TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#KFO

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» ወደ 70 የሚሆኑ አባሎቼ በኦሮምያ ክልል ታስረዉብኛል ሲል ገለፀ። ፓርቲዉ ይፋ እንዳደረገዉ ጽ/ፈት ቤት መዝጋትና ስብሰባና እንዳናካሂድ ማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋዉረን እንዳንሰራ መከልከል የመሳሰሉ ችግሮች ፓርቲዉ እየተጋፈጠዉ ያለዉ ኩነት ነዉ ብሎአል።

#DW
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#KFO #OFC #ADAMA

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] በአዳማ ሊያደርግ የነበረው ህዝባዊ ውይይት በፀጥታ ኃይሎች መከልከሉን የአዳማ ቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።

ውይይቱ ለምን? በማን? ሊከለከል እንደቻለ ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ቤተሰቦቻችን ተናገረዋል። ውይይቱ ለመካፈል መጥተው የነበሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውም ተገልጾልናል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KFO #AWADAY #OFC

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ላይ ተፈጽሟል ያለውን ኢ ሰብዓዊ ድርጊት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አጣርቶ ውሳኔ እንዲያስተላልፍበት ኦፌኮ ጠይቋል።

የኦፌኮ ለፓርላማው በጻፈው የአቤቱታ ደብዳቤው የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ለማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውና ዜጎች እየተቀባበሉ ስለተመለከቱት በአወዳይ ከተማ ማህበረሰብ ላይ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ሲፈጽሙት የሚታየውን ጭካኔ የተሞላበት ደብደባና ግድያ ጉዳይ እንዲጣራ ነው የጠየቀው፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው የድምጽ ምስል መረጃ በቀላሉ የምንመለከተው አይደለም ያለው ኦፌኮ ድርጊቱም እጅግ አሳዝኖኛል ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ሐምሌ 30/2008 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የፀጥታ ሀይሎች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲፈጽሙ ከሚታየው ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን የጠቀሰው ኦፌኮ ም/ቤቱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡

በአወዳይ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትም ፓርላማ አስቸኳይ ምርመራ አድርጎ እንዲወያይበትና ውሳኔ እንዲሰጥበት ኦፌኮ ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia