TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው " ከሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ያሳለፈው አዲስ አደረጃጀት በጉጂ ዞን በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እንደገጠመው የቲክቫህ አባላት ከየአካባቢው አሳውቀዋል። ትላንት ከዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በቦሬ ማቲ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ተሰምቷል። አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ…
" ሠልፉ ያልተፈቀደ ነበር " - የቦሬ ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት

ትላንት በኦሮሚያ ክልል፣ ጉጂ ዞን ቦሬ ከተማ ከተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ 3 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው መግለፁ ይታወሳል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቦሬ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ትላንት በከተማው ስለደረሰው ጉዳት ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቡሌ ትናንት በከተማው በተካሄደው ሠልፍ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠው " ሠልፉ ያልተፈቀደ " እንደነበር ገልጸዋል።

ኃላፊው ፤ " አንዳንድ የሠልፉ ተሰታፊዎች በተቋማት ላይ #ድንጋይ በመወርወር እና ገበያ በመበተን ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል " ብለዋል።

" የፀጥታ አባላት የጉዳቱ መጠን ሳይሰፋ ለመቆጣጠር ችለዋል " ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Credit : #ዶቼቨለ_ሬድዮ
Photo : Social Media

@tikvahethiopia
#መቐለ

" የተለያዩ በደሎች እየደረሱብን ነው " ያሉ በትግራይ የሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ዛሬ በመቐለ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ከመቐለ ዘግቧል።

ፖሊስ ሰልፉ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል ተብሏል።

የጦር ጉዳተኛ ሰልፈኞቹ ከመቐለ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው " መለስ ካምፓስ የጦር ጉዳተኞች ማእከል " በመነሳት እስከ የትግራይ ክልል አስተዳደር መሥርያ ቤት የተለያዩ መፈክሮች እያሰሙ ነበር የተጓዙት።

ሰልፍ የወጡት በአብዛኛው #ወጣቶች የጦር ጉዳተኞች ፦

- «እየደረሰብን ያለውን አስተዳደራዊ በደል ሕዝብ ይስማልን፣ ይወቅልን»

- «በኛ ስም ከሕዝብ የሚሰበሰብ መዋጮ እኛጋ እየደረሰ አይደለም፤ በተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አጥተናል»

- «በቂ ምግብና ውኃ እንኳን አጥተን የከፋ ሁኔታ ላይ ነን»

- «የታጋዮች ድምፅ ይሰማ»

- «ትኩረት ለጦር ጉዳተኞች»

- «ተክደናል» የሚሉና ሌሎች ብልሹ አሠራሮች የሚያወግዙ መፈክሮችን ያሰሙ እንደነበር ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

ሰልፈኞቹ " ድምፃችንን ለማሰማት ወደ ከተማ እንዳንገባ መቐለ ዩኒቨርስቲ አሪድ ካምፓስ አካባቢ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ጭምር እንድንበተን ሙከራ ተደርጓል "  ሲሉም ተናግረዋል።

ዶቼ ቨለ ሬድዮ ፤ የጦር ጉዳተኞቹ ሰልፍ ከፍተኛ የቁጣ ስሜት ይታይበት ነበር ያለ ሲሆን ሁኔታው በሃይማኖት አባቶች ሸምጋይነት እንዲረጋጋ ተደርጓል ብሏል።

ሰልፈኞቹ የክልሉ አስተዳደር መ/ቤት በሆነው ደጀን ቢሮ በር  ቆይታ የነበራቸው ሲሆን የሕወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከሌሎች ወታደራዊ መሪዎች ጋር በችግሮቻቸው ዙርያ መወያየታቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

#ዶቼቨለ_ሬድዮ

@tikvahethiopia
#Oromia

" የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት።

ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤  የፌዴራሉ መንግሥት ባስተላለፈው መሠረት የልዩ ኃይል አደረጃጀት መዋቅርን በተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች መልሶ የማደራጀቱ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራንም #የአገር_መከላከያ_ሠራዊት መረከቡን ገልጸዋል።

" የልዩ ኃይል አደረጃጀት ቀድሞውኑም ለጊዜያዊ የፀጥታ ችግር ያለ ሕገ መንግስታዊ መርህ ነው " የተመሰረተው የሚሉት ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ለሁሉም ክልሎች በወጥነት ተላልፏል ያሉትን መዋቅሩን በሌላ ፀጥታ ተቋማት የማደራጀቱ ሥራ እየተተገበረ ነው ብለዋል።

" ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት የሚፈርስ የሚለው መልሶ ለመገንባት በሚል መወሰድ አለበት። እንደ ወንጀለኛ ፈርሶ የሚሳደድ አካል የለም። አደረጃጀቱ ስህተት ስለነበረበት በዚህ መደራጀት አለበት የሚል ነው መወሰድ ያለበት። አንድ ሕጋዊ ክፍተት መኖሩ ሲሆን ሌላው የሚገዳደር የተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች በአንድ አገር ውስጥ አያስፈልግም በሚል የፀጥታ ችግሮች በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልሎች መደበኛ ፖሊስ በየደረጃው እንዲሠራ በሁሉም ውይይት ተደርጎበት የተወሰነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔው ሁሉንም ክልሎች የሚመለከት እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነር አራርሳ በተደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነትም አተገባበሩም በአንድ ላይ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ሂደቱን የአገር መከላከያ እንደሚያስፈጽም መወሰኑንም አመልክተዋል።

" የፌዴራል መንግሥት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነው። ከዚያ ውስጥ ኦሮሚያ አንዱ እንደመሆኑ መመሪያውን ተቀብለን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እያደራጀን ነው። ኦሮሚያ አላፈረሰም ለአንዳንድ ክልል ብቻ የተላለፈ ነው ሚለው እውነት አይደለም ብቻ ሳይሆን በሬ ወለደ እንደ ማለት ነው። ይሄ የሚደበቅም ስላልሆነ ምንም የተለየ ማብራሪያ አያሻውም። ንጹሑ ህዝብ ግን እንዳይደናገር ውሳኔው ማንንም የሚመለከት መሆኑን ቢገነዘሙ መልካም ነው። " ብለዋል።

አሁን በክልሉ የሚሰማራ የልዩ ኃይል አደረጃጀት የለም ያሉት ኮሚሽነር አራርሳ በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል መደበኛ ፖሊስ እንደየሚያስፈልገው መስፈርት እየተደራጁ ለስልጠና እየተሰማሩመሆኑንም ተናግረዋል።

" በሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች አልደራጅም ያለ አሊያም በጡረታ መገለልም ያለበት በደንቡ መሰረት የመሸኘቱ ሥራ እየተተገበረ " ነው ብለዋል።

#ዶቼቨለ_ሬድዮ

@tikvahethiopia