TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹ለሦስት ቀናት በመተከል ዞን ደንጉር ወረዳ የተከሰተው ግጭት ከትናንት ቀን አጋማሽ በኋላ ወደሠላም ተመልሷል፡፡››

‹‹የጥምረት ኮሚቴው ለኅብረተሰቡ ሰላም እንዲያረጋግጥ እና አጥፊዎች እንዲጠየቁ እየሠራ ነው፡፡›› የአማራ ክልል ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ

.
.
የአማራ ክልል ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ ዛሬ ለአብመድ በሰጡት መግለጫ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ላይ የተከሰተው ግጭት ከትናንትና ቀን አጋማሽ በኋላ #ወደሰላም መመለሱን አስታውቀዋል፡፡

ኮሎኔል አለበል እንደተናሩት ችግሩ ከተከሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ትናንት እኩለ ቀን ድረስ በደንጉር ወረዳ 30 ቀበሌዎች ጠንከር ያሉ ጥቃቶች ተፈጽመው የሰው ሕይወት አልፏል፤ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል፡፡ ለዜጎቹ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ በሁለት ግለሰቦች የትራንስፖርት ክፍያ ‹ጨምር አልጨምርም› የተጀመረ ቢሆንም ከበስተጀርባ ግጭቱ እንዲባባስ የሚፈልጉ የአከባቢው መዋቅር እና ረጅም ጊዜ እቅድ ያላቸው #የፖለቲካ_ኃይሎች አሉ፡፡ በሌሎች ማንነቶች ላይ የተፈጠረው ግጭት በጉሙዝ እና በአማራ ነዋሪዎች ላይ የተቃጣ እንዲመስል አድርጓል ብለዋል፡፡

ከቤኔሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልሎች እንዲሁም የፌዴራል ጥምር ኃይል ኅብረተሰቡ እንዳይፈናቀል እና ሰላሙ እንዲያረጋግጥ እንዲሁም አጥፊዎች እንዲጠየቁ እየሠራ እንደሆነም ኮሎኔሉ በመግላጫቸው ጠቅሰዋል፡፡

በተያያዘም ኮሎኔል አለበል ቀደም ብሎ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢዎች ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች ላይ የተሳተፉትን በሕግ ቁጥጥር የማዋል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

‹‹በቀጠናው የተፈጠረው የግጭት መነሻ አንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎች እና ከድርጊቱ ትርፍ የሚሹ ‹አክቲቭስቶች› ጥንስስ ነው፡፡ ጥቃቱን የፈፀመው የእነዚህን ኃይሎች ጥያቄ ተሸክሞ ራሱን ‹እንትና ነኝ› ሳይል በህቡዕ የሚንቀሳቀስ ሰፊ የሽብር ግብረ ኃይል መሆኑን አረጋግጠናል›› ብለዋል ኮሎኔል አለበል በ መግለጫቸው፡፡

አንድ የመከላከያ ሠራዊት ግለሰብ ‹ግጭቱን የፈጠሩት የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ናቸው› ብለው የሰጡት መረጃ ትክክል እንዳልሆነ በኋላ ላይ ከመከላከያ ጋር የጋራ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከሽብር ኃይሎች ጥቃት ሕዝቡን ሊጠብቅ ብቻ የሂደ ነው›› ሲሉም አስረድተዋ፡፡

በአማራ ክልል በየወቅቱ የተለያዬ መልክ እየያዙ የሚስተዋሉ ግጭቶችን በመፍታት በዘላቂነት ሰላም ለመፍጠር እንደመንግሥት ከቀደሙ ችግሮች ትምህርት መወሰዱንም ነው ምክትል ቢሮ ኃላፊው የተናሩት፡፡ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱም የጋራ ጥቅም ላይ እንዲመሠረት ጥረቶች እንዳሉ አስውቀዋል፡ ኅብረተሰቡም በዚህ ወቅት ለሰው ቅርብ ተደርው የሚፈጠሩ ግጭቶች የታለመላቸው መሆናቸውን በመጠርጠር ከፀጥታ አካላት ጋር አብሮ በመሥራት ብቻ የሚፈቱ እንደሆኑ እንዲረዳ ኮለኔል አለበል አሳስበዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia