TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀረሪ ክልል⬇️

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ህገ ወጥነትን ለማስቀረት የሚሰራ ኮሚቴ ማቋቋሙን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ገልፀዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕስ መስተዳር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ አገራችን በለውጥ ውስጥ እንዳለች ትላንት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይፈልጉ ጥቅማቸው የተነካ አካላት በእምነትና በጎሳ #ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በክልላችንም አልፎ አልፎ ይኸው ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልፀዋል ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በመቀጠልም #የህግ የበላይነትን ለማስከበር በክልሉ ምክር ቤት የሰላም ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የተከማቸውን #ቆሻሻ አስመልክቶም የከተማዋ ነዋሪዎች እስካሁን ላሳዩት #ትእግስት ምስጋና አቅርበው ቆሻሻው በቀጣዮቹ ሁለት
ቀናት ውስጥ ይወገዳል ብለዋል፡፡

በፀጥታው በኩል #ከቄሮ እና #ፋኖ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ባሉበት ቦታ #ሰኞ ምክክር እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር #ጀማል_አባፊጣ👆

#የStopHateSpeech የሁለት ቀን መድረክ በይፋ ተጀምሯል። በመጀመሪያው ቀን መድረክ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ተገኝተዋል። "ጅማ የመቻቻል የፍቅር የአንድነት ተምሳሌት ናት። የጅማ ሰው ሲመርቅ ቡናና ሰላም ከቤትህ አይጥፋ ይላል። ጥላቻ #ቆሻሻ ነው እራሳችንን ከዝህ ተግባር እንቆጥብ" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በከሰዓቱ መርሃግርብር በወጣት ተማሪዎች መካከል ስለጥላቻ ንግግር ውይይቶች ይደረጋሉ።

Via #Bereket
@tsegabwolde @tikvahethiopia