TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . " ማዳበሪያ በወቅቱ ስላልቀረበልን የዘር ስራችን እየተደናቀፈብን ነው " - በደብረ ብረሀን ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች " የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር  ከአቅሜ በላይ ነው " - የደብረብርሃን ከተማ ግብርና መምሪያ በደብረብርሃን ከተማ ዙሪያ በጫጫ ክፍለ ከተማ የጨፋንን ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ካሳየ ሄየ ፦ " በበጋ መስኖ ስንዴ ስናለማ መንግስት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያና…
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምን አለ ?

በአማራ ክልል በ2015/16 የመኸር የእርሻ ዘመን 5 ሚሊዮን ሔክታር ማሣ በዘር በመሸፈን 160 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የትግበራ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ነገር ግን የማዳበሪያ አቅርቦት እንዲሁም ስርጭቱ በሚፈለገው ፍላጎትና ቢሮው በአስቀመጠው የዕቅድ መጠን ልክ እንዳልሆነ አልሸሸገም።

ይህም ካለው የሀገሪቱ አጠቃላይ ወቅታዊ ችግርና ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ የሚመረት እና እንደ ምርጥ ዘር በራሳችን የሚቀርብ አለመሆኑን ሁሉም መገንዘብ ይኖርበታል ብሏል።

ቢሮው  ፤ " ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅርበትና በቅንጅት በመስራት ማንኛውንም የሚቻለንን ሁሉ እየሠራን ነው "  ሲል ገልጾ " ችግሩን ይበልጥ #ማጯጯህ ሳይሆን ይህም ችግር እንደማንኛውም ችግር የሚያጋጥምና ችግሩን መወጣትም አንዱ የትግል አካል በመሆኑ በመተባበርና በመቀናጀት መስራት ይገባል " ብሏል።

ቢሮው ፦

1ኛ. ቀድሞ የገባን ማዳበሪያ ቀድመው ለሚዘሩ ሰብልና አካባቢዎች በመተሳሰብ ማሰራጨት፤

2ኛ. ማንኛውም የሚቀርቡ ግብአቶች ከብልሹ አሰራርና ህገወጥ ድርጊት መከላከል፤

3ኛ. የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፓስት፣ ቨርሚ ኮምፓስትና ሌሎችንም ቢሮው ሲከታተለው የከረመ በመሆኑ በዞኖች በሪፓርት የተላከውን ኮምፓስት መጠቀም መቻል፤

4ኛ. የመረጃ ቅብብሎሽ በትክክለኛና በተመጠነ አኳኃንና እንዲሁም የአርሶአደሩን ሞራልና ስሜት የሚያበረታታና የሚያጠነክር መሆን አለበት ብሏል።

ቢሮው በአሁኑ ሰዓት በክልሉ በሁሉም የሰብል አይነትና መጠን የምርጥ ዘር ችግር በአንጻራዊነት ችግር እንደሌለ ገልጿል።

ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አማራ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሠረት አማራ ክልል በነዚህ በተዘረዘሩት ሰብሎች የሚከተለውን " #ሀገራዊ_ድርሻ " የያዘ ክልል ነው።

- ጤፍ  👉 40% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ሰሊጥ 👉 80% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ስንዴ 👉 32% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- አኩሪአተር 👉 85% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ሩዝ 👉 63% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- በርበሬ 👉 45% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- እጣንና ሙጫ 👉 60% የማምረት ድርሻ አለው።

መረጃው ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia