TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#StopHateSpeech

ደካማ አመራሮች...

"የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ያደረጉት ደካማ አመራሮች ነበሩ። አንዱ ሌላውን #እንዲገድል ጎራዴ በመኪና ተጭኖ እንዲጓዝ ሲያደርጉ የነበሩት አመራሮች ናቸው። ... በሙሉ ሲሰበክ የነበረው #ጥላቻ፤ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ነው። አማራው ኦሮሞው ላይ፤ አማራው ትግሬው ላይ እንዲነሳ፤ ወላይታ ሲዳማ ላይ፤ ሲዳማ ወላይታ ላይ እንዲነሳ ሲሰራ ከርሟል ይሄ ድምር ውጤት ደግሞ #የመንግስት ነው።" አዲሱ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ_ታደሰ በTIKVAH-ETH የStopHateSpeech 3ኛው መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰመራ

"...አብዛኛዎቹ #የመንግስት ቤቶች በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው"
.
.
#በሰመራ_ሎግያ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 200 የመንግሰት ቤቶች መካከል በህጋዊ ውል የተያዙት ከ35 እንደማይበልጡ የአስተዳደሩ ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፅህፈት ቤት በበኩሉ ከ2 እስከ 10 ዓመት ድረስ የቤት ኪራይ ባልከፈሉና የመንግስት ቤት በህገ ወጥ መንገድ በያዙ ግለሰቦች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንጂነር ራሁባ ሙሀመድ እንደገለጹት በመንግስት ቤት ከሚኖሩ 200 አባውሯዎች መካከል ህጋዊ ውል ያላቸው 35ቱ ብቻ ናቸው። “ቀሪዎቹ 165 አባወሯዎች ከፅህፈት ቤቱ እውቅና ውጪ ቁልፍ ገዝተውና በህገወጥ መንገድ ቤቶቹን በእጃቸው ያስገቡ ናቸው” ብለዋል። ህጋዊ ውል ያላቸውም ቢሆኑ በመንግስት የክትትልና ቁጥጥር ድክመት ምክንያት ከ2 እስከ 10 ዓመት ድረስ ያልከፈሉት ከ300 ሺህ ብር በላይ #ውዝፍ የቤት ኪራይ ዕዳ ያለባቸው ከ100 በላይ ሰዎች እንዳሉ በቅርቡ በተደረገው የማጣራት ስራ መረጋገጡን ኢንጂነር ራሁባ ገልፀዋል። የመንግስት ቤቶችን በህገወጥ መንገድ  ባስተላለፉ፣ ቤቶቹን በያዙና ለረጅም ዓመታት የቤት ኪራይ ባልከፈሉ ግለሰቦች ላይ እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ ክስ እንደሚመሰረትም ኃላፊዋ አስታውቀዋል።

Via #ena
ፎቶ፦ ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"... ነጋዴዎች እና አንዳንድ የመንግስት የንግድ ተቋማት ጭምር ምርትን በመደበቅ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን ፈጥረዋል" - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

By : Ahadu Radio 94.3

የአ/አ ከተማ ንግድ ቢሮ ከ1 መቶ በላይ የመንግስት የንግድ ተቋማት የዋጋ ንረት በመፍጠራቸው ምክንያት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገለፀ፡፡

ቢሮው በከተማዋ የተስተዋለው የዘይት ምርት እጥረት በነጋዴዎች በጅምላ ሻጮች ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ የመንግስት የንግድ ተቋማትም ጭምር የተፈጠረ ነው ብሏል።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል መኤሳ፥በከተማዋ የተስተዋለው የዘይትና ሌሎች የፍጆታ ምርቶች እጥረት ከፍተኛ የዋጋ ንረትን በሚፈጥሩ የንግድ አካላት የተፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል።

ጋላፊው ፥ ነጋዴዎቹ እና አንዳንድ #የመንግስት የንግድ ተቋማትም ጭምር ምርትን በመደበቅ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን ፈጥረዋል ያሉ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር ከ1 መቶ በላይ የመንግስት የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ኢሬቻ #መስቀል #የመንግስት_ምስረታ !

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመስቀል፣ ከኢሬቻ በዓላት እና ከመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት በፊትና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ፤ ችግር ቢከሰት እንኳን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ጠንካራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ይፋ አድርጓል።

ኮሚቴው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር ጀኔራል የሚመራ ሲሆን ፦
- ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፣
- ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣
- ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣
-ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
- ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተውጣጡ አመራሮች የተዋቀረ ነው።

@tikvahethiopia
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ መንግስት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል።

መንግስት በመግለጫው "የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የሽብር ወሬ እያሰራጩ ናቸው" ብሏል። ቁልፍ ኢላማቸው ደግሞ በአመራሩና ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ፍርሃትም እንዲነግስ ማሸበር ነው ሲል ገልጿል።

በተለያየ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቻቸው የፀጥታ ችግር እንዳለ በማስመሰል የግል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የማግባባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉም ብሏል።

በህዝቡና በወገኑ ጦር ውስጥ ጥርጣሪዎችን ለመፍጠር የመንግስት ባለስልጣናት ቪዛ እየጠየቁ ነው በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ናቸውም ሲል ገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ ይገኛሉ ብሏል።

በእንዲህ አይነት መንገድ ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#የመንግስት_ጥብቅ_ማስጠንቀቂያ

በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ክስተት ተከትሎ ግጭትን ለማስፋፋት እየሰሩ ያሉ የግጭት ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አስጠንቅቋል።

የጎንደሩን ክስተት ተከትሎ ግጭት ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲስፋፋ እየተሰራ ያለው አሳፋሪ ተግባር በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሃይማኖት ተቀባይነት የለውም ብሏል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ መንግስት የግጭቱ ምክንያት ምንም ይሁን ምን ተግባሩ የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ተግባር ነው ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል።

ህዝቡ የግጭት ነጋዴዎች የሚያተርፉት አንዱን ከአንዱ በማጋጨት መሆኑን በመረዳት ከግጭት አባባሽ ተግባራት እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

ግጭትን ለማስፋፋት የሚደረገውን የትኛውንም እንቅስቃሴ መንግስት አይታገስም ብለዋል።

ጎንደር ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ እስካሁን በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቀዋል።

ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ተጨማሪ ግጭት እና ጥፋት እንዲፈጠር እየሰሩ ያሉ አካላት አሉ ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፤ በዚህ አፍራሽ ተግባር እየተሳተፉ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቀዋል።

ችግሩን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት እየሰሩ ያሉ አካላትን መንግሥት እንደማይታገስ ገልፀው ፤ ወንጀልን በወንጀል ለማካካስ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ከወንጀል ፈፃሚነት ተለይቶ አይታይም ብለዋል።

የአማራን ህዝብ በሃይማኖት፣ በብሔርና በአካባቢ ለመከፋፈል የሚሰሩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አስጠንቅቋል።

#የመንግስት_ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
ሀሰተኛ የትምህርት መረጃ ...

(በዳውሮ ዞን)

በዳውሮ ዞን ፤  ከጪ በተባለው ወረዳ ለመጀመሪያ ዙር በተደረገ ማጣራት ከ264 የትምህርት መረጃ 127 #ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱ ተሰምቷል።

ሀሰተኛ ሆኖ ከተገኘው የትምህርት መረጃ መካከል 6ቱ #የአመራርና ቀሪው #የመንግስት_ሰራተኞች ነው።

የሁለተኛ ዙሪ የማጥራት ስራ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በዚሁ ዞን ፤ ቶጫ በተባለው ወረዳ በመጀመሪያ ዙር ከተደረገው ማጣራት ከ565 የትምህርት መረጃ የ218 ሰዎች #ሀሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

መረጃቸው ወደ ግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ከተጣራው ከ565 የመንግስት ሰራተኞች መካካል የ210 ባለሙያዎችና የ8 #አመራሮች የትምህርት መረጃ ነው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘው።

ይኸው የማጣራት ስራ ይቀጥላል ተብሏል።

መረጃው ከዳውሮ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ያቀረቡት የመሸጫ ዋጋና የተወሰነው መሸጫ ዋጋ ! 👉 ዳንጎቴ - በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 549.49 - አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 811.00 - የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤795.93 👉 ደርባ - በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.59 - አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 779.00 - የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 761.55 👉 ሙገር - በስራ ላይ…
#ሲሚንቶ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በልሁ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ስለሆነው የሲሚንቶ ስርጭትና ግብይት መመሪያ ምንድነው ያሉት ?

አቶ ተሻለ በልሁ ፦

" ... አዲሱ መመሪያ አንደኛ የቀየረው ሲሚንቶ በገበያ ስርዓት ይመራ ነው። በገበያ የሚመራ ሲባል ምን ማለት ነው አከፋፋዮቻቸውን ፤ ቸርቻሪዎቻቸውን የመምረጥ ነፃነት #የፋብሪካዎች ነው። እስከዛሬ ማን ነበር የሚመርጥላቸው ? ሁለቱ ከተሞች እና ክልሎች ነበሩ። ስለዚህ ይሄ መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ #የመንግስት_አካል አከፋፋይ እና ቸርቻሪ አይመርጥም።

ለተወሰነ ጊዜ ምርታማነት እስከሚጨምር በገበያ የሚፈለገውን ያህል መጠን ፋብሪካዎቻችን አምርተው ማሰራጨት እስከሚችሉ ድረስ የፋብሪካ የብር ዋጋ ብቻ በሚኒስቴሩ ይተመናል ይሄም በ6 ወር አንዴ ብቻ ነው እንደ አስፈላጊነቱ ፤ አላስፈላጊ ከሆነ ገበያው እራሱ የሚመራው ከሆነ የዋጋ ተመን አይኖርም።

ሌሎቹን ማን ይተምናቸዋል ? መመሪያው ያስቀመጠው የትራንስፖርት ዋጋን ፣የወራጅ እና አውጪ ዋጋን፣ ውስን ትርፍ ህዳግን መነሻ በማድረግ የፋብሪካ ብር መሸጫ ዋጋን እንደ ቤንች ማርክ ወስደው ፋብሪካዎቹ እያንዳንዳቸው ያሳውቃሉ። ስለዚህ መንግስት ከፋብሪካ ውጭ ያለውን ዋጋ አይተምንላቸውም የሚተምነው ማነው ? ፋብሪካዎች ናቸው ። "

@tikvahethiopia
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል።

አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ " ብሏል።

ግብረሃይሉ ሰልፎቹ በሃይማኖቱ ሽፋን የሚደረጉ እና ሕገወጥ ሰልፎች ናቸው ያለ ሲሆን " በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ ሕገ ወጥ ሰልፍና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት ራሱን ይጠብቅ " ብሏል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ " ከዚህ ውጭ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሎ በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ኃይል እንዲሁም ሰልፎቹን ለማስተባበር እና ለመሳተፍ የሚሞክሩ አካላት ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ ናቸው " ያለ ሲሆን " ለዜጎችና ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል ሕጋዊእርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ " በየክልሉ የምትገኙ የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢያችሁ ሕገወጥ ሰልፎች እንዳይካሄዱ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያኗ፣ለእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች በአጠቃላይ ለሕዝቡ ተገቢውን የደኅንነት ጥበቃ እንድታደርጉ " ሲል አዟል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ። የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል። ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው። አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው። (ዝርዝር ይኖረናል) …
#ዝርዝር

የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ  ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል።

የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ?

#የመንግስት_ግዥ_ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን የማማከር አገልግሎት ለመስጠት በቀጥታ ግዥ በመፈፀም መዋዋሉን ፣ ለአማካሪ ድርጅቱና ለአማካሪ ድርጅቱ ላፀደቃቸው ተቋራጮች ክፍያ በመፈፀም በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጥቆማ ደርሶ ዝርዝር ምርመራ ተደርጓል።

በዚህም በተደረገ የወንጀል ማጣራት ፦

- 195 ሚሊዮን 52 ሺህ 812 ብር ከ81 ሳንቲም የሚያወጡ የተገለያዩ የግንባታ ስራዎች ለዘጠኝ ተቋራጮች ከመንግስት የግዥ አዋጆች እና አፈፃፀም መመሪያ ውጭ በቀጥታ እንዲፈፀም አድርገዋል።

- ዩኒቨርሲቲው ለመሰረተ ልማት ግንባታ የተፈቀደለትን የካፒታል በጀት አላግባብ በመጠቀም የግዥ ህግ እና ደንብ ባልተከተለ መልኩ ዋጋቸው 116 ሚሊዮን ብር የሆኑ 14 ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች በግል ተቋራጭ ድርጅት ስም ግዥ ተፈፅሟል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተሽከርካሪዎቹ እና ማሽነሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ገንዘብ የተገዙ ቢሆንም በግል ተቋራጮች ድርጅቶች  ስም እንዲሆኑ ተደርጋል።

ተሽከርካሪዎቹ እንዲሁም ማሽነሪዎቹ  የተገዙበት ዋጋ እጅግ የተጋነነ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ደብል ጋቢና ፒካፕ ለተሽከርካሪ ተቋራጭ ድርጅቱ ከአስመጪ በብር 3 ሚሊዮን 300 ሺህ ግዥ የተፈፀመ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በብር 6 ሚሊዮን 173 ሺህ 396 ብር ከ83 ሳንቲም እንደተገዛ ተቆጥሮ ክፍያ በመፈፀም ብር 2 ሚሊዮን 873 ሺህ 396 ብር እላፊ ተከፍሏል።

አንድ ሌላ ተሽከርካሪ ግዥ የተፈፀመው በብር 6.1 ሚሊዮን ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በብር 6 ሚሊዮን 415 ሺህ 687 ብር ከ05 ሳንቲም በመግዛት ክፍያ የተፈፀመ በመሆኑ 315 ሺህ 687 ብር ከ05 ሳንቲም እላፊ እንዲከፈል ተደርጓል።

አጠቃላይ የ14ቱ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ባለቤት የዩኒቨርሲቲው ሳይሆን የስራ ተቋራጭ ድርጅቶቹ እንዲሆኑ በማድረግ የተሰጣቸውን የመንግስት ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው ለራሳቸው የማይገባ ጥቅም በማግኘት እንዲሁም አማካሪ ድርጅት በሌለበት የተቋሙ የግንባታ ፅህፈት ቤት በፀደቁ የክፍያ የምስክር ወረቀት 11 ሚሊዮን 532 ሺህ 83 ብር ከ53 ሳንቲም ለተቋራጮች ክፍያ እንዲፈፀም በማድረግ የመንግሥት ሃብት እና ንብረት እንዲባክን አድርገዋል።

- በዶ/ር ጫላ እና ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ በተባለው ድርጅት ላይ በተካሄደው የሃብት ምርመራ ስራ በተገኘው ውጤት ድርጅቱን የሚያንቀሳቅሱት ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ዳይሬክተር ዶ/ር ጫላ ዋታ መሆናቸው በዚህም ድርጅቱ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በገባው ውል መሰረት በድምሩ 23 ሚሊዮን 135 ሺህ 433 ብር ከ27 ሳንቲም ያለአግባብ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የባንክ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ወደ ድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉና ከዚህ በመቀጠል ከድርጅቱ ቢኤችዩ ኃ/የተ/የግል ማህበር የባንክ ሂሳን ተቀንሶ በ6 የተለያዩ ጊዜያት በድምሩ 2 ሚሊዮን 116 ሺህ 16 ብር ከ65 ሳንቲም ወደ ዶ/ር ጫላ ዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ አካውንት ገቢ ተደርጓል።

- በዶ/ር ጫላ ዋታ ባለቤት ስም ወ/ሮ ፀሃይ ኃይሉ ተፈራ ስም 72 ካሬ ላይ ያረፈ በብር 10 ሚሊዮን የተገዛ ባለ 3 ወለል ህንፃ የተገኘ መሆኑና ህንፃው የተገዛበት ገንዘብ በተመለከተ የተደረገው የፋይናንስ ምርመራ ክፍያው የተፈፀመው " ቢዳሩ ኮንስትራክሽን " ከተባለ ድርጅት ብር 4 ሚሊዮን እንዲሁም ደግሞ አቶ ተስፋሁን ሌንጄቦ ሌካ ብር 3 ሚሊዮን 500 ሺህ በተጨማሪ በዚህ ተመሳሳይ ቀን ቦኩይ ኢታንሳ የተባሉ ብር 2 ሚሊዮን 500 ሺህ በዶ/ር ጫላ ዋታ ባለቤት ወ/ሮ ፃሃይ ኃይሉ ስም ወደ ተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ተደርጎ ይኸው ገንዘብ በቀጥታ ለህንፃው ግዥ መዋሉ ታውቋል።

ገንዘቡ ለባለቤታቸው ለወ/ሮ ፀሃይ ኃይሉ ተፈራ ገቢ አድራጊዎች ማንነት ለማጣራት በተደረገው ምርመራ መሰረት በ " ቢዳሩ ኮንስትራክሽን " በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አአ 05069 የሆነ በብር 7 ሚሊዮን 785 ሺህ 157 ከ30 ሳንቲም የተገዛለት መሆኑና ተስፋሁን ሌንጄቦ የተባለው ደግሞ ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ለሚያሰራቸው ግንባታ መሰረተ ልማት እና ኢንፍራስትራክቸር ዝርጋታ ስራ በቀጥታ በደብዳቤ ትዕዛዝ 55 ሚሊዮን 133 ሺህ 893 ብር ስራ የተሠጠው ነው።

- በዶክተር ጫላ ዋታ ስማቸው የተመዘገበ አ/አ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ አንድ ሙሉ ክፍያው የተፈፀመ ኮንዶሚኒየም ቤት በልጃቸው ስም 200 ሺህ ብር በራሳቸው ስም የተገዛ የ1 ሚሊዮን ብር ሼር የተገኘ መሆኑ ተረጋግጧል።

ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አሉ ? ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-04
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ

" በአንድ አገር የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ከዚህ አንጻር በእንጭጭ የሚገኘው የሀገራችን የዴሞክራሲ ስርአት እንዲያብብ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

ህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን #መገደብ እና የፖለቲካ ምህዳሩን #ማጥበብ በሀገራችን ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ይበልጥ ከማባባስ በተጨማሪ ዜጎች እና ልዩ ልዩ የፖለቲካ ኃይሎች መብቶቻቸውን ለማስከበር ሌሎች አማራጮችን እንዲያስቡ እና እንዲጠቀሙ ይገፋል።

ይህንን በመገንዘብ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ #የመንግስት_አካላት በተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ላይ የሚያደርጉትን ህገ ወጥ ጫና በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ በተለይም #በታችኛዉ የአስተዳደር እርከኖች የሚገኙ የገዢዉ ፓርቲ አመራሮች የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ እያደረጉ ያሉትን ከፍተኛ ጫና፣ እስር እና ማዋከብ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ም/ቤቱ በአጽንኦት ያሳስባል "

(የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት)

@tikvahethiopia