TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አንጎለላና ጠራ ወረዳ‼️

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ #ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከመንግሥት ካዝና ከ466 ሺህ ብር በላይ ለግል ለጥቅሟ ያዋለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ጽኑ እሥራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባት።

በሰሜን ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሪት ዘርትሁን ያዘው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ በግለሰቧ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽህፈት ቤት ገንዘብ ያዥ ሆና ስትሰራ የመንግሥትን ገንዘብ ለግል ጥቅሟ ማዋሏ በመረጋገጡ ነው።

ተከሳሿ ወይዘሮ #አበበች_ጽጌ ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ በጽህፈት ቤቱ ስትሰራ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና መንግሥታዊ ሰነድ በመደበቅ የሙስና ወንጀል መፈፀሟ በሰውና በሰነድ ማስረጃ እንደተረጋገጠባትም አስረድተዋል።

ግለሰቧ በአገር አቀፍ ደረጃ በውሃና በአካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት (ዎሽ) ግዢ ከአቅራቢዎች ላይ የተሰበሰበ ሁለት በመቶ ገንዘብ 171ሺህ 417ብር ለግል ጥቅም ማዋሏ ተረጋግጦባታል ነው የተባለው።

እንዲሁም በ56 ደረሰኞች ላይ በበራሪው ትክክለኛዉን የገንዘብ መጠን በመመዝገብና የከፋዮችን ስም በመቀያየር የገቢ መጠኑን በመቀነስ ለመንግሥት መግባት የነበረበት 94ሺህ 90 ብር ሰነድ በማበላለጥ መጠቀሟም ነው የተገለፀው።

በተጨማሪም በራሪ ደረሰኞችን ለከፋይ በትክክል ቆርጣ ከሰጠች በኋላ በሁለተኛና ሦስተኛ ካርኒዎች ላይ አቀናንሳ 181ሺህ 16 ብር ለግል
ጥቅማቸው ማዋላቸው መረጋገጡን ባለሙያዋ ገልጸዋል።

ግለሰቧ ወንጀሉን ከፈጸሟ በኋላ ከአካባቢው በመሰወሯ ፖሊስ ወንጀለኛዋን አድኖ በመያዝ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብም ትዕዛዝ
ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለአምስት ዓመታት ከማንኛውም የእንቅስቃሴ መብቷ እንደታገደችም ተወስኖባታል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia