TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

(አቶ አዲሱ አረጋ)

ሰሞኑን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን ለማስከበር በተደረገ እንቅስቃሴ በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና የመሰረተ ልማት መገንቢያ ቦታዎች ላይ የተገነቡ እና ከከተማዉ የመሬት አጠቃቃም ፕላን ጋር የሚቃረኑ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ይታወቃል። የተወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ ሰፊ #ቅሬታ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

ህገ ወጥነት መከላከል #ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ ባይሆንም በአፈጻጸሙ ሂደት የተፈጠሩ #ግድፈቶች እና #ስህተቶች ካሉ ለይቶ ማረም አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይል ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ ክቡር ፕረዚዳንት #ለማ_መገርሳ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ግብረሃይሉ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ወደማጣራት ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ ሪፖርት መሰረትህገወጥ ግንባታን በማፍረስ ሂደት የተፈጸሙ ስህተቶች ካሉ ህግን ተከትለዉ የሚታረሙ ይሆናል።

ህገ ወጥ ግንባታ የፈረሰባቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ወገኖቻችን ያለ #መጠለያ እንዳይቀሩ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ መሰረት ህግና ስርኣትን በተከተለ መንገድ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

የተወሰደዉ ዕርምጃ #አንድ_ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ሚዲያዎች እየቀረበ ያለዉ ዘገባ #ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

#Addisu_Arega_Kitessa
@tsegabwolde @tikvahethiopia