TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD #ItsMyDam #ItsOurDam

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲሆን ማንኛውም ነገር የኢትዮጵያን ፍላጎትና ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ ብቻ እንደሚከናወንና ብሄራዊ ጥቅም የሚነካ ድርድር የኢትዮጵያ መንግስት እንደማያደርግ ገልጿዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD #ItsMyDam #ItsOurDam

"የህዳሴ ግድብ በአባይ ውሃ መጠን ላይ ተጽዕኖ እስካላመጣ ድረስ ሱዳን ግድቡን ትደግፋለች" - አብደል ቢላል አብደልሰላም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአባይ ውሃ መጠን ላይ ተጽዕኖ እስካላመጣ ድረስ ሱዳን ግድቡን እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም ተናገሩ።

አምባሳደሩ በግድቡ ላይ በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ሱዳን ለግብጽ ወግናለች በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጨውን ወሬ አጣጥለውታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD #ItsMyDam #ItsOurDam

በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም ለኢዜአ የተናገሩት፦

በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሱዳን ለግብጽ እንደወገነች ተደርጎ እየተስተጋባ ይገኛል። የሚሰራጨው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው። የዚህ መሰረተ ቢስ መረጃ ምንጮችም መቀመጫቸውን ግብጽ ካደረጉ የማህበራዊና መደበኛ መገናኛ ብዙሃን የሚመነጭ ነው።

ሱዳን ባላት እውነተኛ ፍላጎት ለግድቡ ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረግ ከኢትዮጵያም ጋር በትብብር ሰርታለች፤ የሱዳን ድጋፍ ባይታከልበት ኖሮ ፕሮጀክቱ እዚህ አይደርስም።

ሱዳን ከቴክኒካል የውሃ ግድብ አሞላል ጉዳዮች ይልቅ በአባይ ወንዝ ዙሪያ የጋራ ትብብር ሁልጊዜም አስፈላጊ መሆኑን ታምናለች። ሀገራችን የታላቁ ህዳሴ ግድብ በውሃ መጠን ላይ ጉዳት የለውም የሚል እምነት ነው የያዘችው።

ጥቃቅን ልዩነቶች ይፈታሉ የሚል ተስፋ አለኝ። አገሮቹ በጉዳዩ ላይ ረጅም ርቀት የተጓዙ በመሆኑ ያን ያህል ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል እምነት የለኝም። በህዳሴው ግድብ ላይ በተደረጉ ድርድሮች የተለያዩ ከበድ ያሉ ጉዳዮች በመታለፋቸው ቀሪ ጉዳዮች ከዚህ ግባ የማይባሉ ናቸው።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #GERD #ItsOurDam

የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ፦

"አባይን መገደብም ይሁን በምትፈልገው መልኩ መጠቀሙ ሉአላዊት የሆነቸዋ ኢትዮጵያ ምርጫ ነው። የኢትዮጵያ ምርጫ የሌሎች የአባይ ተፋሰስ አገራትን ፍላጎት በእጅጉ እስካልተጻረረ ድረስ በግብጽ እጅ ጥምዘዛ አባይን እንዳትጠቀም የሚደረገው ሴራ በአንዲትን ሉአላዊት አገር ላይ የሚደረግ ድንበር ዘለል ጥቃት ተደርጎ ሊቆጠር ይገባል።"

More https://telegra.ph/GERD-02-29-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurdam #GERD

"እኔ እናት ነኝ ለልጄ የተሻለች አገር እፈልጋለሁ! ሰላም እፈልጋለሁ! ለዚህም ካለኝ ላይ ለህዳሴው የምችለውን አድርጌያለሁ። ተማሪ ሆኜ የ3 ወር ቁርሴን፣ ሠራተኛም ሆኜ የ3 ወር ደሞዜን ሰጥቻለሁ። በህዳሴው የመጣ በአይኔ መጣ! ወገኖቼ እኛ እርስ በእርስ ሰንባላ ለጠላት ደስታ ነው፡፡ ሁሉንም ትተን አንድ ሆነን ስለ ህዳሴው እንቁም! የአድዋን ድል ማክበር ብቻ ሳይሆን አድዋን እንድገም መባላት ትተን ለሠላም ለብልፅግና እናብር ያኔ ጠላትም ይፈራናል።" - #GenetHailu

#ItsMyDam #ItsMyBlood
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

"የኅዳሴ ግድብ ድርድር ከምርጫ በኋላ ይከናወን" - አቶ ጃዋር መሀመድ

ምርጫ 2012 እስከሚካሄድ ድረስ ኢትዮጵያ ከኀዳሴ ግድቡ ድርድር እንድትወጣ ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሀመድ ጥሪ አቀረቡ። ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫውንና በቅርቡ በአበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ ቃል የተገባውን ብድር በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላይ ጫና ለማሳደር እየተጠቀመችበት ነው ብለዋል ፖለቲከኛው።

በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንዳትሳተፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ መወሰናቸው ትክክል ነበር ያሉት ፖለቲከኛው ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአቋማቸው ሊፀኑ ይገባል ብለዋል።

ግብፅና ሱዳን አስቸጋሪ የአገር ውስጥ ጉዳይ በገጠማቸው ወቅት ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ጃዋር መሃመድ፤ ኢትዮጵያ ያሉባትን አንገብጋቢ የአገር ውስጥ ጉዳዮች (ምርጫው 2012ን ጨምሮ) እስከምታጠናቅቅ ድርድሩ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም ይገባል ብለዋል። መንግሥት የድርድሩን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ኀብረት በመውሰድ የአባል አገራቱን ድጋፍ እንዲሰበስብም አቶ ጃዋር መሃመድ መክረዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን የተመለከተ ሰነድ አዘጋጅቶ ለድርድር እንደሚያቀርብ ሪፖርተር ጋዜጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለፁልኝ ብሎ ዘግባል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ አመቻችነት የግድቡን የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ የቆየው ድርድር ውጤት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ጥቅም የሚያስከብር የድርድር ሰነድ እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ሰነዱን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከተደራዳሪ ቡድኑ በተጨማሪ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዓለም አቀፍ ሕግ ስምምነት ባለሙያዎች፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ሰነዱን በማዘጋጀት ሒደት ላይ ሌት ተቀን እየሠሩ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል።

More https://telegra.ph/reporter-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/NAMA-03-01

ኢዜማ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/EZEMA-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት በተከበረው 124ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፦

"ሰሞኑን የህዳሴው ግድብ አስመልክቶ የቀረበው የውል ሰነድ ቆምብለን ከውጫሌው ውል በመማር በውሉ የሰፈሩ ሓሳቦችና ቃላቶች፣ በሉኣላዊነታችን ላይ የመጡ ከዛም አልፎ ለሌላ ጂኦፖለቲካዊ ዓላማ ማስፈፀሚያ ገፀ በረከትና እጅ መንሻ ሆኖ እንዳያገለግል በከፍተኛ ጥንቃቄና ሓላፊነት መፈፀም ይገባል።”

#TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ [ኢሕአፓ] በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ከመንግስት ጋር እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል። የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ ከላይ አንብቡ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia