TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦሮሚያ🔝

በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ #የጋራ_ፎረም ለማቋቋም ተስማምተዋል፡፡

የፓርቲዎቹ የጋራ መግባባት እንደ አገር የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

ፓርቲዎቹ ሰላማዊ ትግል ለማድረግና ከዚህ ቀደም የነበረውን የፖለቲካ ባህል ለመቀየር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የአገር ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑ የፓርቲዎቹ ለዚህ ዓላማ በጋራ መስራት ለምርጫ የሚቀርብ እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡

የፓርቲዎቹ ፎረም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በውይይት ይቋቋማል ተብሏል፡፡
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) ም/ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው አለመሆኑን ገልጸወዋል፡፡

ኦሮሚያን የብጥብጥ ሜዳ ለማድረግ ሴራ እየተሴረ መሆኑን ፓርቲዎቹና ህዝቡ ሊገነዘቡት ይገባል ብለዋል አቶ ለማ፡፡

በዚህ የሽግግር ጊዜ እየሆነ ያለውን በንቃት መከታተል እንጂ ሴራን እያሴሩ ላሉት አካላት ቀዳዳ መክፈት ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው የኦሮሞ ቄሮና ህዝብ አንድነት መጠናከር እንዳለበት ገልጸው፣ በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ያሏቸውን ልዩነቶች በውይይት ፈተው ለህዝብ ጥቅም አብረው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳም የኦሮሞን ህዝብ ችግር ለመፍታት አንድነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረው፣ በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድነት ለህዝቡ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

አቶ ዳውድ አክለውም መንግስት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በሚያደርገው ጥረት ውስጥ እኛም #የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮና OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia