TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ

በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከፍተኛ የመንግስት የትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ያህል አልተወጡም ተባለ፡፡ ለሰላም ግንባታ የዪኒቨርሲቲዎች ሚና በሚል መሪ ቃል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከምሁራንና ተማሪዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡ የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ የህግና ጉድ ገቨርናንስ ትምህርት ክፍል ከሴንተር ኦፍ ኮንሰርን ጋር በመተባበር ለሰላም ግንባታ የዩኒቨርሲቲዎች ሚና በሚል መሪ ቃል ከምሁራንና የሁለተኛ ዲግሪ የሰላምና ግጭት አፈታት የሚያጠኑ ተማሪዎችን ያሳተፈ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትና የአመራር ሽግሽግ አደረገ!

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ የአመራር ሽግሽግ አደረገ። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባደረገው አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትና የአመራር ሽግሽግ አቶ መልካሙ ወርቁ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ቦንቴ ቦቼ የከተማዋ የደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ኮሌኔል ሮዳሞ ኪአ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣ ምክትል ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና አቶ ሀይለዮሐንስ ነጌሶ የቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርጎ መሾሙን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ዘግቧል።

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላጆች ልጆቻችሁን አስመዝግቡ!

በ2012 የትምህርት ዘመን ከ 7 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን መዝግቤ ለማስተማር እየሰራሁ ነው አለ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ፡፡ በመላው የክልሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም ሁለት ብቻ መሆኑን ወላጆች አውቀው ልጆቻቸውን ከወዲሁ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ እንዳሉት በ2012 የትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን፤ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል 4 ነጥብ 7 ሚሊየን፤ ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ደግም 6 መቶ 81 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመን አላርም ትሁነን!

•ከ70 ሺህ በላይ ንፁሃን ህይወታቸውን አጥተዋል!
•ከ11 ሺህ በላይ ዜጎች አካላቸው ጎድሏል!
•24 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል!
•ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ብቻ 85 ሺህ እድሜያቸው ከ5 ዐመት በታች የሆኑ ህፃናት በምግብ እጥረት ሞተዋል!
•በርካታ ሚሊዮን ዜጎች ቤታቸውን ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል!

ብልቂሳ አብደላ ከ20 ዓመታት በላይ በየመን ነዋሪ ናት ይህንን ብላለች፦ "ወላሂ! የጦርነት ጥሩ ነገር የለም፤ የመንን ያየ... ሰላም የሆነውን ሀገር ባያደፈርሱ ጥሩ ነው። ...ኢትዮጵያ ችግር አለ ሲባል የመንን፣ ሶሪያን፣ ኢራቅን አላዩም ወይ...የመን እንኳን አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት ነው፤ ይሄ ደግሞ የተለያየ ስላለ ከጀመረ የሚያቆም አይመስለኝም"

የመን ለምን እንዲሆነች??
•አለመደማመጥ
•ምክንያታዊ ሆኖ አለማሰብ

#የመናውያን መነጋገርና መደራደር የሚለውን #አማራጭ ባለመተግበራቸው ለዚህ ችግር ተጋልጠዋል። ጦርነት ሩቅ አይደለም፤ በፖለቲካና በሃይማኖት መካረሩ መዳረሻው ግልፅ ነው👉ጦ ር ነ ት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

Via #SRTA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የአለታ ወንዶ የመረዳጅ #ዕድር አባላት በአለታ ወንዶ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ800 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

Via #SRTA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
ሚዛን አማን⬆️

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ከቤንች ሸኮ እና ከምእራብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ጋር ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ በዚህ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ላይ የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በዞኑ ያሉ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ📸ይሄ ደግሞ ሀዋሳ መግቢያ #ቶጋ አካባቢ የደረሰ የመኪና አደጋ ነው። በአደጋ ስለደረሰው ጉዳት ወደበኃላ መረጃዎችን ሰብስበን እናሳውቃለን። @tsegabwolde @tikvahethiopia
የሁለት ሰው ህይወት አልፏል!

ከቢሻንጉራቻ ከፍ ብሎ ልዩ ቦታ ውሻሎ ምርጥ ዘር አካባቢ በዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ8 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን በምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ጉሳ ዴኮ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-03954 አይሱዙ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ ሲመጣ ባልታወቀ ምክንያት የቀኙን መስመር ለቆ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣው ኮድ 3-0739 በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ በሚጠራው ሚኒ ባስ መኪና ጋር ተጋጭተው ዶልፊን ሚኒ ባስ መኪና ውስጥ ከነበሩት ሰዎች አስሩ ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በዚህም ለህክምና አቅራቢያ ወደሚገኘው ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደው እየተረዱ የሚገኙ ሲሆን በአደጋው የ2 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ ቀሪዎቹ 6 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ጊዜው ክረምት በመሆኑም አሽከርካሪዎች ሲያሽከረክሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የፍጥነታቸውን ወሰን እንዲጠብቁ ኢንስፔክተሩ አሳስበዋል፡፡

Via #SRTA
ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪን ለመቆጣጠር እንዲቻል መመሪያ ተዘጋጀ!

በግል ትምህርት ቤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተደረገ ያለውን የተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪን ለመቆጣጠር እንዲቻል መመሪያ መዘጋጀቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የመማር ማስተማር እና ምዘና ዘርፍ ኃለፊው አቶ ተሰማ ዲማ ለደ.ሬ.ቴ.ድ እንዳስታወቁት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በተለይም በከተሞች የግል ትምህርት ቤቶች በየጊዜው ምክንያታዊ ያልሆነ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ቢሮው ጥቆማ ይደርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶችን የመማር ማስተማር ሥራ የሚከታተልበት አሠራር ያለው ቢሆንም ክፍያን በተመለከተ መቁረጥ ስለማይችል ትምህርት ቤቶቹ ሊመሩበት የሚገባውን መመሪያ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ቢሮው ከግል ትምህርት ቤቶች ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የትምህርት ቤት ክፍያ ላይ ጭማሪ ከማድረጋቸው አስቀድሞ በዓመቱ ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ባሉት ወራት ከተማሪ ወላጆች ጋር በጥልቀት በመነጋገርና ምክንያቶችን ዘርዝረው የማስቀመጥ ኃላፊነት እንዳለባቸውም በመመሪያው ላይ በግልጽ መቀመጡን አብራርተዋል፡፡

የተማሪ ወላጆችና ማህበረሰቡ ያላመነባቸው የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ በአሠራሩ መሠረት ተቀባይነት እንደሌለው አውቆ በየአካባቢውና ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው ቦታዎች ህዝቡ መብቱን እንዲያስከብርም አቶ ተሰማ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግና ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያላትን ማንኛውንም ጥያቄ በውይይት በአጭር ጊዜ ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው ትላንት በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ በተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፦

•የመስቀል በዓል የፍቅርና የይቅርታ በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።

•በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስና እንዳይደናቀፍ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን የበኩላቸውን ድጋፍና አስተጽፆ እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

•ሀዋሳ ከተማ ቀድሞ የምትታወቅበት የፍቅር፣ የሰላምና የመቻቻል ከተማነቷን ዳግም እንዳገኘች አንስተዋል።

•ከተማዋ አሁን ላለችበት ሁኔት የህዝቡና ነዋሪዎች ጥረት እንደሆነ አንስተው በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ስራዎችም ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል።

•ከተማዋ አሁን ባለችበት እንድትቀጥልም ከነዋሪዎችና ከመላው ህዝብ ጋር የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

•ምክትል ከንቲባው አዲሱ ዓመትና የመስቀል በዓል የሰላም፣ የልማት የብልጽግና እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#SRTA
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvagethipia
#ጊፋታ2012

የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ ላለፉት ሳምንታት በደመቀ መልኩ በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ዛሬም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ አመራሮችና የብሄሩ ተወካዮች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia