TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር ነው የሚገኙት " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ 7 ታዳጊዎች #እንደጠፉ እና #እንደታገቱ ተደርጎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ነው አለ።

ፖሊስ መረጃው እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ስለመሆኑ #አረጋግጥላችኃለሁ ብሏል።

ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

ፖሊስ ምን አለ ?

- #አራት ወንድ እና #ሦስት ታዳጊ ሴቶች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 " መካኒሳ ቆሬ " አካባቢ ከሚገኘው የወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት እንደጠፉ እና ታግተዋል በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም።

- ታዳጊዎቹ ለመጥፋት በማሰብ ከወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት ልብሶቻቸውን ይዘው እንደወጡ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው መኖር እንደሚፈልጉ በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

- በልመና ተግባር ላይ ተሰማርተውም ባገኙት ገንዘብ የተወሰኑ የቤት ቁሳቁስ በማሟላት ሰባቱም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው " ቡልቡላ " አካባቢ በ1 ሺ 800 ብር መኖሪያ ቤት ተከራይተው #ሦስቱ ወንዶችና #ሦስቱ ሴቶች #የፍቅር_ግንኙነት በመመስረት በጋራ እየኖሩ እንደሚገኙ እራሳቸው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

- የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ከተለያዩ ቦታዎች መረጃ በማሰባሰብ በተደረገው ክትትል ያሉበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ ተችሏል።

- ታዳጊዎቹ የስነ-አእምሮና ተያያዥ የጤና ምርመራ እንዲያገኙ እንዲሁም ማህበራዊ ችግራቸው ሊፈታ በሚችልበት ሁኔታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው።

- አንዳንድ መገናኛ ብዙኃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃን ስላገኙ ብቻ  የሚያስከትለውን አሉታዊ ጫና ታሳቢ ሳያደርጉ ዜናውን ማሰራጨታቸው በህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያስከትል መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው ሊገነዘቡ ይገባል።

- ወንጀልን በማጣራት እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ስራ ጊዜን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia