TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ገበታ ለሸገር ከዶክተር አብይ ጋር...!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ለአዲስ አበባ ወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት አዘጋጁ።

ለእራት ምሽት ዲፕሎማቶች፣ የኩባንያ ስራ አስኪያጆች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እና ሎሎች አካላት እንዲሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።

የእራት ምሽቱ ለሸገር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር በሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱ ነው የተነገረው።

ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ጥሪም አዲስ አበባን #ንፁህና #አረንጓዴ ለማድረግ ተሳትፏችሁ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ያስችላል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፋችሁ ይህን ታላቅ አላማ #ስኬታማ በማድረግ የመዲናዋን ነዋሪዎች አኗኗር ለመቀየር ወሳኝ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

በአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ የምታደርጉት ተሳትፎ ለቀጣይ ትውልድ ውብ ከተማን ለማስተላፍ በዋጋ የማይተመን ነው በማለት ገልፀዋል። በዚህ የእራት ምሽት አንድ እራትን 5 ሚሊየን ብር #ለመሸጥ ዋጋ ተቆርጦለታል።

የአዲስ አበባን ዋና ዋና ወንዞች ተፋሰስ #ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት እና ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
የ ' ሰላም ስምምነቱ ' #ስኬታማ እንዲሆን ምን ይደረግ ?

የፕሪቶሪያው የ "ሰላም ስምምነት" ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦች በአግባቡ መሬት ይዘው፤ ሲፈጸሙና የጦርነቱ ሰለባ የሆነው ሕዝብ እፎይታን ሲያገኝ እና ሲታከም ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በላከል መግለጫ አሳውቋል።

ም/ ቤቱ የሰላም ስምምነቱ ፍሬያማ ይሆን ዘንድ ፦

- የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሓት በስምምነቱ ማእቀፍ ሊተገብሩ በተስማሙት ሠነድ መሠረት ፦ የአፈጻጸም ሂደቱ አካታች ፣ ተዓማኒ እና ግልጽ ሆኖ በታመለት ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንዲቻል በፍጹም ቁርጠኛነት እንዲሁም በተጠያቂነት መንፈስ እንዲያከናውኑ በአጽንዖት ጠይቋል።

- የፓለቲካ ኃይሎች ስምምነቱ ፍሬ እንዲያፈራና በሀገራችን ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲኖር የሰላም ደጋፊ ሊሆኑ ይገባል ብሏል። የእልህ እና የብሽሽቅ ፕሮፖጋንዳዎች ቆመው የአሸናፊነትና ተሸናፊነት ኋላቀር አስተሳሰብ ሊወገዝ እንደሚገባው ገልጾ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን #በይቅርታ ሕመማችንን በጋራ እንድናክም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

- የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት እጅግ በጣም ውጤታማ ይሆን ዘንድ በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብሏል ፤ ለዚህም ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርቧል።

- በተደረገው የሰላም ስምምነት ስኬታማነት ላይ ስጋት ያላቸው ዜጎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ አክቲቪስቶች ፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎችም ኢትዮጵያ ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በማወቅ ስለሰላም መልካሙን እንዲያስቡና እንዲያደርጉ አሳስቧል።

(ሙሉ የም/ቤቱ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia