TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መለዋወጫ !

ከዚህ ቀደም ተከፍተው አገልግሎት ላይ የነበሩት የመልዕክት መቀበያዎች በተደጋጋሚ በቴሌግራም ቴክኒንክ ችግር አገልግሎታቸው እየተደነቃቀፈ ነው።

በዚህም ምክንያት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚመጡትን መልዕክቶች ለማግኘት ችግር ሆኗል ፤ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ችግሩን ለመቅረፍ እና በየትኛውም መልኩ ነፃነቱ የተጠበቀ ለቲክቫህ አባላት ብቻ የሚያገለግል የሀሳብ መለዋወጫ በቅርቡ ይፋ የምናደርግ ሲሆን እስከዛው ድረስ ግን በዚህ አዲስ መልዕክት መቀበያ ላይ ብቻ መልዕክት ማጋራት ይቻላል  👉@tikvah_eth_BOT

በተጨማሪ @tikvah_Ethiopia_Fam ወይም ደግሞ 0703313630 መደወል ይቻላል።

በቲክቫህ ቤተሰብ ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻሉ መልዕክቶች ምን አይነት ናቸው ?

- የፀጥታ ችግሮች፣ የደህንነት ስጋቶች፣ የወንጀል ድርጊቶች በመንግስት አካላት / ተቋማት የሚፈፀሙ ማንኛውም አይነት አስተዳዳራዊ በደሎች፤
- የየመንገድ ፣ የውሃ፣ እንዲሁም የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚና የሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎች፤
- በግልም ሆነ በጋር የማያጋጥሙ ችግሮች፣ ሊበረታቱ የሚግባቸው ተግባራት፣
- ለሀገር እና ለትውልድ ጠቃሚ ናቸው የሚባሉ ሃሳቦችን፣
- የእርስ በእርስ እገዛዎች ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣
- ጥቆማዎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ይሄ ነገር ለቤተሰቡ ቢጋራ መልካም ነው የምትሉትን (ዜና ፣ መረጃ) ሁሉ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ምን መላክ አይቻልም ?

ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ፣ የማንኛውም የግለሰብ ማንነትን በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ፣ ህዝብን በጅምላ የሚፈርጅ፣ ፣ ህዝብ ላይ ጥላቻን የሚያሰርፅ፣ ሀገር ሊያስጣ የእርስ በእርስ ግጭት የሚያባብስ፣ ሀሰተኛ መረጃ ፅሁፍ / መልዕክት መላክ በፍፁም አይቻልም። በየትኛውም አካል ላይ ትችትም ይሁን ቅሬታ ለመግለፅ የሚፈልግ የቤተሰቡ አባል የሚጠቀማቸውን ቃላት የመምረጥ ግዴታ አለበት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም መልዕክት ስትልኩ የራሳችሁ የግላችሁ መልዕክት መሆኑን በማስረጃ አስደግፋችሁ ላኩልን። እናተ ያላረጋገጣችሁትንና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስላያችሁት የራሳችሁ በማስመሰል ማንኛውም መልዕልት መላክ ፍፁም አይቻልም።

ማስታወሻ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት #በፌስቡክ#ዩትዩብ#ቲክቶክ ላይ ምንም አይነት የመሰባሰቢያ መድረክ (ገፅ) የላቸውም።

ትዊተር ፦ https://twitter.com/tikvahethiopia?t=jZrpieALuIGzw6OM-HWgEw&s=09

ሀሳባችን ስንገልፅ ቃላትን እንምረጥ !!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ!!
#TikvahFamily

@tikvah_eth_BOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ? የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦ " ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል። ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦ - የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣ - ነጋዴው…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዶ/ር ደሳለኝ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ መሆኗና ለዚህም ተጠያቂው ገዢው ብልፅግና ፓርቲና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወደቀ አመራር በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣናቸውን #እንዲለቁና ስልጣናቸውን ለሚቋቋም ጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፤ ፓርላማውም ተበትኖ ለምርጫ መንገድ እንዲጠርግ በሚል በዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለተጠየቀው ጥያቄ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርቲያቸውና መንግሥታቸው ላይ ከታቃዋሚ ፓርቲ በኩል የቀረበውን ክስ በተመለከተ " እንዲህ ያለው ንግግር ለዛሬ #ፌስቡክ፣ ለዛሬ #ዩትዩብ ጥሩ ነው ፤ አቶ እንትና እንትና እንዲህ አደረጉ ለሚለው ለፌስቡክ ፍጆታ ጥሩ ነው ለትውልድ እና ሀገር ግን አይጠቅምም " ብለዋል።

" ቆም ብለን እኛ ማናየውን በማሳየት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመውን ሃሳብ ብናቀርብ ጠቃሚ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" በኢኮኖሚ፣ በሰላም እና በአንዳንድ ጉዳዮች የቀረቡትን የምንወስዳቸውና የምንሰራባቸው እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም " ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ " በጥቅሉ ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ናት ከተባለ ግን ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት በኢኮኖሚ 3ኛ ናት፣ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት ፣ ትላልቅ ተቋማትን እየገነባች ያለች ሀገርናት የሚል መልስ ሆኖ ያልቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

ምርጫን በተመለከተ ፤ " ምርጫ ይካሄድ የሚለውን ሃሳብ በጣም አደንቃለሁ ፤ ብዙ ጊዜ የተቃዋሚዎች ችግር ምርጫ አይፈልጉም ዝም ብላችሁ ልቀቁና እኛ እንያዝ ነው የሚሉት ፤ አሁን ምርጫ ይደረግ የሚለው በጣም ጠቃሚ ነው ግን ሶስት ዓመት #መታገስ አለብን " ብለዋል።

" በየሳምንቱ ምርጫ ስለማይደረግ ፤ ሶስት አመት ታግሰን ያለንን ሃሳብ ይዘን ቀርበን እኛም ይዘን ቀርበን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈርደውን ፍርድ በፀጋ መቀበል ነው ፤ የዛሬ ሁለት ዓመት የፈረደውን ፍርድ አልተቀበልኩምና አሁን ፓርላማው ፈርሶ ምርጫ ካልተካሄደ አሁንም ፈርሶ ቢካሄድና ቢመረጥ ካልተመረጥን ይቀጥላል ጉዳዩ በየሁለት አመቱ ምርጫ ለማካሄድ አቅም ስለሚያንሰን በተቀመጠው መንገድ በ5 ዓመት እናደርጋለን " ብለዋል።

" ምርጫ ሲደረግ ያሉ ሀሳቦች ለህዝብ ቀርበው እኛ ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ካላገለገልንና ካልጠቀምን ህዝቡ በምርጫው ሲቀጣን እጅ ስመን፣ ባንስምም እጅ ነስተን እናስረክባለን ፤ እስከዛ መታገስ ጥሩ ነው ፤ ፍርዱን ለህዝብ እንተወው " ሲሉ መልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ከገባችበት ቀውስ ጋር በተያያዘ ስልጣናቸውን እንዲለቁ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ህዝብ በመረጣቸው የምክር ቤት አባላት ሲጠየቁ የዛሬው ሁለተኛ ነው።

የምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በመልቀቅ " ላለው ችግር የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት ? " የሚል ጥያቄ አቅርበው የነበረ።

በወቅቱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኃላፊነት መውሰድ ካለብን በጋራ ቢሆን መልካም ስለሆነ " ስልጣን ብንለቅ " ነው የሚባለው ምክንያቱም መንግስት ማለት አስፈፃሚ ብቻ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸው ነበር።

የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ንግግር : https://t.iss.one/tikvahethiopia/79527

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia