TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.8K photos
1.57K videos
216 files
4.29K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል። " ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር…
#MoE

በወጥነት ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምግብ ሜኑ ምን ይመስላል ?

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑም ሁሉም ጋር ወጥ እንዲሆንብ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ፤ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል።

የምግብ ሜኑው ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል እንዳለባቸው ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ለዩኒቨርሲቲዎች በተላከው የምግብ ሜኑ ከላይ የተያያዘ ሲሆን ፦

👉 ቁርስ ላይ ፦ እንጀራ ፍርፍር / ሩዝ + ዳቦ + በሻይ ፣ ቅንጬ ፣ ስልስ ፣ ማካሮኒ ተካተለዋል።

👉 ምሳ ላይ ፦ ምስር/አተር ክክ/ሽሮ / አተር / ባቄላ / ድንች / አትክልት ማለትም ጎመን ፣ድንች፣ ካሮት የመሳሰሉ / ፓስታ /  + እንጀራ / ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

👉 እራት ላይ ፦ ምስር/ክክ/ፓስታ / ሽሮ + በእንጀራ/ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።


🔵 ለበለጠ መረዳት ከሰኞ እስከ እሁድ የተከፋፈለውን የምግብ ሜኑ ከላይ መመልከት ይቻላል።

አጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በላከው የምግብ ሜኑ መሰረት ለቁርስ ፣ ለምሳ፣ ለእራት ለአንድ ተማሪ የተመደበው 100 ብር ነው።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሽፍን ባለመቻሉ መንግሥት በፊት የነበረውን ዕለታዊ የተማሪ ምግብ ወጪ 22 ብር ወደ 100 ብር ከፍ አድርጎታል።

(በትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#NGAT

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET

ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።

የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

#MoE

Via @tikvahuniversity
#MoE

የመውጫ ምዘና ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12 /2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በክረምት በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ ቆይ የመውጫ ምዘና ለሚጠባበቁ መምህራን የመውጫ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

በዚህም የመውጫ ምዘናው ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን መምህራኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳያድረጉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ምዘናው በየአቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ " በቀጣይ ክልል / ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮዎች በኩል የምናሳውቃችሁ ይሆናል " ብሏል።

#MinistryofEducation

@tikvahethiopia
#MoE

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ምዝገባው እስከ ጥር 14/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ታውቋል።

ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ምዝገባ ማድረግ አይቻልም።

ምዝገባው በ
https://exam.ethernet.edu.et ላይ የሚካሄድ ሲሆን ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል።

የመፈተኛ User Name እንዲሁም Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ማንኛውም አይነት ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በኢሜል
[email protected] በስልክ ቁጥር 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ተብሏል።

Via
@tikvahuniversity
#EthiopianDefenceUniversity

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሳወቁት ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።

#MoE

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ ማስረጃ እንዳትሰጡ " - ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡ በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው…
#MoE

በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ሲከታታሉ ለቆዩ መምህራን የመውጫ ምዘና ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የምዘና ፈተናው መምህራኑ በሚኖሩባቸው አቅራቢያ ባሉ አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደተጠናቀቀ ማለትም ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ማሳሰቡ ይታወቃል።

Via @tikvahuniversity
#MoE

" በዚህ ዓመት 150 ሺህ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይን) ይወስዳሉ " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ባለፈው ዓመት ወደ ተግባር የገባው የኦንላይን ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮም እንደሚቀጥል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት 150 ሺ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይ ) እንዲወስዱ ቅድመ ዝግጅ እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

ይህንን ያሉት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ ነው።

ከዚህ ባለፈ በመድረኩ  " ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥራት ያለው ትምህርት በማግኘት ረገድ እኩል እድል እንዲኖረው ፤ በድሃና ሃብታም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ሥራ መስራት አለብን " ብለዋል።

" ይችን ሀገር መለወጥ የሚቻለው የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር ሲቻል " ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተሻለ የመማር ማስተማር እንዲኖር ማድረግ ላይ መሥራት እንደሚገባና ' በትምህርት ለትውልድ ' የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል የተጀመረው ንቅናቄ ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመምህራንን አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከተመረቁ  ዜጎች ውስጥ ልዩ የማስተማር ሙያ (pedagogy) ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ሙያው እንዲገቡ እንደሚደረግ ይፋ አድርገዋል።

#MoE

@tikvahethiopia
#MoE

" በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።

በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ / እንደ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡን አሳስቧል።

Via
@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያስፈፅሙ አሳሰበ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ * የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ መዘንጋት የለባቸውም " ሲሉ አሳሰቡ።

ሚኒስትሩ ይህን ማሳሰኒያ የሰጡት ዛሬ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

" ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅባቸዋል " ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ፥ ተቋማቱ በአካባቢ ሳይታጠሩ ለተመሠረቱበት ዓላማ መኖር አለባቸውም ብለዋል፡፡

- የሙስና መንሰራፋት፣
- ግብረ-ገብነት ማጣት
- ዕውቀት የመቀያየር ባሕል በምሁራን ዘንድ መቀዛቀዙን አንስተዋል

እነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የዕውቀት ማዕከል እንዳይሆኑ አድርገዋል ብለዋል።

" ሀገራችን በዘርፈ-ብዙ ችግሮች ውስጥ በመሆኗ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት እና የእውነት ማዕከል እንዲሆኑየሪፎርም ሥራ እየተከናወነ ነው " ሲሉም አመልክተዋል።

ተቋማቱ፤ ጥራት ባለው ትምሕርት ትውልድን መቅረጽ እና የማሕበረሰቡን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ ምርምሮችን በማድረግ ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም በአጽንኦት አሳስበዋል።

Credit -
#FMC

@tikvahethiopia
#MoE #NGAT

ትምህርት ሚኒስቴር የሶስተኛውን ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ።

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ
https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያ ሊንክ በኩል እንደሚከናወን አሳውቋል።

ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ
[email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 እና 0911335683 ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚቻልም አመልክቷል።

የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል ይላካል ያለው ሚኒስቴሩ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 እንደሆነና በቴሌብር በኩል ብቻ እንደሚፈጸም ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል። ተፈታኞች በፈተና ወቅት የተሰጣቸውን User Name እና Password፣ እንዲሁም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

#MoE

@tikvahethiopia