TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀረማያ_ዩኒቨርሲቲ

"የተመደበልንን ችግኝ ተክለን ጨርሰን ሌሎች ጋር የተረፈ ካለ ፍለጋ እየሄድን ነው! ከችግኞች የተላጡ ላስቲኮችንም ሰብስበን አስወግደናል።" ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
#አረንጓዴ_አሻራ_በድሬዳዋ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከነዋሪዎች እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ችግኝ እየተከሉ ነው። ከተማ አስተዳደሩ በዛሬው ዕለት 200 ሺህ ችግኞችን እንደሚተክል አስታውቋል።
#የኢትዮጵያ_ካቶሊካዊት_ቤተክርስቲያን የሐምሌ 22 ቀን 2011 የችግኝ ተከላ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተከርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር
#አረንጓዴ_አሻራ

"ከኮልፌ መ/ኢየሱስ ቤ/ክ ነው በጠዋት ወተን በሆላንድ ኢምባሲ ጀርባ በተዘጋጀው ቦታ ከተለያየ ቦታ ከመጡ ሰዎች ጋር ችግኝ ተክለን የትውልድ አሻራችንን አሳርፈናል። ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለናም በቦታው ተገኝቶ ነበር!"
#ጎንደር_አረንጓዴ_አሻራ

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ልዑካን ቡድን አባላት የአረንጓዴ አሻራ ቀንን ምክንያት በማድረግ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ ችግኝ ተከሉ።
#አረንጓዴ_አሻራ በሰሜን ሸዋ ዞን በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2011ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ጀምሮ በተዘጋጁ 65 የተከላ ጣቢያዎች ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የአማራ ክልል የሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር፣ ሌሎች የፌደራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የየካ ቅርንጫፍ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን ኣሳርፋዋል። #አረንጓዴ_አሻራ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
141 ሚሊዮን ደርሷል!

በአገር አቀፍ ደረጃ የተተከለው ችግኝ እስካሁን 141 ሚሊዮን ደረሷል።
አ/አ የሚገኙ የጅማ አባጅፋር ልጆች #አረንጓዴ_አሻራ #ECA
#ICT-Park እምንገኝ የ IT አና የሶፍትዌር መተግበሪያ ሰራተኞች በዛሬው እለት የሀገራችንን ታሪክ በመጋራት እኛም አሻራችንን አኑረናል #አረንጓዴሻራ #GreenLegacy #CIMAC-ET #ICT-Park-Administration
"በአንዳንድ አካባቢዎች ሰው ችግኝ ስያልቅበት በብሩ ገዝቶ እየተከለ ነው 👏" #አዲስአበባ #ጅማ #አዳማ
በደቡብ ብብህክመ የአርብቶ አደር ኮሚሽን ሰራተኛኞች እና ሀላፊዎች በሀዋሳ አየር ማርፈያ ለችግኝ ተከላ በተዘጋጀው ቦታ በማለዳ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራ አኑረዋል።
#አቡነ_ጴጥሮስ

ኢ/ር ታከለ ኡማ በአቡነ ጴጥሮስ የ83ኛ ዓመት የሰማዕትነት የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በአቡነ ጴጥሮስ የሰማዕትነት የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡ የአባታችን አቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት ዛሬ ላለነው ትውልድ ብዙ መልዕክት አለው ያሉት ኢ/ር ታከለ ለሀገር የሚከፈል መስዋዕትነት የራስን ህይወት አሳልፎ እስከመስጠት መሆኑን ትምህርት የሰጠን ነው ብለዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ለብፁዕነታቸው በሃውልታቸው ስር የመታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ካኖሩ በኃላ ችግኝ ተክለዋል፡፡

(ከንቲባ ጽ/ቤት)
#ጎንደር

"የኃይሌ ሪዞርት-ጎንደር ማኔጀመንት እና ሰራተኞች በጎንደር ገነት ተራራ ላይ የ #አረንጓዴአሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደናል!"
#አዳማ የአዳማ 09 ቀበሌ ነዋሪዎች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
#አረንጓዴ_አሻራ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የገቢዎች ሚኒስቴርና ኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።