TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከድሬዳዋ ወጣቶች፦

ለመጀመሪያ ጊዜ በድሬዳዋ ብስራተ ገብረኤል ት/ቤት እና በእመቤታችን ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በመሰረቱት የሽልማት እና የድጋፍ ማህበር በአይነቱ ልዩ የሆነ ውድ እና አንጋፋ መምህራኖቻችንን የምንሸልምበት እና የምንዘክርበትን የመጪው ታዳጊ ልጆቻችን እና የድሬ ተስፋዎችን በርቱ ጠንክሩ የምንልበት የሽልማት እና የድጋፍ መርሃግብር ቅዳሜ ሐምሌ 20, 2011ዓ/ም በብስራተ ገብርኤል ት/ቤት ለማከናወን ዝግጅቱን ጨርሶ ታዳሚዎቹን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። የማይቀር የማይታለፍ መርሀ ግብር! ከእናንተው ልጆች ለእናንተ ልጆች!
#ሀምሌ21 #2_ቀን_ቀርቶናል!

የዚህ ገፅ #ባለቤት የሆናችሁ በሙሉ ይህ የናተ ቀን ነውና እሁድ ሃምሌ 21 ከቀኑ በ6:00 ሰዓት በአበበች ጎበና የህፃናት ማሳደጊያና ልማት ድርጅት እንድትገኙ ከታላቅ አክብሮት ጥሪዬን አቀርባለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንገናኝ #ሀምሌ21

R= ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን (ከፒያሳ ታክሲ መያዝ ይቻላል)

T1= ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሲመጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን ያገኛሉ፡፡ አስፓልቱን ትተው ቀጥታ የሚወስደውን ኮብልስቶን መንገድ ይዘው ይጓዙ

T2= ኮብልስቶኑን ተከትለው ቀጥታ ሲጓዙ የአስፓልት መንገድ ያገኛሉ ከዛም ወደ ቀኝ(ወደ ላይ) ይታጠፋሉ፡፡

T3= አስፓልቱን እንደያዙ ወደ ላይ ትንሽ ከፍ እንዳሉ ወደ ድርጅቱ መግቢያ ያገኛሉ፡፡

📌 በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እለቱን የተመለከቱ ባነሮች መሰቀላቸውን ያረጋግጡ፡፡

Google Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡
#update የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በለጠ ካሳ መታሰሩን ንቅናቄው አስታውቋል፡፡ በለጠ የታሰረው ፖሊስ ትፈለጋለህ ብሎት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከሄደ በኋላ ነው፡፡

በተጨማሪ፦

1. አቶ አንተነህ ስለሺ የአብን የአዲስ አበባ የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ እና
2. አቶ ንጉሴ ይልቃል የአብን የየካ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ በአዲስ አበባ 3ኛ ፓሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አብን አስታውቋል። ለአቶ አነተነህ እስር ፓሊስ ያቀረበው ምክንያት የአሰምነውን ፎቶ በኪሱ ይዞ ተገኝቷል የሚል ነው ሲልም ንቅናቄው በፌስቡክ ገፁ አሰራጭቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updatesport በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ከጅቡቲ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ በአስቻለው ታመነ ጎል 1-0 አሸንፋለች፡፡ የመልሱ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ በቀጣ ሳምንት ይደረጋል፡፡

IVia Soccer Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA

ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ማካሄድ ጀምሯል። በዋነኛነት የኦሮሞን ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህል ለማጥናት የተቋቋመው ኦሳ፤ ላለፊት 32 ዓመታት ጉባኤውን ከኢትዮጵያ ውጪ ሲያካሄድ ነበር።

ዛሬ በተጀመረውና ለሦስት ቀን በሚቆየው ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ፕሬዘዳንት ኩለኒ ጃለታ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ስለ ኦሮሞ ታሪክ ያለውን የተዛባ ትርክት ለማስተካከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ከኦሮሞ ቋንቋ እና ባህል ውጪ ስለሌሎች ብሔረሰቦች ታሪክ በማጥናት ጽሁፎች ያዘጋጃል። በዚህም የተቀረው ዓለም ስለነዚህ ማህበረሰቦች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ፕሬዘዳንቷ ተናግረዋል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ እስካሁን የጥናት ተቋሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በፖለቲካ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ተገዶ የነበረው የጥናት ተቋምና ደጋፊዎቹ "አሸንፈዋል" ብለዋል። "ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ ልጆቻችሁ እንኳን ተመለሱላችሁ" ብለዋል አቶ ሽመልስ በንግግራቸው።

አሁን ያለው ትውልድ የገዳ ሥርዓት እንዲጠነክር እየተካሄደ ያለው ጥናትና ምርምር እንዲቀጥልበት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጥሪ አስተላልፈዋል። "ተሳታፊዎች በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል የጀመረው 'የዜግነት አገልግሎት' ሥራ ላይ እንደውል ሊደግፉ ይገባል" ብለዋል።

የኦሳ ፕሬዘዳንት፤ የጥናት ተቋሙ የጥናት ማዕከል ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ፍኖተ ካርታ ማሳየት አለበት ብለዋል። በጉባኤው ላይ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ምሁራን ይታደማሉ።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በወረብ ቆላ ጽዮን አውሎ ነፋስ እና በረዶ ቀላልቅሎ በጣለ ዝናብ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። ሐምሌ 18 ቀን 2011ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ አውሎ ነፋስ እና በረዶ ቀላለቅሎ በጣለ ዝናብ በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል። ሐምሌ 18/ 2011 ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰው ውሽንፍር የቀላቀለ ዝናብ በርካታ ቤቶች የቆርቆሮ ክዳናቸውን አጥተዋል። ከቤቶቹ በተጨማሪ በጣለው በረዶ ሰብል ላይም ጉዳት ደርሷል። ነዋሪዎቹ የተነቀለው ቆርቆሮ ከአካባቢው እንደጠፋ እና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። የወረብ ቆላ ጽዮን ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ጥጋቡ በለጠ እንደተናገሩት ከ300 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እገዛችንን ከፈለገ ከጎኑ እንቆማን አለ፡፡
.
“የደርግ ሰራዊት” የሚለው የበፊት መጠሪያው “የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት” በሚል ተቀይሮ ከመንግስት እውቅና እንደተሰጣቸውም የማህበሩ መሪዎች ተናግረዋል፡፡ “አሁንም የኢትዮጵያን #አንድነት ለማስጠበቅ ከቆመ መንግስት ጋር አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡

በመላው አገሪቱ 53 ቅርንጫፎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ የማህበሩ ሀላፊዎች በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት ማለታቸውን ከጋዜጣዊ መግለጫው ሰምተናል፡፡ ማህበሩ ከቀድሞዎቹ ሚሊሺያዎች እስከ ከፍተኛ የጦር መኮንንነት የደረሱ አባላት እንዳሉት ተነግሯል፡፡

ምንጭ - ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሐምሌ 22 ቀን የሚደረገዉን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን በተመለከተ ያስተላለፉት መልእክት👇
https://telegra.ph/PMO-07-26

#አረንጓዴአሻራ
#PMOEthiopia
ኢራን የሚሳኤል ሙከራ አደረገች!

ኢራን የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ሙከራ #በመተኮስ፣ በፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ያለውን ውጥረት ማባባሷን፣ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለሥልጣን አስታወቁ። በስም እንዲጠቀሱ ያልፈለጉት እኝህ ወታደራዊ ባለሥልጣን ትናንት ሐሙስ እንደገለጹት፣ የዕሮብ ዕለታው የኢራን ሚሳይል ሙከራ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ወታደራዊ ጦር ሰፈር የሚያሰጋ አልነበረም።

ከደቡባዊ ኢራን ወደብ አካባቢ የተተኮሰው ሚሳይል፣ በ1,100 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ፣ በዋና ከተማዋ ምሥራቃዊ ቴህራን ላይ መውደቁም ተሰምቷል። ሚሳይሉ ከመተኮሶ አስቀድሞ ግን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን የሚሳይል ሙከራ ጣቢያ ስትከተል እንደነበር እኝሁ በስም ያልተጠቀሱ ወታደራዊ ባለሥልጣን ተናግረዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለጥያቄው_ምላሽ፦ TIKVAH-ETH የተመሰረተው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በሃምሌ 19/2009 ዓ/ም ነው። TIKVAH በተመሰረተበት ወቅት የቤተሰቡ አባላት 20 አይደርሱም ነበር። የነበሩትም #ንቁ ተሳታፊ አልነበሩም። ዛሬ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኘው የቤተሰባችን አባል ከ320 ሺ በላይ ነው። በተመሰረተበት ወቅት ቀለል ያሉ የመዝናኛ ነክ ጉዳዮችንና ፎቶዎችን ያቀርብ ነበር። ለጥቂት ጊዜ ትውውቅ ከተደረገ በኃላ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበረው ችግር ሳቢያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተማሪ ድምፅ ሆኖ አገልግሏል።

TIKVAH ማለት #ተስፋ ማለት ነው!

√እኛ ማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበት፤ ሰውነቱ ሲከበር ብሄሩ፣ ቋንቋው፣ ባህሉ፣ አመለካከቱ፣ እምነቱ የሚከበርበት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ አስተማማኝ ደህንንነት እና ሰላም ያለባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ ማንም ሰው በአመለካከቱ የማይገፋበት ለሁሉም ዜጎች እኩል የሆነች ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን!

√እኛ አይደለም ለኢትዮጵያዊ በምድር ላይ ላለሰው ሁሉ የምትሆን ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ ዜጎቿ የማይበደሉባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

#ተስፋችን_ደግሞ_በፍጡር_ሳይሆን_በፈጣሪ_ብቻ_ነው!

ይህ አቋማችን የዛሬ ሳይሆን የነበረ፤ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው!! #ETHIOPIA

🏷ይሄ ቤተሰብ "የኢትዮጵያ ተስፋ" ነው ብለን እናምናለን!! በመነጋገር የሚያምን ከጥላቻ የራቀ፤ ስድብ የሚፀየፍ አንድ ጠንካራ የሆነችን ሀገር ለመገንባት ዘውትር የሚተጋ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ስብስብ ነው።

ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈቱ።

ከተጠረጣሪዎች መካከል በነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 57 ጉዳያቸው ተጣርቶ ሐምሌ 19 ቀን 2011ዓ.ም ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/15-07-27
#update በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በመልካም አስተዳደር እና ሌሎች ጥያቄዎች ምክንያት በወረዳው በሚገኙ አንደንድ ቀበሌዎች ለ11 ወራት ተሷተጓጉሎ የነበረው መንግስታዊ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመራቸውን የአበሽጌ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል። በወረዳው ዛሬ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮችን ያሳተፈ የእርቅ እና የሠላም ስነ-ሰረአት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ለክልሉ ሕዝብ ሠላም ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ በራቸው ድረስ በመሄድ ለመሥራት ተዘጋጅተናል፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ
.
.
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለአማራ ሕዝብ ክልል ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ክልሎች ሠላምና ፀጥታም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የአብመድን በጎበኙበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ለክልሉ ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ ለመሥራት በራቸው ድረስ ለመሄድ ተዘጋጅተናል›› ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ በቅድሚያ የሚጠቅመው የክልሉን መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ‹‹የአማራ ክልል ሕዝብ ከክልሉም ውጭ ስለሚኖር የሌሎች ክልሎች ሠላምና ፀጥታ የአማራ ክልልም ጉዳይ በመሆኑ ከክልሎች ጋር አብረን ለመሥራት ተዘጋጅተናል›› ነው ያሉት፡፡

‹‹ወደ ስልጣን የመጣሁበት ወቅት የክልሉ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት በማያውቀው መልኩ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረበት ነው›› ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉን ከዚህ ቁዘማ ለማውጣትና የፀጥታ ስጋት የማይፈጠርበት እንዲሆን እየሠሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ማስጠበቅ የፀጥታ ኃይሉ ብቻ ኃላፊነት አለመሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ‹‹የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ብዙኃን መገናኛ ለክልሉ ሕዝብ ሠላም አበክረው ሊሠሩ ይገባል›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የሕዝቡን የሠላምና የፀጥታ ስጋቶች በመለዬት መሥራት የሚዲያው ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ማኅበራዊና ባሕላዊ እሴቶችን ሽፋን መስጠት ላይ ሚዲያዎች እንዲያተኩሩም ጠቁመዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#አምቦ

በአምቦ ከ5መቶ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፖለቲካ ኃላፊም አባላትና፣ ደጋፊዎቼ እንዲሁም አመራሮቼ ታስረዋል ብሏል፡፡ የከተማው ፖሊስ መምሪያ የታሰረ ሰው የለም ሲል አስተባብሏል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ለክልሉ ሕዝብ ሠላም ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ በራቸው ድረስ በመሄድ ለመሥራት ተዘጋጅተናል›› - ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከተንከባከብነው የማይፀድቅ ችግኝ የለም። ካስተማርነው የማይለወጥ እና የማያድግ ወጣት የለም።" አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
.
.
"ከተንከባከብነው የማይፀድቅ ችግኝ የለም። ካስተማርነው የማይለወጥ እና የማያድግ ወጣት የለም" የሚሉ እና ሌሎች መርኾችን በመያዝ የአረንጓዴ ልማትን ለመደገፍ የመልካም ወጣት 2011 "መልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት" የመጀመሪያው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ትላንት በሀዋሳ ታቦር ተራራ ተከናውኗል።

በዚህም የችግኝ ተካላ መርሀግብር አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ: የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና አባላት: የማርሲል ቴሌቪዥን ሰራተኞች እና ከ4000 የሚበልጡ የመልካም ወጣት የ2ኛው ዙር ሰልጣኞች ተሳትፈውበታል።

የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 22 በአረንጓዴ አሻራ ቀን በአንድ ጀንበር 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተያዘው ዕቅድ ለመሳተፍም ማር ሲል ቴሌቪዥን ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ተገልጿል።

Via #ማርሲል_ቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእጅ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ...

በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ የተቀመጠ የእጅ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ባልደረባ ኮማንደር ናስር ኡመር ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  እንደገለጹት አደጋው በ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ላይ የደረሰው ትናንት ነበር።

አደጋው የደረሰው በከተማዋ  ምዕራብ ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ውስጥ በሕገ ወጥ  መንገድ የተቀመጠ ቦምብ ወጣቷ ስትነካካት እጇ ላይ በመፈንዳቱ ነው ብለዋል፡፡
በአደጋው በቤት ውስጥ በነበረ ንብረት ላይም ጉዳት መድረሱንም ገልጸዋል።

ፖሊስ ቦምቡን አስመልክቶ  ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ኮማንደር ናስር አስረድተዋል። ኅብረተሰቡ ሕገወጥ መሳሪያዎችን በቤት ውስጥ ደብቆ ማስቀመጥ ወንጀል መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ  እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 72ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከስብሰባው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የዛፍ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia