TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
CSA ግቢ ውስጥ ተኩስ ነበር!

የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ ተኩስ ነበር ተብሏል። ጋዜጠኛ አሮን ማሾ ትዊተሩ ላይ እንዳሰፈረው ተኩሱ የነበረው ለህዝብና ቤት ቆጠራ የሚያገለግሉ ታብሌት ኮምፒውተሮችን ይጠብቁ በነበሩ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መሀከል ነበር ብሏል። ስለ ጉዳዩ ያውቁ እንደሆን የተጠየቁ ሁለት የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች "ልክ ነው፣ ግን መናገር አንችልም። ፖሊሶች መጥተው ምርመራ አርገው ሄደዋል" ብለው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/#AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ ለተራራ ጎሪላዎች ሕይወት አስጊ ሆኗል!

የኮሮና ቫይረስ አስጊነት ተከትሎ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ቨሩንጋ ብሔራዊ ፓርኳን እስከ ወርኃ ጁን ለቱሪስት ዘግታለች።

ሩዋንዳም በተመሳሳይ ሶስት ብሄራዊ ፓርኮችን ለቱሪስቶች እንዲሁም ለጥናት ስራዎች ዘግታለች። ኡጋንዳ ግን እንደ ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተመሳሳይ እርምጃ አልወሰደችም።

በኡጋንዳ ፣ ሩዋንዳና ኮንጎ ጥበቃ በሚደረግላቸው ሥፍራዎች የሚገኙት የተራራ ጎሪላዎቹ ቁጥር ከ1,000 ያልበለጠ ነው።

#AP #SBS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“...ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” - ሄኮ ማስ

ጀርመን ናሚቢያን ቅኝ በገዛችበት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሟን አመነች፡፡

ጀርመን እአአ ከ1904-08 ባሉት ዓመታት በናሚቢያ ዜጎች ላይ የፈጸመችውን ግድያ በጅምላ ጭፍጨፋነት ለመቀበል ስታቅማማ ቆይታለች፡፡

ነገር ግን 5 ዓመታትን በወሰደ ንግግር ጭፍጨፋውን ስለመፈጸሟ አምና ተቀብላለች።

ይህን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት መሰረት ለተለያዩ ልማቶች የሚውል የ1.3 ቢሊዬን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ተስማምታለች።

ጄኔራል ሎታር ቮን ትሮታ በሄሬሮ ጎሳዎች የተነሳውን የጸረ ቅኝ ግዛት ተቃውሞ ለማርገብ በማሰብ ሙሉ የጎሳው አባላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዝ 65 ሺ ገደማ የጎሳው አባላት መጨፍጨፋቸውን እና በትንሹ 1 ሺ የናማ ጎሳ አባላት መገደላቸውን የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄኮ ማስ “ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” ብለዋል ባወጡት መግለጫ፡፡

ማስ በመግለጫቸው “ዓላማችን ተጎጂዎቹ የሚታወሱበትን እውነተኛ የእርቅ መንገድ መፈለግ ነው” ብለዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ በዛሬዋ ናሚቢያ ቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶችን “በይፋ ጅምላ ጭፍጨፋ ብለን እንጠራቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን #AP

@tikvahethiopia
#Sudan

በጎረቤት ሀገር ሱዳን ፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 31 ሰዎች ሲገደሉ 39 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው በርካቶችም ሰላም ፍለጋ መሸሻቸው ተሰምቷል።

ግጭቱ የጎሳ ግጭት እንደሆነ ተገልጿል።

በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳ የመሬት ውዝግብ ምክንያት በሮሰሪስ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 31 ሰዎች ሲገደሉ፣ 39 ሰዎች ቆስለዋል በርካታ ሱቆች ተቃጥለዋል።

በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሳቢያ አንድ ሰው (በግብርና ስራ የሚተዳደር) ከተገደለ በኃላ ግጭቱ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ ነው የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ተብሏል።

ምንም እንኳን ሱዳን በአካባቢው ተጨማሪ ወታደሮችን ብታሰማራም ግጭቱ እስከ ትላንት ከሰአት በኋላ ቀጥሎ መዋሉ ታውቋል።

መንግስት ደም አፋሳሹን ግጭት ለማስቆም ችግር ባለባቸው ቦታዎች ላይ የምሽት ሰዓት እላፊ አውጇል።

#CGTNAFRICA #AlJazeera #AP

@tikvahethiopia