TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

የህዝቡን #ደህንነት እና #ሰላም ለመጠበቅ ሲል መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትእግስት #ገደብ እንዳለው በመግለፅ #ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት #ሁከቶች #በሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ስም የተቀነባበሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት በቡራዩና አካባቢው ብዛት ያላቸው ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመጠቆም፥ በተለያዩ ቦታዎች ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችን የማሰባሰብ ስራ መሰራቱንም ነው ያስታወቁት።

በአጠቃላይም በቡራዩ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ #ገንዘብ ተከፍሏቸው ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እንዲሁም ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስድቦችንም ጭምር በማሰራጨት #የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም አንስተዋል።

ይህ ድርጊት #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባና በአርባ ምንጭ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነሩ በቡራዩና አካባቢው የተፈፀመውን ግድያ ለማውገዝ በርካታ ሰላማዊ ሰው መውጣቱን ጠቅሰው #የተወሰኑ ቡድኖች ግን አዝሚሚያቸው ሌላ ነበር ብለዋል።

ከእነዚህ የተወሰኑ ግለሰቦች መካከልም #ቦምብ ይዘው የነበሩ በህብረተሰቡ ትብብር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፒያሳና በመርካቶ #ለዝርፊያ የሚቃጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ነው የጠቀሱት።

የተወሰኑት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ ጠብመንጃ ለመንጠቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር #ግብግብ ገጥመው ነበር ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግርግር ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ #እንዳይሳካ #ታስቦበት የተከናወነ መሆኑን ነው ያነሱት።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ያለውን የገቢና ወጪ ንግድ #ለመቆጣጠር የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ነዳጅን ጨምሮ በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ #ገደብ እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዲኦ

በጌዲኦ ዞን #ገደብ እና #ጎቲቲ ወረዳዎች በርካታ ተፈናቃዮች ያለ ምግብ እና ህክምና #እርዳታ በስቃይ አሉ። በህክምና እጦት 15 ህጻናት #የአይናቸውን_ብርሃን አተዋል። አብዛኞቹ በመጠለያ እና በምግብ እጦት #በመሰቃየት ላይ ናቸዉ። የተራድኦ ድርጅቶች እርዳታ ማቅረብ #አልቻልንም ብለዋል። ወቅቱ የዝናብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቸግሩን የከፋ አድርጎታል።

Via Bisrat Melese
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር አብይ🚁ጌዴኦ-ገደብ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጌዲኦ ዞን #ገደብ ወረዳ ተገኝተው ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስፔን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዘገበ!

ባለፉት 24 ሰዓት በስፔን 87 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። በሀገሪቱ የእንቅስቃሴ #ገደብ ከተጣለበት ቀን ጀምሮ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቻይና የተገኙት 57 የኮቪድ-19 ታማሚዎች...

በቻይና 57 አዲስ በኮሮና ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። ይህም ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ወዲህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር መሆኑን #BBC አስነብቧል።

የቻይና ብሔራዊ ጤና ኮሚሽን 38ቱ ከማህበረሰቡ ውስጥ የተገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሰላሳ ስድስቱ (36) በቤጂንግ የተገኙ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ከትናንት አንስቶ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ አዳዲስ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎም በአንዳንድ አካባቢዎች ከቤት ያለመውጣት #ገደብ እንደገና ተጥሏል፡፡

አብዛኞቹ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙት 'ከገበያ ቦታዎች' ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በዚህም በአቅራቢያው ያሉ አስራ አንድ (11) የመኖሪያ መንደሮች እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡ ነዋሪዎቹ መውጣት የሚፈቀድላቸው መሰረታዊ ግዥ ለመፈጸም ብቻ ነው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መንግስት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ ያንሳ " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ  እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁን ለቲክቫህ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡ ከሰሞኑን መንግስት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ #ገደብ ከተደረገባቸው አንድ ወር ሊደፍን ነው።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል #ለህዝቡ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም።

ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች የተጣለባቸውን ገደብ በVPN በማለፍ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መግለጫ መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁ አይዘነጋም።

ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ከተፈጠረው ኃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሕግን መሰረት በማድረግ #ሀሳብን_በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ መንግስት ገደብ ሊያደርግ እንደማይገባ ም/ቤቱ እንደሚያምን ማስታወቁን ይታወሳል።

@tikvahethiopia
" ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ጥቅል አገልግሎቱ ላይ የዋጋ ማሻሻያ በማድረግ እንዲሁም ያለተገደበ አማራጭን አካቶ ማቅረቡን ገለፀ።

ድርጅቱ ፤ በቪ.ፒ.ኤን (VPN) አገልግሎቱ ደህንነቱ በተጠበቀ የዳታ አገልግሎት #የድርጅት አገልግሎት ማሳለጥ፣ #ቢሮዎችን እርስበእርስ ማገናኘት እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የድርጅት መረጃ እና መሳሪያዎች በመጠቀም ቢዝነስ ማከናወን የሚያስችል ነው ብሏል።

ደንበኞቹ ፤ አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያቸው የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን መጎብኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ነገር ግን ድርጅቱ የዋጋ ማሻሻያውን በሚመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቹ ያሰራጨው መረጃ በርካቶችን ጋር ያጋባና " VPN ምንድነው ? " ብለው እንዲጠይቁ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ወራትን ካስቆጠረው የማህበራዊ ሚዲያዎች #ገደብ ጋር የሚገናኝ የመሰላቸውም ብዙ ናቸው።

ለመሆኑ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ምንድነው ?

(ኢትዮ ቴሌኮም)

ቪ.ፒኤ.ን (VPN) ማለት የግል እና የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ ቅርንጫፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ነው።

ተቋማቱ የራሳቸውን የግል ኔትወርክ እንዲያደራጁ ያስችላቸዋል፤ መረጃን ለማጋራት እንዲሁም በቅርንጫፎች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓቶችን በመደበኛ ወይም በተንቀሻቃሽ አማራጮች መተግበር ያስችላል።

አገልግሎቱ የሞባይል ኔትዎርክ ሽፋን ተደራሽ በሆነባቸው እና የዳታ አገልግሎትን በሚሰጡ በሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛል።

ኢትዮ-ቴሌኮም የቪፒኤን አገልግሎቶች በሁለት አማራጭ የሚያቀርብ ሲሆን እነዚህም " የሞባይል ብሮድባንድ ቪፒኤን " እና " የፊክስድ ብሮድባንድ ቪፒኤን " ናቸዉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ " ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው። " ያለ ሲሆን " የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትዎርክ ሽፋን ባለባቸው አካባቢዎች ነገርግን ግን መደበኛ ባለገመድ መስመር ተደራሽነት ባሌለባቸው አካባቢዎች ልክ እንደ #ባንክ ያሉ የድርጅት ደንበኞች ቅርንጫፎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማገናኘት የሚረዳ የግል መዳረሻ አውታር ሆኖ እንደ አማራጭ የቀረበ ነው።  " ሲል አስረድቷል

የሞባይል ቪፒኤን / VPN / ጥቅል ዋጋ ማሻሻያ የሚመለከተውም ይሄን ነው ብሏል።

Credit : #EthioTelecom

@tikvahethiopia