TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ንቁ! #ሰውነት_ከምንም_ይበልጣል!
ሀገር
ብሄር
ዜግነት
ባንዲራ...ሁሉም ነገር እኛ እንደሰው ልጅ ካልተከበርን #አይጠቅሙንም። ሰው ሲገደል፣ ሰው ሲደበደብ፣ ሰው ሲፈናቀል ልባችን #ሊደማ የሚገባው የኛ #ብሄር ተወላጅ ስለሆነ አይደለም እንደኛ ሰው #ብቻ ስለሆነ መሆን አለበት። ያን ጊዜ ለሰማይም ለምድርም መልካም ስራን ሰርተን ማለፍ እንችላለን። ከሁሉም የሚበልጠው ሰውነት ብቻ ነው። ትግሬው የአማራው፤ አማራው የትግሬው ሞት ካላስለቀሰው፣ ኦሮሞው የአማራው፤ አማራው የኦሮሞው ሞት እና ስቃይ ካልተሰማው፣ ኦሮሞው የጋሞው ጋሞውም የኦሮሞው ችግር እና መከራ ካልተሰማው፣ ሲዳማው የወላይታው፤ ወላይታው የሲዳማው ሞት እና ስቃይ ካላስለቀሰው ችግሩ #የፖለቲካ ሳይሆን የሰውነት ስሜት መጥፋት ነው። የሰውነት ስሜት መጥፋት ደግሞ በቁም #መሞት ነው።

መፍትሄው....

እኔም አንተም አንቺም በገባን ልክ ስለሰው ክቡርነት እናስተምር። በየቤታችን ስለሰውነት እንነጋገር። ታች ወርደን ስለሰውነት እናስተምር። ሁላችንም ትልቅ ሀላፊነት አለብን! መጀመሪያ ሰው ሁሉ እንዲከበር፣ እንዲወደድ፣ እንዲፈቀር እንስራ!


ፀጋአብ ወልዴ
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈጣሪ ማስተዋል ይስጠን!

ዛሬ አንዳንዶች ባሉበት ሆነው ተዋልደው ተከባብረው የሚኖሩ #ብሄሮችን ለማጋጨት ይሞክራሉ፤ ሰዎችን ለጥል ያነሳሳሉ፤ እርስ በእርስ እንዲገዳደሉ ይቀሰቅሳሉ፤ በፍቅር የሚኖረውን ህዝብ ይከፋፍላሉ፤ ወጣቱ ሰብዓዊነቱን እንዲረሳና ብሄሩን እንዲያስቀድም በሙሉ አቅማቸውን ቀን ማታ ይቀሰቅሳሉ፤ ህግን ስርዓትን አክብሮ የሚኖረውን ወጣት ተነሳ ግደል፣ አጥፋ እያሉ ይመክራሉ፤ ብሄር መስደብ፣ ማንቋሸሽ ባህል እንዲሆን ይሰራሉ፤ ወጣቱን ሳያውቀው ከፈጣሪው ጋር ያጋጫሉ፤ የተወሰነ ሰው ባጠፋው ወንጀል ሚሊዮኖች መሰደብ፣ መገለል እንዳለባቸው ምንም ሳይፈሩ ይናገራሉ።

እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎች ብዙዎቹ ከራሳቸው ጋር የተጣሉ፣ ሰውነታቸውን የረሱ፣ ፈጣሪን የካዱ፣ እውቀት የራቃቸው፣ ማስተዋል ያልፈጠረባቸው ናቸው።

ዛሬ በብሄሮች መካከል እሳት ለመለኮስ የሚጥሩ ሰዎች የለኮሱት እሳት እራሳቸውን እንደሚያነድ፤ እራሳቸውን እንደሚፈጅ ፍፁም አላስተዋሉም።

የዛሬዎቹ የጥላቻ ነጋዴዎች #ነገን አሻግረው አላዩም። ይህ ህዝብ በጣም የተዋሀደ፣ እርስ በእርሱ የተዋለደ ህዝብ ነው። ዛሬ ብሄር ለይተው በለው የሚሉት ተራ ግለሰቦች ነገ የራሳቸው ወንድም እና እህቶች ካሉበት አካባቢ ወጥተው እንደሚማሩ ረስተውታል፤ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ ሄደው የሚማሩትን #ምስኪን ልጆችን ረስተዋቸዋል።

የብሄር ተቆርቋሪዎች መስለው የራሳቸውን ወንድም እና እህቶች የሚያጋድሉት ሰይጣኖች ናቸው። ወንድም እና እህቶቻቸው በሄዱበት ቦታ ሁሉ በቋንቋቸውና በባህላቸው እንዲሸማቀቁ ሊያደርጓቸው ያሰቡ እነሱ እውነትም የዚህች ሀገር ጠላቶች ናቸው።

እናተ የጥላቻ ነጋዴዎች...

◾️ነገ ምስኪን እህት ወንድሞቻችሁ የት ተመድበው እንደሚማሩ አታውቁምና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን አስተምሩ።

◾️ነገ ምንም የማያውቀው ሰራተኛ የዕለት ጉርሱን ፍለገ የትኛው ከተማ እንደሚሄድ አታውቁም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን አስተምሩ።

ሁሉም ሰላምን የሚወድ፤ ሀገሩን የሚወድ ሰው በብሄር ማካከል ጥላቻ እንዲኖር የሚሰሩትን ያግልላቸው። የማዕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጥላቻ ገፆች እና ግለሰቦችን #Block አድርጓቸው።

ለወጣቱ ፍቅርን እናውርሰው። ፍቅር እንደሚያሸንፍ ደጋግመን እንገረው። #ሰውነት ከሀገር፣ ከብሄር፣ ከዘር እንደሚበልጥ እንገረው።

ፈጣሪ ማስተዋልን ይስጠን!
ፀጋአብ ወልዴ-ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኧረ እንንቃ‼️

በዚህች #ድሃ በሆነች ሀገር ላይ እየኖርን #የጎደለንን ለሟሟላት ከመጣር ይልቅ ያለንን #በማጉደል ላይ ተጠምደናል። ምቀኝነት፣ ተንኮል፣ ክፋት፣ መጠላለፍ፣ ማጥላላት፣ መከፋፈል፣ መባላት፣ ለጦርነት መንደርደር፣ ሰው አለማክበር የማንነታችን መገለጫ ሊሆን አይገባም። ያለችን አንድ ሀገር ናት ሰርተን እንቀይራት!! እንዋደድ፤ እንከባበር፤ መጥፎ ስራዎችን እየፀየፍ፤ አንድ የሚያደርገን #ሰውነት ነው።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየቤታችን እንወያይ!

የዚህች ሀገር ችግር ተመዞ አያልቅም። ከእናተው ጋር ሆኜ ብዙ እየሰማው እና እያየሁ እንደመዋሌ ላለፉት 3 ዓመታትም በየቀኑ እዚሁ ከናተው ጋር መረጃዎችን ስቀባበል ስውል እንደተረዳሁት ትልቁ ችግራችን ስለሰው ክቡርነት በሀገራችን ብዙ ስራ አልተሰራም። ዛሬ ዝርፊያው፣ ማሳደዱ፣ መግደሉ፤ ማፈናቀሉ...የምንሰማቸው ዘግናኝ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ሁሉ ሰው ምን ምንድነው የሚለውን በጥልቀት ካለመረዳት የመጣ ይመስለኛል። አንድን ሰው በሰውነቱ ካከበርነው ብሄሩን፣ ዘሩን፣ ቋንቋን፣ ማንነቱን...ሁሉንም እናከብርለታለን።

#በጥቅም ተደልለንም፤ በግለሰቦች ቅስቀሳም ወገናችንን የምንጎዳውም፤ ሰው የምናፈናቅለውም፤ ሰው የምንጠላውም #ሰውነትን በአግባቡ ስላልተረዳን ነው። መጀመሪያ ሰው እንሁን! ሰው ስንሆን የሌላው ሞት የኛ፤ የሌላው ስቃይ የኛ፤ የሌላው በደል የኛ ...ይሆናል! ሰውን ሁሉ እንደራሳችን ማየት ስንጀምር #ሰላም እንሆናለን።

ስለአንድነት፣ ስለነፃነት ፣ስለዴሞክራሲ ለማውራት በቅድሚያ እውነት እኛ #ሰውነት_ገብቶናል?? ብለን ልንጠይቅ ይገባል። ሁላችንም በሰውነት ጥላ ስር ከተከለልን የስቃይ እና የመከራ ጊዜው ያጥራል።

•እንደመነሻ ሀሳቤን ገልጫለሁ እናተስ ምን ትላላችሁ...?

ሀሳባችሁ ገፁ ላይ እንዲለጠፍ...👇

•በአማርኛ ፅሁፍ አጠር አድርጋችሁ ሀሳባችሁን ማቅረብ ወይም

•በድምፅ ከ4 ደቂቃ ያልበለጠ በጨዋ ቋንቋ የግል ምልከታችሁን ብቻ በ @tsegabwolde መላክ ይቻላል!

🔹ሚቀድመውን እናስቀድም! ከምንም ነገር በፊት ሰውነት ይቀድማል!! እውነት እኛ የሌላውን ስቃይ እንደራሳችን እናያለን?? ወይስ እኛን ሊያስለቅሰን የኛ ዘመድ ወይም የኛ ብሄር ሰው መሆን አለበት??
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ...

"እኛ ኢትዮጵያዊያን በሚያሳዝን ሁኔታ ለሰው ያለን ክብር እየተሸረሸረ ነው። አሁን አሁን ሁሉም ነገር ከብሔር ጋር ተያያዘና #ሰውነት ቦታን አጣ። በሚገርም ሁኔታ አሰፋ መዝገቡ የሚነግረን የትራፊክ አደጋ መረጃ ብቻ ሆኗል ብሔር ሳይለይ ይሄን ያህል #ሰው ሞተ እና ቆሰለን የምንሰማበት። ሌላው ነገር ሁሉ ከብሔር የተገናኘ ሆኗል።
መፍትሔ የሚመስለኝ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወደ ቀልቡ ይመለስ። ድሮ ይወድ የነበረውን ወንድሙን ለምን ጠላሁ ብሎ ይጠይቅ?? ያኔ ወደየቀልቡ ይመለሳል። አማኑኤል ከሐዋሳ ዪኒቨርስቲ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ነው #የግጭት_ትርፉ! ይህን እንኳን አይተን እንማር፤ እኛ ላይ ሲደርስ ደም እንባ ከምናነባ ሁላችንም ለኢትዮጵያ ሀገራችን #ሰላም ዘብ እንቁም!
.
.
#ሰውነት ከብሄር፣ ከዘር፣ ከቀለም ይቅደም!
.
.
ፎቶ ቁጥር 1. #ሶሪያ
ፎቶ ቁጥር 2. #ኢትዮጵያ/የሶርያ ስደተኛ ህፃን-አዲስ አበባ/

#እኔ ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ የምትሉ የቤተሰባችን አባላት ይህቺን🕊የሰላም ምልክት የሆነችን እርግብ ተጫኗት!

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰው ሁኑ! ቅድሚያ #ሰውነት ይቀድማል! ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል! ከዘርም ሰውነት ይቅደም! አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል ሊገፋ አይገባም፣ ሊሰደድ አይገባም፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁት በማለት አዟል!" ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጂ ኡመር እንድሪስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ፣ ሀዋሣ፣ አምቦ፣ መቀለ፣ ሀረማያ፣ ወልቂጤ፣ ድሬዳዋ፣ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንመጣለን ተዘጋጁ!!

#ሰውነት ያስተሳሰረን የኢትዮጵያ ልጆች ነን!! በፍፁም ሀገራችን #እንድትፈርስ አንፈቅድም!!

#STOP_HATE_SPEECH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ፣ ሀዋሣ፣ አምቦ፣ መቀለ፣ ሀረማያ፣ ወልቂጤ፣ ድሬዳዋ፣ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንመጣለን ተዘጋጁ!!

#ሰውነት ያስተሳሰረን የኢትዮጵያ ልጆች ነን!! በፍፁም ሀገራችን #እንድትፈርስ አንፈቅድም!!

#STOP_HATE_SPEECH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ተስፋዎች👆

#ሰውነት ያስተሳሰራቸው፤ #ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች #የተሰባሰቡ፤ ሀገራችንን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣት በየዩኒቨርሲቲው እየተጓዙ የሚገኙት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #ኑ ኢትዮጵያን #ከጥላቻ አላቀን #ታላቅ እናድርጋት የሚል #ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ: የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት #ለእንግዶቹ ያደረገው #የእራት እና #የምሳ ግብዣ #WKU

Photo: @Dura_pic

ደማችን #አንድ ነው!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia