#ECX

#የኢትዮጵያ_ምርት_ገበያ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ቶን ምርት በመጠቀም በ33̇̇.8 ቢልዮን ብር #ማገበያየት መቻሉን አስታወቀ፡፡ ተቋሙ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ቶን ምርት በመጠቀም በ33̇̇.8 ቢልዮን ብር ማገበያየት እንደቻለ አስታዉቋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2011 በጀት አመት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተደራሽነቱን በማሳደግና ዘመናዊ የግብይት ስርአትን በመከተል ሃገራዊ ተልእኮዉን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ተደራሽነቱን ለማስፋት በክልሎች ኤሌክትሮኒክስ የግብእት ስርአትን ተግባራዊ ማድረጉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምአገኘሁ ነገራ ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ ከግብይት ስራዉ ባሻገር በተለያዩ የቡና አብቃይ አካባቢዎች የሚመረቱ የቡና ምርቶች በሚመረቱባቸዉ አካባቢዎች እንዲጠሩ ተደርጓልም ብለዋል፡፡ በበጀት አመቱ ተቋሙ አጠቃላይ በ33.8 ቢልዮን ብር የተለያዩ ምርቶችን ሲያገበያይ መቆየቱን ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተደራሽነቱን በሃገር ዉስጥ ለማስፋት የሚያከናዉናቸዉን ተግባራት አጠናክሮ በመቀጠል ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ጋር ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡

Via #AddisTv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ አይደለችም-" የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ቀጣዩን ብሄራዊ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ እንደማትገኝ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ። ኢትዮጵያ የ2012 ብሄራዊ ምርጫን ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ እንደማትገኝና ለሰላምና መረጋጋት ቅድሚያ በመስጠት መስራት እንደሚገባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮቹ በህጉና በህገ መንግስቱ መሰረት ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ቢካሄድ ፍላጎታቸው ቢሆንም አሁን ከምርጫ ይልቅ በትኩረት መሰራት ያለበት በሰላም ጉዳይ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ለዚህ ደግሞ ገዥውና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለብሄራዊ ምርጫው መሳካት የድርሻቸውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው ብለዋል። እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ የአገሪቷ ሰላም ሳይረጋገጥ ”ምርጫ ካልተደረገ ሞቼ እገኛለሁ” ማለት አላዋቂነት ነው።

መራጩ ህዝብ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አጀንዳ ጠንቅቆ ባልተረዳበት ሁኔታ ምርጫን ማካሄድ ኢ-ዴሞክራሲያዊነት መሆኑንም ያነሱ አሉ። የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዑመር መሃመድ ምርጫ ያለሰላምና መረጋጋት የማይታሰብ ነው ይላሉ።

ይሁንና አሁን አገሪቷ ያጋጠማትን #ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈታ በማድረግ የ2012 ምርጫን ማካሄድ አለባት ብለዋል። ለምርጫው በጣት የሚቆጠሩ ወራት የቀሩ ቢሆንም መንግስትና ባለድርሻ አካላት የሰላም ችግሩን በመፍታት ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲከናወን ጥረት ማድረግ አለባቸውም ነው ያሉት።
 
Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶችን እየተቀበለች ነው። #የኦሮሚያ እና #የሶማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ #ነገ ይካሄዳል።

ፎቶ፦ Mame/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገብረክርስቶስ ቢራራ የድቻ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተመረጠ!

የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቡ ገብረክርስቶስ ቢራራን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡን አስታወቀ፡፡ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ እንደገለጹት ክለቡ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ላለፉት 15 ቀናት ዋና አሰልጣኝ ለመቅጠር ግልፅ ማስታወቂያ በማውጣት ሲያወዳድር ቆይቷል፡፡ “በሂደቱም ለውድድር ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል በወጣው መስፈርት መሰረት ብልጫ በማምጣት ገብረክርስቶስ ቢራራ ሊመረጡ ችሏል” ብለዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ሕዝቦች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ተካሄደ። በዞኑ ሳሲጋ ወረዳ የተካሄደው መድረክ የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች ወደ ሰላምና አንድነት ለማምጣት ታስቦ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ገቢዎች ሚኒስቴር በ284 ድርጅቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምርመራ ሊያካሂድ ነው። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያለፈውን በጀት ዓመት የተጨማሪ እሴት ታክስ አጠቃቀም የመከታተል እና የመቆጣጠር ሥራ በስፋት እንደሚያከናውን አስታውቋል። በመሆኑም በ284 ድርጅቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቁጥጥር እንደሚካሄድና 245 ድርጅቶች ደግሞ ለምርመራ እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሕገ-ወጥ የሰዎች ማሸጋገር ተወንጅሎ ለ21 ወራት በፓሌርሞ የታሰረው ኤርትራዊ መድኅኔ ተስፋ ማርያም በርሔ ነፃ ወጥቶ በጣልያን ጥገኝነት ማግኘቱን ጠበቃው አስታወቁ። ከሱዳን የተያዘው መድኅኔ ይኅደጎ መርዕድ የተባለ ተጠርጣሪ ነው በሚል ነበር።

Via #እሸትበቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አደጋና #ግጭቶችን የመከላካልና የመቋቋም አቅም ለማጎልበት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ሪፎርም ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተፈራ እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲዎች ግጭት፣ የንብረት መውደም የሰው ህይወት መጥፋትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እየተከሰቱ ይገኛል። የአደጋ ስጋት አስተዳደር በዕቅድና ዝግጁነት መምራት አስፈላጊ በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን የመከላከልና የመቋቋም አቅማቸውን የማጎልበት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ #አዲስ_አበባ

🏷ከገርጂ መብራት ወደ የረር በሚወስደው መንገድ እያሽከረከራችሁ የምትገኙ መንገዱ በውሃ ተሞልቷልና ጥንቃቄ አድርጉ።

√በሌሎች የአዲስ አበባ አካባቢዎችና #በኢትዮጵያ ከተሞች የምትገኙ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ስታሽከረክሩ ከፍተኛ #ጥንቃቄ አድርጉ።

ፎቶ: ኤርሚ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦክስፋም ማስጠንቀቂያ!

#ኢቦላ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከቁጥጥር ውጭ የመሆን አቅም እንዳለው ኦክስፋም አስጠንቅቋል። ኦክስፋም ይህን ያለው ባለፈው ማክሰኞ ኢቦላ ለሁለተኛ ጊዜ በምስራቃዊ ጎማ ከተማ  እንደተከሰተ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ በጊቤ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ላይ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ባህላዊ ጀልባ መስጠሟ ተሰማ። ከጣውላ የተሰራችው ጀልባ ከቀኑ 5 ስአት ከ30 አካባቢ ወደ አሰንዳቦ ገበያ የሚመጡ 18 ሰዎችን አሳፍራ በመጓዝ ላይ እያለች ተሰብራ መስጠሟን ነው የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ ከሊፋ የተናገሩት። አደጋው እንደተከሰተም የወረዳው አስተዳደር አካላት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰው የ13 ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ተችሏል ብለዋል።

ቀሪዎቹ 5 ሰዎች ግን እስካሁን አልተገኙም፤ ፍለጋውም መቀጠሉ ነው የተነገረው።የጀልባዋ ቀዛፊም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። አደጋው የደረሰባቸው የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ከሰኮሩ እና ኦሞናዳ ወረዳ ወደ አሰንዳቦ ገበያ ሲያመሩ የነበሩ ናቸው የተባለ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ ደህንነታቸው አስጊ በሆኑ ጀልባዎች ከመጓዝ በመቆጠብ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የአማን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በሰባት የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 667 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ 485ቱ ሴቶች ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ #በ2012 የተመደበው #በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ተኛ አመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ማጠቃለያ ጉባኤውን የከተማ አስተዳደሩን የ2012 በጀት በማጽደቅ አጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2012 በጀት አመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መድቧል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ያሉባትን ችግሮች ለሚቀርፉ ፤ነዋሪዎቿን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ለተባሉ እንዲሁም አንገብጋቢ ለተባሉ የልማት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ለሚችሉ ዘርፎች ልዩ ትኩረት የሰጠ በጀት ምደባ ነው ተብሏል፡፡

በጀት ከመመደብ ባለፈ አጠቃቀሙ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጀቱን አዋጪ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የአስፈፃሚ ተቋማትን አቅምና አደረጃጃት የማስተካከል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የተመደበው በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia