ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሔፒታይተስን ለመከላከል፣ የምርመራ እና የሕክምና አገልግሎት ለማቅረብ በየአመቱ ተጨማሪ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በተለምዶ የጉበት በሽታ ተብሎ የሚታወቀውን ሔፒታይተስ በጎርጎሮሳዊው 2030 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ፖለቲካዊ አመራር እና ተግባራዊ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዶክተር ቴድሮስ ጥሪ አቅርበዋል።
የዓለም #የሔፒታይተስ ቀን ዛሬ ሲከበር የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት ሔፒታይተስን ከአስራ አንድ አመታት ገደማ በኋላ ከመላው ዓለም ለማጥፋት በየአመቱ ተጨማሪ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ሲሉ ይገልፃሉ። «በመላው ዓለም 325 ሚሊዮን ሰዎች በተላላፊ ሔፒታይተስ ተጠቅተዋል። ከአስሩ መካከል ስምንቱ ለመከላከል፣ ለምርመራ እና ለሕክምና የሚያስችል አገልግሎት አያገኙም። ሁሉም ሰው የሚፈልገውን ክብካቤ እንዲያገኝ #የሔፒታይተስ የሕክምና አገልግሎትን በአፋጣኝ ማሳደግ ያስፈልጋል። ዛሬ የዓለም የጤና ድርጅት ሁሉም መንግሥታት እና አጋሮች ሔፒታይተስን በ2030 ለማስወገድ የሚያስችል ሥራ እንዲሰጡ ጥሪ ያቀርባል። ከዚያ ግብ ለመድረስ የመከላከያ፣ ምርመራ እና የሕክምና አገልግሎቶችን ለማሳደግ የዓለም የጤና ድርጅት በመላው ዓለም በየአመቱ ተጨማሪ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ይገምታል» የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚጠቁመው በመላው ዓለም 325 ሚሊዮን ሰዎች በሒፒታይተስ ተይዘዋል። በየአመቱ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ይሞታሉ። ከሳንባ ነቀርሳ ቀጥሎ ብዙ ሰዎችን የሚገድለው ይኸው ሔፒታይተስ ነው።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia