TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወጣቷን #በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ #ሞት ተፈረደበት‼️
.
.
አንዲት ወጣት ላይ አሰቃቂ ግድያ ፈፅሟል ያለውን ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ፍርድ ቤቱ ቅጣቱ የወሰነው በሐረማያ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ በሆነው #ጫላ አህመድ ሙመድ የተባለው ግለሰብ ላይ ነው።

የፍርድ ቤቱ ዳኛ አቶ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በግለሰቡ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በቤት ሠራተኝነት ሕይወቷን ትመራ የነበረች ወጣትን በግፍ መግደሉ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ነው።

ሟች በአወዳይ ከተማ ከባለቤቷ ጋር ተጋጭታ በሐረር ከተማ በቤት ሠራተኛነት ስትሰራም ነበር።

“ግለሰቡ ወጣቷን ለትዳር እንደሚፈልጋት በመግለፅ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት በመውሰድ ከአቅም በላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከፈፀመባት በኋላ ጆሮዋ አካባቢ እንደመታትና አንቆ እንደገደላት ታውቋል” ብለዋል።

“ወጣቷ ላይ ግድያ ከፈፀመ በኋላ ቤቱ ቆልፎባት ጠፍቷል” ያሉት ዳኛው፣የቤቱ ባለቤቶች ግለሰቡ በመጥፋቱ መጋቢት 24 ቀን 2010 ቤቱን ለሌላ ግለሰብ ለማከራየት ፈልገው በሩን ሲከፍቱ አስከሬኑን እንዳገኙት አስረድተዋል።

“የተዘጋውን በር ሲከፍቱ ያልጠበቁት መጥፎ ጠረን ያጋጠማቸው አከራዮች ዘልቀው ሲገቡ በቤቱ ወለል ላይ የፈረሰ የወጣቷን አስከሬን አግኝተነዋል” ሲሉም አብራርተዋል።

የሐረማያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወንጀሉ ወደ ተፈፀመበት ቤት በማምራት አስከሬኑን ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ ከተደረገለት በኋላ መቀበሩን ተናግረዋል።

“ግለሰቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የወሲብ ጥቃት ይፈጽሟል በሚል ጥርጣሬ በመኖሪያ ቤቱ በተደረገ ፍተሻ የሟች አልባሳት፣ የተለያዩ ሴቶች ፎቶግራፎች፣ ማሰቃያ ሰንሰለትና ሌሎች ወንጀል መፈፀሚያ ቁሶች ተገኝተዋል” ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን የሕክምናና የሰው ማስረጃዎች በመመልከት ቅጣቱን መበየኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia