TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...እንኳን በአገር ውስጥ ያለ ይቅርና በውጭ አገር #በወንጀል የተጠረጠረ ካለ ይዘን እናቀርባለን"~ጄነራል #እንደሻው_ጣሰው
.
.
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እስካሁን ድረስ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦች ቢዘገይም ነፃ እንደማይሆኑ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንደሻው_ጣሰው ሐሙስ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በኮሚሽኑ መሥሪያ ቤት በሰጡት መግለጫ፣ የእስር ትዕዛዝ ለወጣባቸው ግለሰቦች ትዕዛዙን ለማድረስ ሲኬድ ያጋጠሙ ችግሮች እንደነበሩ በመግለጽ፣ በእንደዚህ ዓይነት ወቅት መታኮስ አስፈላጊ ስላልነበር የተለያዩ አማራጮች ላይ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹አንዳንድ ጉዳዮች በመደበኛ የፖሊስ ሥራዎች ብቻ የሚፈቱ አይደሉም፡፡ የተለያዩ ቦታዎች ሔደው #የተደበቁ ሰዎች አሉ፡፡ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው በኋላም የእስር ማዘዣውን ቦታው ድረስ ሄዶ ለመስጠት ሲሞከር ያጋጠሙ #እንቅፋቶች አሉ፡፡ በዚህ ወቅት አትታኮስም፡፡ ሁኔታው አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ በጥሞና እንዲታይ ይደረጋል፡፡ ይኼ #ለሰላም_ሲባል ነው፡፡ ይኼ የሚደረገው አጠቃላይ ነገር እንዳይበላሽና እንዳይደፈርስ ሲባል ነው፡፡ ይኼ ማለት ግን ሄዶ ሄዶ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ሰዎች #ነፃ ይወጣሉ ማለት አይደለም፡፡ እንኳን በአገር ውስጥ ያለ ይቅርና በውጭ አገር በወንጀል የተጠረጠረ ካለ ይዘን እናቀርባለን፤›› ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ይኼንንም ለማስፈጸም ከተለያዩ ክልሎች ጋር አስተዳደራዊ ውይይቶች እንደተደረጉ በማስታወቅ፣ ‹‹ጉዳዮቹ ጊዜ ተሰጥቷቸው የክልል መንግሥታትም የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ይደረጋል፤›› ብለዋል፡፡

ይሁንና በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ይዘው የሚያስረክቡ ክልሎች እንዳሉም ያወሱት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፣ በተቃራኒው የሚደብቅ፣ የሚሸሽግና አካባቢዬ ላይ ተጠርጣሪው የለም ብሎ የሚያብር ሰው መልካም ተሞክሮ እንዳልሆነ፣ ብሎም የተጀመረውን ለውጥ የሚያናጋና የሚያበላሽ እንዲሁም የወንጀል መከላከል ሥራ ላይም ጥላ የሚያጠላ ጉዳይ ስለሆነ #በሚታረምበት መንገድ #ይታረማል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#በወንጀል_ይፈለጋሉ #Wanted

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በፎቶ የሚታዩትን ተጠርጣሪዎች በወንጀል እየፈለጋቸው ይገኛል።

የተጠርጣሪዎቹን አድራሻቸውን የሚያውቅ አልያም በአጋጣሚ የተመለከተ ማንኛውም ገለሰብ በስልክ ቁጥር ፦

👉 0115309139 ዘውትር (በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30)

👉 በ0111119475 / 0111711012 በማንኛውም ሰዓት ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።

ነፃ የስልክ መስመር 861 መጠቀምም ይቻላል።

ግለሰቦቹ በሞጆ፣ አንድ ወርቅ ቤት በመግባት ሲዘርፉ የሚታይ ሲሆን ከመካከላቸው የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሰ ይገኝበታል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወደ ወርቅ ቤቱ በመግባት በሰዓቱ ስራ ላይ የነበረችውን ግለሰብ በማዘናጋት ብዛት ያለው ለሽያጭ የቀረበ ንብረት ዘርፈው ሲወጡ በቤቱ የደህንነት ካሜራ አይን ውስጥ ገብተዋል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፥ ከሀገር ውጭ የሚገኙትን ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌውን ፣ በቅርቡ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንደፈታ የተነገረለት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የሚዲያ ሰዎች እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ የሚዲያ ሰዎችን " ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እንዲሁም #በሽብር_ወንጀል " እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።

ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል እየወሰድኩ ነው ባለው እርምጃ " ፅንፈኛ ናቸው " ላላቸው ኃይሎች የሚዲያ እና ፕሮፖጋንዳ ክንፍ በመሆን እየሰሩ ናቸው ያላቸውን አካላት ነው #በወንጀል እንደሚፈልጋቸው ያሳወቀው።

በውጭ ሀገር ያሉትን ተፈላጊ ግለሰቦች በዐለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት እንዲሁም ከሚኖሩባቸው ሀገር መንግስት የፀጥታ እና ደህንነት ተቋማት ጋር በተመሰረቱ የትብብር ማዕቀፎች ተላልፈው እንዲሰጡ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል የፀጥታ እና ደህንነት  ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል " በህቡዕ አደረጃጀት " ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ አገኘኃቸው ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

ከእነዚህ 47 ግለሰቦች ውስጥ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውጋቸው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ተዳርጋ የተፈታችው መምህርት መስከረም አበራ ይገኙበታል።

ግብረ ኃይሉ የተያዙት ግለሰቦች የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን " ለመግደል፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል " በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ስለደረስኩባቸው ነው ብሏል።

ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
" የፀጥታ አካላት ነን ፤ #በወንጀል_ትፈለጋለህ " በማለት አስፈራርተው ከኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ ገንዘብ የተቀበሉ ግለሰቦች በእስራትና ገንዘብ መቀጣታቸው ተነገረ።

የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾች ፦
1ኛ. ጫላ መገርሳ፣
2ኛ. ለሊሳ በቀለ፣
3ኛ  ዳዊት ጉደታ፣
4ኛ. ዮሃንስ ደረጄ
5ኛ  ብርቱካን ለታ ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በመጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ገፈርሳ ክ/ ከተማ አካባቢ በሚገኝ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ የሆነን የግል ተበዳይን " የፀጥታ አካላት ነን ፣ በወንጀል ትፈለጋለህ " በማለት መንገድ ላይ ያስቆሟቸዋል።

በኃላም ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳይታይ አድርገው በስቲከር ሸፍነው ወደአዘጋጁት የቤት መኪና ውስጥ በማስገባት ወደ መልካ ናኖ ክ/ከ አንፎ ወደ ተባለ አካባቢ ይወስዷቸዋል።

ከዚህም በኋላ የሞተ ሰው ፎቶ ለግል ተበዳዩ በማሳየትና በመሳሪያ በማስፈራራት ግማሽ ሚሊየን ብር እንዲያመጣና እንደሚለቁት ይገልጻሉ።

ገንዘቡን ካልከፈለ ደግሞ " ወደ ጦር ኃይሎች እንወስድኃለን " በማለት ገንዘብ እንዲከፍል ያስፈራሩታል።

ይህን ተከትሎ የግል ተበዳዩ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ 100 ሺህ እንዳለው ይገልጽላቸዋል።

በዚህም ጊዜ 1ኛ ተከሳሽ ባለቤቱ በሆነችው በ5ኛ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ የግል ተበዳዩ 100 ሺህ ብር እንዲያዘዋውር ያደረገና ቀሪውን 400 ሺህ ብር እንዲያመጣ በማስጠንቀቅ ይለቁታል።

በህገወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ደግሞ 5ኛ ተከሳሽ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ምንጩን ለመደበቅ በማሰብ በተለያዩ መጠኖች ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅም እንዳዋሉት የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ያሉትን የሰው ምስክሮች ፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል።

ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ስላልቻሉ ፍ/ቤቱ  የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

በዚህም ፦
1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፤

ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ

5ኛ ተከሳሽ በ1 ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ቢ ሲ (ታሪክ አዱኛ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia