TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#GoE የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክተኞች እና አምባሳደሮች የመቐለ ቆይታን በተመለከተ ጉዳዩን የያዙበት መንገድ በመንግስት ላይ ቅሬታ እንደፈጠረበት ገልፀዋል። አምባሳደሩ፤ ልዩ መልዕክተኞቹ እና አምባሳደሮቹ ለሰላም ንግግር ጥረት ማድረግ ሲገባቸው በሌላ ወገን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ላይ ተጠምደዋል ብለዋል። "…
#ድርድሩ

በአዲስ አበባ ከፌዴራል መንግስት ጋር እንዲሁም መቐለ ተጉዘው ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ካለው ህወሓት ጋር ሰሞኑን የተወያዩት የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔቴ ዌበር ከጀርመን ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በፌዴራል መንግስት እና ህወሓት መካከል ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የሰላም ድርድር " የመተማመን መጥፋት " መሰናክል መሆኑን ተናግረዋል።

ዌበር ለሬድዮ ጣቢያው " ዋነኛው መሰናክል (ለሰላም ድርድሩ) የእምነት እጦት ነው ብዬ አስባለሁ። አንዱ ከሌላው ጋር በቅን ልቦና እየተደራደሩ ለመሆናቸው የበለጠ መተማመኛ እንደሚፈልጉ 2ቱም ግልፅ አድርገዋል።

ሁለቱ ወገኖች ዝግጁነታቸውን ከማሳወቅ ባሻገር ወደ ድርድሩ እንዲመጡ የሚያስፈልገውን መተማመን የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ያጠናክራሉ ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ።

የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎች እንደሌሉት አረጋግጧል። ከመንግስት በኩል የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር ምልክት ከሰጠ ወይም ካስጀመረ ህወሓት በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በመቐለ ጉብኝታችን ተረድቻለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ ዌበር በጥቂት ቀናት ውስጥ ስራ ይጀምራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ከሬድዮ ጣቢያው ጋር በነበራቸው ቃለምምልስ ወቅት ተናግረዋል።

ዌበር " እኛ አሁን እጅግ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ ከሚጀምሩበትን፤ መጀመራቸውን እየተጠባበቅን ነው። በዚህ ረገድ ከአዲስ አበባም ሆነ ከመቐለ የተቀየረ ነገር ካለ አልሰማሁም፤ ነገር ግን ይህ በማንኛውም ቀን ተግባራዊ ይሆናል ብዬ እጅግ ተስፋ አደርጋለሁ። " ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/EU-08-05

@tikvahethiopia
" በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " - ፕ/ር መስፍን አርአያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

አሁንም " ወደ ምክክር መድረኩ ኑ " ያለው ኮሚሽኑ ፤ ለታጠቁ አካላት ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና በኮሚሽኑ እንደሚያመቻች ገልጿል።

ይህ የተሰማው በምክክር ጉባዔው የሚሳተፉ የኦሮሚያ ክልል ማህበረሰብ ተወካዮች የማጠቃለያ ልየታ መድረክ በሻሸመኔ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

" በትጥቅ ትግል ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ #ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " ያሉት ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ " የሚያዋጣን ይሄ ነው ፤ በየታች ድረስ ሄደን ያገኘነው ህዝባችን ሰላምን እንደሚፈልግ ነው የገለጸለን  " ብለዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ በበኩላቸው ፥ እንዲህ አይነት ምክክር ትልቅ ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።

" ይህን አጋጣሚ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ሊጠቀሙበት ይገባል " ብለዋል።

" በተለይ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካላት ወደ መድረኩ ሊመጡና ሀሳባቸውን ሊገልጹ ይገባል ፤ እነሱ መጥተው በሚሳተፉበት ጊዜ ኮሚሽኑ ተገቢውን #የዋስትና_ጥበቃ /safe space/ የሚያመቻች ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዶቼቨለ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia