#አረንጓዴአሻራ
የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማዋ ሁሉም ክፍሎች በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ለረዥም ጊዜያት በከተማዋ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ በቆየው በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ወላይታ_ሶዶ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአረንጓዴ አሻራ ቀን በወላይታ ሶዶ ችግኝ ተክለዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ፥ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞኑ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በሶዶ ከተማ ስምንት ችግኝ መትከያ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንደኛው በመገኘት ችግኝ ተክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶዶ ስታዲየም በመገኘት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለሚመለከተው_አካል
ጥቂት በማይባሉ አካባቢዎች ነዋሪዎች ችግኝ ለመትከል እና አሻራቸውን ለማኖር ከፍተኛ ተነሳሽነትን ቢያሳዩም "ችግኝ የለም፣ ችግኝ አልቋል" የሚሉ ምላሾች እየተሰጡ ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ ይህን መርሃ ግብር የሚያስተባብረው አካል ጉዩን ይመልከተው።

#አረንጓዴ_አሻራ የሀበሻ ስቲል ፒሌሲ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል። "Guyya Ashaaraa Magarisumma"
#አሰላ
"ጥዋት የተወሰነ ችግኞች ተተክሏል ግን አሁንም ብዙ ሰው አለ የችግኝ እጥረት አለ፤ ይመጣል ብለው ነበር ግን እስካሁን አልመጣም ሰው ተስፋ ቆርጦ እየተመለሰ ነው። የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ ይስጥ!

#NewsAlert
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን በርካታ ችግኝ በመትከል የተያዘውን ክብረ ወሰን የሚበልጥ ችግኝ ተከለች። በአንድ ቀን 66 ሚሊዮን የዛፍ ችግኝ በመትከል በህንድ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን የሚበልጥ ችግኝ በዛሬው ዕለት በስድስት ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያ ተከለች።
ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር መረጃ ቋት እየወጣ ባለው መረጃ መሰረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 67 ሚሊዮን ችግኝ ከማለዳ ጀምሮ ተተክሏል። ይህ ቁጥር እንደሚያሳየው ከዚህ ቀደም በክብረ ወሰንነት ተመዝግቦ የሚገኘውን 66 ሚሊዮን የሚልቅ ነው።
ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም 'የዜጎች የአረንጓዴ አሻራ ቀን' በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን በመተከል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ክብረወሰን ለማስመዝገብ አቅዳ ስትሰራ ነበር። በመሆኑም በዛሬው ዕለት በገጠርም ሆነ በከተማ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች በነቂስ ወጥተው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ተራራማ መልክዓ ምድር የበዛባት ኢትዮጵያ የቀድሞ ደን ሽፋኗ የተመናመነና አፈሯ እየታጠበ በመሆኑ የደን ሽፋኗን ለመመለስ፣ የዝናብ ስርጭቱን ለማስተካከል፣ የሙቀት ሁኔታውን ለማሻሻል የደን ሽፋን ሁኔታ መለወጥ የግድ በመሆኑ በዘንድሮ የክረምት ወቅት አራት ቢሊዮን ችግኝ ይተከላል። ኢትዮጵያ ለዓለም አረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ካዘጋጁ አገሮች አንዷና የመሪነት ሚናዋን እየተጫወተች ያለች አገር ናት።
ለክረምት ችግኝ ተከላ ዘመቻው ከ4 ነጥብ 7 ቢሊየን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል። በኦሮሚያ 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን፣ በአማራ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን፣ በደቡብ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
Via #ENA

#ሶማሌ
በሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሀመድ ዑመር በተገኙበት የችግኝ ተከላ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
Via #AMMA

#ቴፒ የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
#ሻሸመኔ የወላቡ የወጣቶች በጎ አድራጎት ማህበር አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። WALDAA TOLA OOLTUMMAA DARGAGGOOTA WALAABUU
"የኢትዮጲያ ድሕረምረቃ ሥነመለኮት ት/ቤት ያደረግነው የችግኝ ተከላ፣አረንጓዴ ልማትን ጽዱነትንና ሰላምን እንከተል በሚል ዋና ጥቅስ ከ500 ችግኞች በላይ ተክለናል።"
#GreenLegacy Ethiopian Graduate School of Theology planted 500 plants this morning!

ከ100 ሚሊዮን በላይ!
በዛሬው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው 200 ሚሊዮን ችግኝ ውስጥ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ የተተከለው ከ108 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ ቢያንስ 200 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሟን ለማስፈር ሕዝባዊ ንቅናቄ ፈጥራ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡
ከወዲሁ አገሪቱ ከዚህ ቀደም በዘርፉ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተመዝግቦ የቆየውን ሬኮርድ በሰፊ ልዩነት እንዳሻሻለችው ተገልጿል፡፡
Via #etv