TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ታላቅ የጥበብ ድግስና የመፅሀፍ ምረቃ🔝

#ኡቡንቱ, መጋቢት 22 በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል

"ሀገራችን እንድትለወጥና እንድታድግ ኡቡንቱ የግድ ያስፈልገናል!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #Ubuntu

“Umuntu Ngumuntu Ngabantu" የባንቱዎች ቋንቋ ነው:: ሰው ሰው የሚሆነው በሌሎች ሰዎች ውስጥ ነው እንደማለት ነው። በእኛ በሰዎች መካከል አንድ ጥብቅ ቁርኝት አለ:: በዚያ ሰው የመሆን ሚስጥር ውስጥ የኛነታችን ምክንያት እናገኘዋለን። በኡቡንቱ አመለካከት የተሞላ ሰው ህይወት በክፍልፋይ የምትገነባ ሳትሆን በአብሮነት ስሜት የምትሰራ  መሆኗን ይረዳል።

አንድ ትልቅ የፈጣሪ ቤተሰቦች በአንዱ ማደግ ሌሎችም እንደሚያድጉ በአንዱ መውደቅ ሌሎችም እንደሚወድቁ ማመን ሲጀምር ከኡቡንቱ ጋር ተዋውቋል ማለት ነው።

አንድ ከምዕራብ የመጣ የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያ ብዙ ጊዜውን ከአፍሪካ ህፃናት ጋር ያሳልፍ ነበር:: አንድ ቀን ከህፃናቱ ጋር መጫወት ፈለገና ዛፍ ላይ ከረሜላ አስቀምጦ ህፃናቱን እንዲህ አላቸው " ከእናንተ ውስጥ ሮጦ አንደኛ የወጣ ቅርጫት ውስጥ ያለውን ከረሜላ በሙሉ ይወስዳል..."

ህፃናቶቹ መሮጥ ጀመሩ ግን አንደኛ ለመውጣት ሳይሆን እጅለእጅ ተያይዘው ነበር የሚሮጡት። ሁሉም እኩል ደረሱ ሁሉም ከረሜላውን እኩል ተካፍለው በሉት። ይህ ሰውዬ ገረመው 'አንዳቹ ቀድማቹ ሁሉንም መብላት ስትችሉ እንዴት አንድ ላይ ትሮጣላቹ?" ብሎ ጠየቃቸው። ህፃናቶቹ በአንድ ላይ "ኡቡንቱ!" አሉት። ሌሎች ተከፍተው እንዴት ደስተኛ መሆን ይቻለናል? እንደማለት ነው።

(Abrar Amdela)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ

ቲክቫህ ኢትዮጵየ ከፒስ ሞዴል እና ከጋሞ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር "ኡቡንቱ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የአንድ ሳምንት የግንዛቤ ማስጨበጫ ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ ይጀምራል። በተለያዩ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከጋሞ አባቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አብሮ ስለመኖር፣ ስለመከባበር፣ የአንዱ ለአንዱ የመኖር ዋስትና ስለመሆኑ የተለያዩ መልዕክቶች ይተላለፋሉ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day1 #ኡቡንቱ #Ubuntu

አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - #ኡቡንቱ በሚል ርዕስ ያዘጋጀነው የግንዛቤ መፍጠሪ መድረክ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ስኬታማ ነበር። ሁሉንም አካላት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን! ከወጣቶች ጋር የምናደርገው ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ እስከ ህዳር 27 ይቀጥላል።

“Ubuntu is about a community coming together to help one another.”— Paul Pierce

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ፒስሞዴል
#ጋሞዞንአስተዳደር

"ኡቡንቱ" ላይ የምንሰራቸው ሀገር አቀፍ ስራዎች ላይ አስተያየታችሁ፣ ሃሳባችሁን አካፍሉ። በምን በኩል ብንሰራ ውጤት እናመጣ ይሆን? ልታግዙን ይምትችሉ አካላትም አናግሩን! @tsegabwolde
@tikvahethiopiaBot 0919743630
#ኡቡንቱ - 'እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን'

ቲክቫህ ቤተሰቦች - አርባ ምንጭ❤️

ኡቡንቱ - እኛ አንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሆናችን ላይ የተመሠረተ የአፍሪካ ጥንታዊ ፍልስፍና ነው። እኛ ወንድምና እህት ነን። እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው የሚበላው ሲያጣ ሁሉም ሰዎች በዚህ ረሃብ ይሰቃያሉ። አንዱ ሲበደል ሁላችንም ህመሙን ይሰማናል፡፡ አንድ ልጅ በሚሰቃይበት ጊዜ እንባዎች በሁሉም ሰው ጉንጮዎች ላይ ይፈስሳሉ፡፡ የእኛን ተቀዳሚ ሰብአዊነት በመገንዘብ፣ እኛን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ትስስር፣ የሰው ልጆችን በሙሉ የሚያስተሳስር የማይጠፋ ቦንድ ነው።

#Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ #Day2

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ጋሞዞን #ፒስሞዴል

(AFRIKHPRI FOUNDATION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day2 #Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፦ የሃሳቡ ደጋፊዎች፣ ተካፋዮች ፣ አስተባባሪዎች የሆኑ እጅግ የምናከብራቸው የሀገራችን ወጣቶች በተለያዩ የከተማው ክፍሎች በመዘዋወር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ብሮሸሮችን በመበተንና ስለ ዓላማው በማስረዳት ስራቸውን ሲሰሩ ውለዋል። ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

ነገ የ3ኛው ቀን ስራ ይቀጥላል!

ሃሳብ፣ መልዕክት የላችሁ፣ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ልታግዙን የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት ካላችሁ እነዚህ አድራሻዎች ተጠቀሙ፦ @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde 0919743630

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል
#Day3 #አርባምንጭ #ኡቡንቱ

ዛሬ በአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"


ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን!

#TIKVAH_FAMILY

#ፒስሞዴል #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ጋሞዞን #አርባምንጭፖሊቴክኒክኮሌጅ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ተስፋችሁ እኛ ነን፤ ፍቅር አስተምሩን!

አርባ ምንጭ❤️ዊዝደም አካዳሚ❤️

እነዚህ ትንንሽ የነገ ሀገር ተረካቢዎች ስናይ ተስፋችን ተሟጦ እንዳላለቀ በደንብ እንገነዘባለን። ለተተኪው ትውልዱ ከቂም፣ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ከመገፋፋት፣ ከጥላቻነፃ የሆነች ሀገር የማስረከብ ግዴታ አለብን። ለነዚህ ሀገር ተረካቢ ልጆች ፍቅር፣ መዋደድን፣ መተባበርን፣ መደጋገፍን የማስተማር ግዴታ አለበን።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ኡቡንቱ #Day3

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛው አይነት ሃሳብ፣ አስተያየት እና መልዕክት ካላችሁ በ @tsegabwolde ወይም በ @tikvahethiopiaBot ላይ ማድረስ ትችላላችሁ!

@tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #Ubuntu #አርባምንጭዩኒቨርሲቲ

(ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዩኒቨርሲቲው ስላለው ሰላም እንዲሁም አጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል፦

"በከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የአዕምሮ ሥራ የሚሰሩ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚቆዩበት ጊዜም አጭር በመሆኑ ባላቸው ጊዜ አዕምሯቸውን ሙሉ ለሙሉ በሳይንሱ ሥራ ላይ ቢያተኩሩ ወደፊት ለሀገራቸውም ሆነ ለራሳቸው ሙሉ የሆነ የዕውቀትና የክህሎት አስተሳሰብ ታጥቀው ይወጣሉ፡፡ ይህ ባልሆነበት ግን በሌሎች ሀሳብና አስተሳሰብ ጊዜን ማባከን በተሟላ መልኩ ሊያገኙት የሚችሉትን ነገሮችን ያጓድላል፡፡ እኛም እንደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን የምንገኘው ጊዜን መሻማት ላይ ነው፡፡ በዚህም የትምህርት ዘመኑ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌሎች ግቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች እኛንም እኩል የሚያሙን ጉዳዮች ናቸው፡፡ ያሉ ችግሮች ተቀርፈው ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንዲቻል ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት

የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ዝርዝር መረጀዎች ይኖሩናል!

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia