TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቱ በፍቃዱ #ለቀቀ

አትሌት ሃይሌ መልቀቂያ ደብዳቤውን ለጠቅላላ ጉባኤ አባላት ማዘጋጀቱን ዛሬ ቦሌ በሚገኘው የራሱ ቢሮ ለስፖርት ጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በደብዳቤው እንዳመለከተውም እስከ ቀጣዩ የምርጫ ወቅት ድረስ ኮሎኔል አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ተክታ እንድትሰራ መወከሉንም ገልጿል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኮሎኔል አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆና ተሾመች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ምሽት ላይ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል። ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአስቸኳይ ስብሰባው ሰሞኑን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት በፈቃዱ ባገለለው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ቦታ በውክልና የፌዴሬሽኑ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉን በፕሬዚዳንትነት ሰይሟል። በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት ለቀሪዎቹ ሁለት ዓመታት የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንት እንደሚያስመርጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አትሌት አልማዝ አያና አጋጥሟት ከነበረው የጤና እክል ሙሉ በሙሉ ማገገሟን ተከትሎ በኮሎኔል አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በመኖሪያ ቤቷ ተገኝቶ እንኳን ለዚህ በቃሽ ብለዋታል። አልማዝ አያና በኦሎምፒክ የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤትና አሸናፊ እንዲሁም በተለያዩ አህጉራዊና አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ሀገሯን በመወከልና በግሏ በድንቅ ብቃት በማሸነፍ የምትታወቅ አትሌት ናት።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደራርቱ_ቱሉ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን

ትናንት ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ጽ/ቤት ልዩ የዕውቅና ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፦

• ፍልቅልቋ ዝምተኛ ጀግና አትሌት ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት የኦሎምፒክ የወርቅ መዳልያ አሸናፊ በመሆኗ ከአፍሪካ ኅብረት ጽ/ቤት ልዩ ሽልማት አበርክቶላታል፡፡ እንዲሁም የዲሲ ከንቲባ ጽ/ቤት በክብር ሠርተፍኬት አበርክቶላታል፤

• ተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ደግሞ በምሽቱ ሦስት ሽልማቶችን ተሽልሟል፡፡ በሙዚቃ ሥራው ለአፍሪካውያን ወጣቶች አርአያ በመሆኑ ከአፍሪካ ኅብረት ልዩ ዋንጫ ሲሸለም፤ የዲሲ ከተማ ከንቲባም የእውቅና ሠርተፍኬት አበርክቶለታል፡፡

የሜሪላንድ ኢትዮጵያውያንም ለቴዲ አፍሮ ልዩ ስጦታ ሰጥተውታል፤ ቴዲ አፍሮ (ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን) ባደረገው ንግግር፤ ሽልማቱን ላበረከቱለት ሁሉ አመስግኖ ሽልማቱን ለአፍሪካውያን ወጣቶች መታሰቢያ እንዲሆን አበርክቷል፤

Via #GETU_TEMSEGEN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደራርቱ_ቱሉ

' አይክፋችሁ እንክሳችኃለን '

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በብሔራዊ ቤተመንግስት የተናግረችው ፦

" ... ቶክዮ እኔ ውጭ ሀገር መኖር ሆነ መጥፋት አስቤው አላውቅም ከመጀመሪያው ጀምሮ የዛሬ ዓመት ግን መጥፋትም አስቤ ነበር፤ በጣምም ከፍቶኝ ነበር።

አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንመጣ እነ ሰለሞን ባረጋ እና ሌሎችም ናችሁ ጥሩ ድጋፍ ያደረጋችሁልን።

ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚወደው 5 ሺ እና 10 ሺህ ውድድር ውጤት አላገኘንም። በእርግጠኝነት የዛሬ ዓመት እና የዛሬ ሁለት እንክሳችኃለን አይክፋችሁ።

እነ ሰለሞንም ሞራላችሁ አይነካ እንወዳችኃለን፤ ወርቆቻችን ናችሁ።

በስፖርቱ ቤተሰብ ፊት ቆሜ ቃል ገባላችኃለሁ የምንወደው እና የምንፈልገው ዘንድሮ ያጣነው ውጤት ይመጣል። ተስፋ አደርጋለሁ እንሰራለን ከሰራን እናመጣዋለን "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ደራርቱ_ቱሉ

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከተናገረችው ፦

" እንደምናውቀው የትግራይ አትሌቶች ቤተሰብ የማግኘት እድል አሁንም አላገኙም ክብርት ፕሬዜዳንታችን በእርግጠኝነት ይሄንን ነገር ይቀርፋሉ ብዬ ገምታለሁ፤ መንግስታችን ይሄን ነገር ይቀርፋል ብለንም እናስባለን።

ምክንያቱም ደስታችን እውን እንዲሆን ለሚቀጥለው በሙሉ ልብ እንድንሰለፍ አትሌቶች አሉን እዛ ፣ ትግራይ አትሌቶች አሉን አልመጡልንም እዛ ባሉበት ስራቸውን እንዲጀምሩ፣ አስፈላጊ አትሌቶች እዚህ እንዲመጡ አስፈላጊውን ነገር ደግሞ መንግስት ለእነዚህ አትሌቶች መንገድ ከፍቶ ፣ መሰረታዊ ነገሮች ብዙ አሉ እሱን መንግስት ያውቀዋል እነዛ ሁሉ ነገሮች እንዲሆኑልን ከጣም እንፈልጋለን መንግስታችንን በትህትና እንጠይቃለን።

በእርግጥ መንግስታችን ፈቅዶ ምናልባትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካልፈቀደ ስለማይሆን በእርግጠኝነት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም ይሄን ከግምት አስገብቶ እነዚህ አትሌቶች ቤተሰባቸውን የሚያገኙበት ሁለቱ መንግስቶች የሚመለከታቸው አካላት ይሄን ያደርጋሉ ብዬ ነው የማስበው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
' 2015 ለኢትዮጵያ የተሻለ እንዲሆን እመኛለሁ '

ኮማንደር አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል ወቅት የተናገረችው ፦

" ዛሬ ያወደስናቸው የትግራይ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው ይሩኑ አይኑሩ ፤ ይብሉ አይብሉ ፣ ይታከሙ አይታከሙ የሚለውን የሚያውቁት ነገር የለም።

ስለዚህ እዚህ ጋር ጥሩ ጎናቸውን ተቀብለን እዛ ጋር ያ ጉድለታቸውን መሙላት ስላለብን እነዚህ አትሌቶች የሚፈለግባቸውን ነገር ሁሉ አድርገዋል መንግስት ደግሞ እንደመንግስት ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመነጋገር የተሻለ ነገር አድርጎ ቤተሰቦቻቸውን እንዲያገኙ ፣ የትግራይ ህዝብም የተሻለ መሰረታዊ ነገር እንደ ስልክ፣ መብራት፣ ባንክ የመሳሰሉትን ነገሮች እንዲያገኝ ቢያደርረግ ደስ ይለናል።

ምክንያቱም እኛ ለእነዚህ አትሌቶች ቅርብ ነው ያለነው። ቅርብ ስትሆን ትሳቀቃለህ ፣ ከአንዱ አንዱን ስታይ ትሳቀቃለህ ሁለተኛውን ፣ ሶስተኛውን ስታይ ትሳቀቃለህ ብዙ ነገር ነው ያለው እዛ በቅርብ ስናይ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው።

እኛም እስከመቼ ነው የምንጨነቅው ከእነዚህ አትሌቶች ጋር ? ስለዚህ እኔስ ብሆን ፣ እናቴስ ብትሆን፣ አባቴስ ቢሆን፣ ወንድሜስ ቢሆን፣ ልጄስ ቢሆን ብለን ማሰብ አለብን የኢትዮጵያ መንግስት ከአፅንኦት ጋር የማሳስበው ይሄን ነገር ያደርጋል ብዬ ገምታለሁ።

እነዚህ አትሌቶች ልዩነታቸውን ጠብቀው ፣በሀገራቸው ጉዳይ ጠንክረው ፣ ጠንክረን ይሄን ውጤት አምጥተናል ያሉንን ልዩነቶች አጥበን መሰረታዊ ነገሮች አሟልተን እዛ ያሉትን አትሌቶች ረድተን እዚህ ያሉትንም አጠንክረን ሞራል ሰጥተን የተሻለ ዓመት 2015ን እንድንቀበል የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትንም የኢትዮጵያ መንግስትንም እጠይቃለሁ። እግዚአብሔር ይርዳን።

2015 ለኢትዮጵያ የተሻለ እንዲሆን እመኛለሁ። ህዝብ ተፈናቀለ፣ ሞተ፣ ተሰደደ፣ ተራበ የሚባለው ነገር ጠፍቶ በአትሌቶቻችን ደስ እንዳለን ሁሉ ኢትዮጵያን ደስ የሚላት ነገር እንዲመጣ ከልቤ ፀልያለሁ፤ ከልቤ እመኛለሁ፤ እኛ ከለመነው እግዚአብሔር ያን ያሳካዋል።

ሁላችንም የጥላቻ ልብ ወደጎን አድርገን የይቅር ባይነት ልብ ካቀረብን ይሆናል። ጥላቻን ባቀረብን ቁጥር ሁለመናችን ወደጥላቻ ይሄዳል፤ ጥላቻን ትተን በጎ ባሰብን ቁጥር ሁሉ ነገር በጎ ይሆናል።

የጥላቻ ልብን እንደምንም አሸንፈነው የይቅር ባይነት ልብ፣ የመረጋጋት ልብ፣ የማስተዋል ልብ ፣ ከጭካኔ የራቀ የርህራሬ ልብ እግዚአብሔር እንዲሰጠን የሁል ጊዜ ፀሎቴ ነው።

ህዝቤ የተሻለ ነገር እንዲያገኝ ከልቤ እመኛለሁ "

@tikvahethiopia