TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ጾመ ፍልሰታ እና የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ! በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ " የጾመ ፍልሰታ " መልዕክት አስተለልፈዋል። ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦ " . . . እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ…
#EOTC

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው #በፍቅር እንዲኖሩ እና #ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳሰቡ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ያሳስቡት ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የጾመ ማርያም ሱባኤ ማጠናቀቂያ በዓል ላይ ነው።

ቤተክርስቲያንኗ ፤ " በኢኦተቤ በዐዋጅ ከተደነገጉት አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገተ ሥጋ አስመልክተው ሐዋርያት የጾሙት ጾመ ማርያም በየዓመቱ በወርሓ ነሐሴ ከመባቻው አንስቶ ባሉት 16 ቀናት ካህናት እና ምእመናን ሌሊት በሰዓታት ጸሎት፤ ቀን በሥርዓተ ቅዳሴ በመሳተፍ በሕብረት ያሳልፉታል " ብላለች።

" በዚህ በጾመ ማርያም ወይም በተለምዶ የፍልሰታ ጾም ተብሎ በሚታወቀው ወቅት በርካታ ምእመናን እንዲሁም ሕጻናት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሥርዓተ ቅዳሴውን ይከታተላሉ፤ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ይቀበላሉ " ስትል ገልጻለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ ሕጻን ዐዋቂው፤ ወንድ ሴቱ የክረምት ብርድ እና ዝናብ ሳይበግረው በሕብረት በሚጸልበት የሱባኤ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት እና ምእመናንን በመባረክ ማሳለፋቸውን ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር  በገዳሙ ተገኝተው በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በቅዳሴው መካከል ባስተላለፉት ትምህርትና ቃለ ቡራኬ " የሰላም ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔርን ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው በፍቅር እንዲኖሩ እና ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳስባለሁ " ብለዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሱባኤው ወቅት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ 

መረጃ እና ፎቶ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ/ጽ/ቤት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia