TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኡቡንቱ - 'እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን'

ቲክቫህ ቤተሰቦች - አርባ ምንጭ❤️

ኡቡንቱ - እኛ አንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሆናችን ላይ የተመሠረተ የአፍሪካ ጥንታዊ ፍልስፍና ነው። እኛ ወንድምና እህት ነን። እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው የሚበላው ሲያጣ ሁሉም ሰዎች በዚህ ረሃብ ይሰቃያሉ። አንዱ ሲበደል ሁላችንም ህመሙን ይሰማናል፡፡ አንድ ልጅ በሚሰቃይበት ጊዜ እንባዎች በሁሉም ሰው ጉንጮዎች ላይ ይፈስሳሉ፡፡ የእኛን ተቀዳሚ ሰብአዊነት በመገንዘብ፣ እኛን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ትስስር፣ የሰው ልጆችን በሙሉ የሚያስተሳስር የማይጠፋ ቦንድ ነው።

#Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ #Day2

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ጋሞዞን #ፒስሞዴል

(AFRIKHPRI FOUNDATION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day2 #Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፦ የሃሳቡ ደጋፊዎች፣ ተካፋዮች ፣ አስተባባሪዎች የሆኑ እጅግ የምናከብራቸው የሀገራችን ወጣቶች በተለያዩ የከተማው ክፍሎች በመዘዋወር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ብሮሸሮችን በመበተንና ስለ ዓላማው በማስረዳት ስራቸውን ሲሰሩ ውለዋል። ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

ነገ የ3ኛው ቀን ስራ ይቀጥላል!

ሃሳብ፣ መልዕክት የላችሁ፣ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ልታግዙን የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት ካላችሁ እነዚህ አድራሻዎች ተጠቀሙ፦ @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde 0919743630

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል