TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረር ውሃ ማግኘት ጀመረች‼️

በህገ-ወጦች እገታ ውሃ አጥታ የከረመችው #ሐረር የተወሰነ አካባቢዋ ውሃ #ማግኘት ጀመረ፡፡

በአምስት ቀን ውስጥ 10 ሚሊዮን ብር ይከፈለን ያሉ የሃሮማያ አካባቢ ወጣቶች የውሃ ማጣሪያ ቁልፉን ነጥቀው መውሰዳቸውንና ሞተሮቹንም ማጥፋታቸው ይታወስ ነበር፡፡

የከተማዋ የውሃ ፍሳሽ ቢሮ ሀላፊ አቶ #ተወልደ_ሀብዶሽ እንደተናገሩት በበዛ ጥረት #ቁልፉን አግኝተናል ብለዋል፡፡

ከምስራቅ ኦሮሚያ አስተዳደር፣ ከአወዳይ ከንቲባ ጽ/ቤትና ከሃሮማያ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በእምቢተኝነታቸው ፀንተው ከነበሩ ወጣቶች ቁልፉን ተረክበናል ብለዋል፡፡

የውሃ ማጣሪያ ጣቢያው የተወሰኑ የመቆጣጠሪያ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተቃጥለው ተገኝተዋል፡፡

አንድ ቀን በፈጀ የጥገና ስራ አሁን የሃሮማያ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ ስራ #ጀምሯል ብለዋል፡፡

በመሆኑም አንድ ሶስተኛው የሃረር ከተማ አካባቢ ውሃ እያገኘ መሆኑን አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡

አጥፊዎችም #ለህግ እንዲቀርቡ ስራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ ሌላው የሃረር የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ህገ-ወጥ የካሳ ጥያቄ ባቀረቡ ቡድኖች የውሃ መስመሩ ተሰብሮ የነበረው ኤረር አካባቢ የሚገኘው ነበር፡፡ ይህ ግን ገና እልባት ያላገኘ መሆኑን ከከተማዋ የውሃና ፍሳሽ ቢሮ ሀላፊ ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1 FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ‼️

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪውን ያቀረቡት ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው።

መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለፖለቲካ ጥቅም የማዋል ዝንባሌ እንደሚኖር ቀድሞ ተረድቶ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ውይይት ቢያደርግም በተወሰኑ ተቋማት ግጭቶች ተከስተው የተማሪዎች ህይወት መጥፋቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታሰዋል።

“በመሆኑም ተማሪዎች የማንም ፖለቲካ ኃይል ዓላማ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ እራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው” ሲሉ ምክር ሰጥተዋል።

“ተማሪዎችን እሳት እያስጨበጡ የፖለቲካ የበላይነት ለማምጣት የሚፈልጉ ሃይሎች፤ ተግባራቸው ህገ-ወጥና ጊዜው ያለፈበት መሆኑን በመገንዘብ እጃቸውን ይሰብስቡ” ሲሉም አሳስበዋል።

ከተማሪዎች በተጨማሪ ሁሉም ህብረተሰብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመሰል ሁኔታዎች ጸድተው የስልጠናና ምርምር ማዕከል እንዲሆኑ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቀርበዋል።

መንግስት #አጥፊዎችን #ለህግ ከማቅረብ በተጨማሪ የህግ የበላይነን ለማስፈን ከመቸውም ጊዜ በላይ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በክልሉ #ወንጀል ሰርተው የተደበቁ አሉ፡፡ ይሄንን ያስተባበረ ያቀናበረ ተልዕኮ የሰጠ እጁን ያስገባ አካል ካለ ተጣርቶ #ለህግ ይቀርባል፡፡" የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲ በድሪ ለአዲስ ዘመን የተናገሩት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia