TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርቃት

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የሚያስመርቋቸው።

ዘንድሮ ከተሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ በምርቃት መርሃግብር ላይ ከመሳተፍ ጋር በተገናኘ በተመራቂዎች ዘንድ ጥያቄዎች የነበሩ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ የተቋማቱ #የሴኔት ውሳኔ ጉዳይ መሆኑን ገልጾ ነበር።

በዚህም መሰረት በተቋማት ሴኔት ውሳኔ ለምርቃት ብቁ የሆኑ / የምረቃ ፎርማሊቲ የሚያሟሉ ተማሪዎች የምርቃት ስነሥርዓት ላይ ይሳተፋሉ ፤ ነገር ግን ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃቸውን የሚወስዱት የመውጫ ፈተና ያለፉት ብቻ ናቸው።

የተቋማት የምረቃ ቀን መቼ ነው ?

ነገ ረቡዕ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ተቋማት መካከል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይገኝበታል።

የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦

- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) ፤ ጊምቡ እና ሻምቡ በነጋታው።
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) ፤ በ15/2015 (ቡሬ ካምፓስ)
- ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ) ፤ በነጋታው በሳውላ ካምፓስ
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
- ዲላ ዩኒቨርሲቲ
- እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)  በነጋታው (ዱራሜ ካምፓስ)
- መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
- ቀብሪ ድሃር ዩኒቨርሲቲ
- ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ በኃላ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከሐምሌ 16 ጀምሮ ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#tikvahethiopia

@tikvahethiopia