TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጎጆብሪጅ #ጤናባለሙያዎች

➡️ " ውላችን ይቋረጥ ፣ #ገንዘባችንም_ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች

➡️ " ከጤና ሚኒስቴር፣ ከዳሽን ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ

ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ #የጤና_ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ ብሪጂ ሀውሲንግ ፦
➡️እጣውን በወቅቱ እያወጣ ባለመሆኑ፣
➡️እጣ የወጣላቸውም ግንባታ ባለመጀመሩ፣ 4,000 ቆጣቢዎች ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢጠይቁም እንዳልተመለሰላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ጠይቀዋል።

የቆጣቢዎቹ ኮሚቴ በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " በየሶስት ወሩ ለማውጣት እጣው ሳይሰጥ 2 ዙር አልፏል። ለምን ? ተብለው ሲጠየቁ ' #የመሬት_አስተዳደር_ችግር_ስላለብን_ነው ' እያሉ እስካሁን ቆዩ " ብሏል።

" ውላችን ይቋረጥ ፤ ገንዘባችንም ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 የቤት ቆጣቢዎች አሉ " ሲል የገለጸው ኮሚቴው በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተሰጠው አስረድቷል።

ለተነሳው የቤቶች እጣ መዘግየት ቅሬታ በ ' ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ' በኩል ምላሽ እንዲሰጡን የተጠየቁት አቶ አልማው ጋሪ ፤ " የገጠመን ችግር በአደረጃጀት ላይ #መዘግየቶች ስለነበሩ ነው " ብለዋል።

" የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የሚባለው ነው " ያሉት አቶ አልማው፣ " ሌላ ሳይት ላይ በተፈጠረ ክስ ትንሽ ሥራው ስለቆመ እስኪ ውጤቱን እንየው የሚል ሀሳብ ተነስቶ ስለነበረ የመዘግየት ጉዳይ አጋጥሟል " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የቤት ቆጣቢዎቹ ከጠየቁ ለምን ገንዘባቸውን አልመለሳችሁም ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ውሉ የሚያስቀምጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ይህን ደግሞ ለብቻችን ሳይሆን ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " ብለዋል።

" የመጀመሪያው እጣ ማውጣት ተደርሶ ወደ 300 ሰዎች እጣ የደረሳቸው አሉ። እነርሱን ለማደራጀት በሂደት ላይ ነው ያለነው " ያሉት አቶ አልማው " አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ አላቸው እየመጡ ይጠይቃሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጉዳይም ባለፈው ሳምንት ጤና ሚኒስቴር የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ አቀረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ምናልባት በዚህ ሳምንት አንድ ደረጃ ላይ ይደርሳል " ብለዋል።

#TikvahEthinpiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM