TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#REPOST

ለኮሮና ቫይረስ በፍጥነት ክትባት ይገኝለት ይሆን ?

በአሜሪካ የጤና ተቋም CDC በኃላፊነት የሚሰሩት ዶክተር ኤርሚያስ በላይ #ETHIOTUBE ላይ ቀርበው ይህን ተናግረዋል ፦

ክትባትን ለመፍጠር ብዙ ሰዎች በተለያዩ ሀገሮች ብዙ ስራ እየሰሩ ነው ያለው። ይሄ ክትባት ሊገኝ እንደሚችል ብዙ ተስፋ አለኝ። በቫይረስ ጥቃት ለሚመጡ በሽታዎች ክትባት ማግኘት በአብዛኛው ጊዜ ብዙ አይከብድም። የሚከብድባቸው ሆኔታዎችም ግን አሉ።

የኢንፉሌንዛ ቫይረስን ብንመለከት በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚተላለፈው፤ ለኢንፉሌንዛ ቫይረስ ክትባት በየአመቱ ይሰራል። ለዚህኛውም ቫይረስ ክትባት እንደሚገኝለት #ተስፋ አደርጋለሁ። ግን ይሄን ክትባት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ከ8-12 #ወራት ሊወስድ ይችላል።

ቫይረሱ ቢጠቃ በክትባት ሊሸነፍ የሚችልበትን ቦታ ማግኘት ያስፈልጋል፤ ይሄ በላብራቶሪ ጥናት ከተደረገ በኃላ ለዛ ክትባት ተዘጋጅቶ በእንስሶች ውስጥ ሙከራ ማድረግ ይፈልጋል፣ ከዛም በሰዎች ላይ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፣ ከዛም ቁጥሩ በዛ ያለ ህዝብ ላይ ይሄ ክትባት ከበሽታው መከላከል መቻሉ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይሄ ሁሉ ሂደት ረጅም ጊዜ ይወስዳል።

አንዴ በጥናት ከተረጋገጠ በኃላ እንኳን ለብዙ ሰዎች እንዲሆን አድርጎ በስፋት ማምረት እንኳን ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ቢያንስ ቢያንስ ሁለትና ሶስት ወራት ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ ክትባት ማግኘቱን ቀላል ነገር ተደርጎ ቢታሰብም ለግለሰቦች እንዲባዛ አድርጎ ማቅረቡ በጣም ጊዜ ይወስዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

አንድ ታማሚ ከኮሮና ቫይረስ አገገመ የሚባለው መቼ ነው?

አንድ ታማሚ ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በሽታ ሙሉ ለሙሉ አገገመ የሚባለው ለሶስት (3) ተከታታይ ቀናት ምንም አይነት ምልክት ሳይኖረው ሲቆይ እና በሚደረግለት ሁለት ተከታታይ የላብራቶሪ ምርመራ ነጻ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ምንጭ፦ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

አዲሶቹ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ፦

ተከታታይ ቁጥሮች ፦

የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ።

ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት ፦

የብሩን ዋጋ የሚገልፅ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት አለው።

ጎርባጣ መስመሮች ፦

የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል።

ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደህንነት መጠበቂያ ምልክት።

የደህንነት መጠበቂያ ክር ፦

የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥ NBE ፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተፅፎ ይገኛል።

የውሃ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልክት ይታያል።

ትይዩ ምልክት ፦

የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘብ በስተኃላው ካለው ተመሳሳይ ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ።

ፈሎረሰንስ ምልክት ፦

አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ ፍሎረሰንት ምልክት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳትጭበረበሩ አዲስ ታትመው ስለተሰራጩት የብር ኖቶች የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች መረጃ ይኖራችሁ ዘንድ ከላይ ያለውን ምስል ተመልከቱ።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት ምን ያስፈልገኛል ?

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት አመልካቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. ይህን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሰነዶች ማዘጋጀት ፦

• ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ
• የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት/ማስረጃ

2. የሚያመለክቱት ለአስቸኳይ አገልግሎቶች ከሆነ ከሚከተሉት መካከል ቢያንስ አንዱ ሊኖርዎት ይገባል ፦

• የሕክምና ደብዳቤ
• የትምህርት እድል እና ዲቪ
• ከተፈቀደለት ድርጅት የተጻፈ ደብዳቤ
• የውጭ ሀገር የነዋሪነት ፍቃድ
• የግብዣ ደብዳቤ
• አስቸኳይ የስራ ጉዞ
• በሀዘን/ጋብቻ ምክንያት የሚደረግ ጉዞ

3. ለአዲስ ፓስፖርት የሚከፈለውን ክፍያ ያረጋግጡ ፦

• ለ32 ገጽ ፓስፖርት - 600
• ለ64 ገጽ ፓስፖርት - 2186 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍላችሁ online አድራሻ ላይ አባሪ ያደርጉታል።

ኦንላይ ላይ "ለአዲስ ፖስፖርት" አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎት ለማግኘት ይህን ሊንክ ተጠቁሙ👇
www.ethiopianpassportservices.gov.et

@TIKVAHETHIOPIA
#REPOST

በግጭቶች ፣ በሌሎች የብጥብጥ ሁኔታዎች / በአደጋዎች ወቅት ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ወይም ሊጠፉ ይችላሉ።

ይህ ሁኔታ በቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ላይ ጭንቀትና አለመረጋጋት ይፈጥራል።

ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ወይም የጠፉ ዘመዶቻቸው ምን እንደገጠማቸው የማወቅ #መብት አላቸው።

የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ የዘመዶቻቸውን ዕጣ ፈንታ እና የት እንደሚገኙ ለማወቅ የሚጥሩ ቤተሰቦችን ይደግፋል ፤ ያግዛል።

የICRC አገልግሎትን ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የICRC ኢትዮጵያ ልዑክ 0943122207 / 011 552 71 10 ላይ በመደወል ማነጋገር ይቻላል።

(ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00 - 11:00 ሰዓት)

* የስልክ መስመሮቹ ሊጨናነቁ ስለሚችሉ ደጋግማችሁ ሞክሩ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#REPOST

ኣብ ግጭታት እዋን ኣብ ካልኦት ናይ መጥቃዕቲ ኩነታት ወይ ከኣ ሓደጋታት ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ክጠፍኡ ወይ ክእሰሩ ይኽእሉ ፤ እዚ ድማ ኣብ ስድራቤቶም ጭንቀትን ዘይምርግጋዕን ይፍጠር።

ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ስድራቤቶም ናይ ምፍላጥ መሰል ኣለዎም።

ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ድማ ስድራቤቶም ዝጠፍእዎም ቤተሰብ አበይ ከምዘለዉ ንምፍላጥ ንምድጋፍ ይደሊ።

ኣገልግሎትና ዝደቢ ዝኾነ ሰብ ድማ ናብ ኢትዮጵያ ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ልኡኽ ፦
- 0943122207
- 0980192706
- 0980192709
- 011 552 71 10 ብምድዋል ምዝራብን ምርካብን ይኽእሉ ኢዮም።

(ካብ ሶኒ እስካብ አርቢ ካብ 2፡00 ሰዓት እስካብ 11፡00 ሰዓት)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ማን ናቸው? 

( በቲክቫህ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ #Repost )

- ገና በሕጻንነታቸው የተደገሰላቸውን የጋብቻ ድግስ ጥለው አዲስ አበባ ገቡ።

- ለትምህርት ወደ ውጪ ሊላኩ ብለው በመጨረሻ ሰዓት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

- ወላጅ አልባ ሕጻናትን በማለታቸው የሞቀ ትዳራቸውን ጥለው በዶሮ ማርቢያ ቤት ውስጥ ተቀመጡ።

- ድርጅታቸው እራሱን ችሎ ገቢ ማግኘት ሲጀምር የለፋውበት ነው ብለው አንደም ሳንቲም ለግላቸው ተጠቅመው አያቁም፡፡ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ቢሆኑም ደሞዝ አይቀበሉም፡፡

- በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 1.5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ድጋፍ አግኝተው የሕይወት መስመራቸው ተስተካክሏል፤ 2700 በላይ ሕጻናት በእቅፋቸው አድገዋል።

- በዚህ ስራቸው የበጎ ሰው ሽልማትን ጨምሮ በርካታ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሽልማቶችን ወስደዋል።

Readmore https://telegra.ph/ይህንን-እንወቅ--ክብርት-ዶር-አበበች-ጎበና-ማን-ናቸው-06-04
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia