TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦነግ/WBO‼️

የ'ኦነግ' የቅበላ ቀነ ገደብ ተጠናቋል!
(*የልዩ ሁነት #አምስት የመጨረሻ ቀናት አሉ)
.
.
ከመንግሥት ጋር በተፈጠረው ያለመግባባት ዳግም በውጊያና የተለያዩ ግጭቶች ላይ የቆየው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የከበረውን የገዳ ሥርዓት መርሖዎችና ሕጎች መሰረት አድርጎ ለቀረበው ጥሪና የሰላም አዋጅ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲደረግለት የቆየው አቀባበል ትላንት ምሽት 12:00 ላይ መጠናቀቁን የእርቀ ሰላሙ የቴክኒክ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል።

በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል እርቀ ሰላም ለማውረድ፤ በኦሮሚያ አባገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች(Haadha Siinqee)፣ በአገር ሽማግሌዎች፣ በምሁራንና ለሰላም መስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ በቆዩ በርካታ ዜጎች እንቅስቃሴ ጥረቱ መልካም ፍሬ አፍርቶ #በጫካ የነበረው ሠራዊት ላላፉት ሦስት ቀናት በኦሮሚያ 12 ዞኖችና 22 ወረዳዎች አቀባበል ሲደረግለት ቆይቷል።

ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአባገዳዎች #የሰላም_አዋጅ ታውጆ የእርቀ ሰላም ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ጥሪው በጎ ምላሽ አግኝቶ ሠራዊቱ መሳርያውን ለአባገዳዎችና ለቴክኒክ ኮሚቴው በማስረከብ ባሕላዊ አቀባበል፣ ባርኮት(Muuda) እና ፍቅራዊ ክብካቤ እየተደረገለት ቆይቷል።

ከነገ ጀምሮም በተዘጋጀለት ካምፕ በመግባት በሰላም ተጠሪዎች፣ በሕግ ባለሙያዎች እና በሌሎች ምሁራን የተለያዩ ስልጠናዎች መውሰድ ይጀምራል። ከሁለት ወር በማይበልጠው በዚህ ቆይታ የሠራዊቱ አባላት እንደየፍላጎታቸው እና ችሎታቸው ስልጠና ወስደው በመስካቸው የሚመደቡ ሲሆን በቆይታቸውም በአባገዳዎች፣ በቴክኒክ ኮሚቴው አባላትና በሰላም ተጠሪዎች አያያዛቸው የሚጎበኝ ይሆናል።

እስካሁን በነበረው ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የቴክኒክ ኮሚቴው የፊታችን እሁድ ተገናኝቶ አጠቃላይ ምክክርና ግምገማ የሚያደርግ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና -- በ'ልዩ ሁነት' በቀነ ገደቡ መግባት ላልቻሉ የሠራዊቱ አባላት ተጨማሪ #አምስት ቀን የተሰጠ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት በየወረዳው የሰላም ክፍሎች በመገኘት #መሳርያቸውን ማስረከብና ወደካምፕ ገብተው ለቀጣይ ሰላማዊ ሕይወታቸው ጠቃሚ የሆኑትን #ስልጠናዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via Gulale Post
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር-የሰላም ዋጋ ስንት ነው?🔝

በዛሬው ዕለት #በባህርዳር ከተማ "የሰላም ዋጋ ስንት ነው?" በሚል የጎዳና ላይ #የሰላም_ጉባኤ ተካሂዷል።

Via NAH(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH ETHIOPIA #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች በነገው ዕለት #አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፦

(StopHateSpeech)

1. አቅለሲያ ሲሳይ
2. የምስራች ጋሻው
3. በረከት ጉዲሳ
4. ቢንያም ይርጋ
5. ዱሬሳ በዳሶ
6. እዩኤል በቀለ
7. እዮብ ተስፋዬ
8. ቤቴል አባይነህ
9. ፍላጎት ጥላሁን
10. ሀያት እንድሪስ
11. አዚዛ እንድሪስ
12. ቤተልሄም ሴታ
13. አዲስወርቅ ተክሊ
14. ጉተማ ብርሃኑ
15. ፉአድ ኑሪ
16. አበበ ከበደ
17. ሲሳይ ታደሰ
18. ይድነቃቸው አዳነ
19. ዳንኤል ጥበቡ
20. ንብረት አበበ
21. ዮርዳኖስ ግርማ
22. ቤተልሄም እንዳልክ
23. ፍሬህይወት ማቴዎስ
24. ቃልኪዳን አክሊሉ
25. ሳሮን ገ/መድን
26. ገመቺስ ፍቃዱ
27. ሙልጌታ አደሩ
28. ምሩፅ ደማሶ
29. ቤተልሄም ቱሉ

ትሩ ላይፍ የኪነጥበብ ክበብ፦

•4 የውዝዋዜ አቅራቢዎች
•2 ገጣሚያን

ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፦

•የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳት(ወጣት ዘገየ)

#አርባምንጭ ተዘጋጁ...

እኛ ኢትዮጵያ ልጆች ነን!
እኛ የአንድነት ልጆች ነን!
ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ!

#StopHateSpeech

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንመጣለን!
#TIKVAH_ETHIOPIA - እኛ ከጥላቻ የነፃን፤ ሰውነትን ያስቀደምን #የፍቅር እና #የሰላም አምባሳደሮች ነን!!

አርባምንጭ...🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደሰላም አምባሳደር ተቋም #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ የTIKVAH-ETH #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች #ምድብ_1

•ጊዜው ጌትነት
•ወንድማገኝ ብርሃኔ
•ቤተልሄም አዱኛ
•ዱሬሳ በዳሶ
•ትግዕሥት ተስፋዬ
•ዮርዳኖስ ግርማ
•ፍሬህይወት ማትያስ
•ቤተልሄም ገ\መድን
•ቤተልሄም ሴታ
•አበባ በቃና
•ራህመት አብዱልቃድር
•ቤተልሄም ቱሉ
•ሀያት እንድርያስ
•ቤተል አባይነህ
•እዮብ ተስፋዬ
•ነብያት ዘውዱ
•እዩኤል በቀለ
•ፍቅርተ ዋለልኝ
•ቢንያም ይርጋ
•ፍላጎት ጥላሁን
•ናርዶስ ዮሃንስ
•ቃልኪዳን አክሊሉ
•ቤተልሄም እንዳልክ
•ገመቺስ ፍቃዱ
•ምሩፅ ደምሴ
•ሙልጌታ አደሩ
•ዳንኤል ተሾመ
•ፍሬዘር ገዛኸኝ
•ጉተማ ብርሃኑ
•ሲሳይ ታደሰ
•በረከት ጉዲሳ
•አቅለሲያ ሲሳይ
•የምስራች

√ 19 ሴት
√ 15 ወንድ

የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች
የሰላም ፎረም ተወካዮች

#WSU #StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምድብ ሁለት!

ወደሰላም አምባሳደር ተቋም #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ የTIKVAH-ETH #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች #ምድብ_2

(AMU)

•አስቻለው ደቻሳ
•ተመስገን አየለ
•መሰረት መኮንን
•ደብረወርቅ ተስፋዬ
•ቤተልሄም ዘመኑ
•ኤልያስ ምስጋና
•ማሃሪ ዳርሰማ
•ሳምራዊት ሀጎስ
•እሌኒ ነጋልኝ
•ታሪኩ ተሾመ
•የምስራች ይቆየኝ
•ጣነሮ ሁሴን
•ሀብታሙ አማረ
•ልኡል ሽመልስ
•ሀብታሙ ይልማ
•ሀብታሙ አጌና
•ቢቂላ መኮንን
•አቤል ተስፋሁን
•አዲሱ ፍስሃ
•ብሩክ አበራ
•ልኡል ዩሴፍ
•ሰለሞን አማረ
•ምስራቅ በዛብህ
•መልካሙ ማትዮስ
•ጌትነት ላይኔ
•ሙላለም እንዳሻው
•ሲሳይ አድኖ
•ዮናታን አልዮ
•አማረ ባሻ
•ተመስገን ኢሳያስ
•ኢማን መሃመድ
•ታምራት ፈረደ
•አዲሱ
•አሜን ላየ
•አዳነ ጌቱ

√ 8 ሴት
√ 29 ወንድ

የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች
የሰላም ፎረም ተወካዮች

#AMU #StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምድብ ሶስት!

ወደሰላም አምባሳደር ተቋም #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ የTIKVAH-ETH #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች #ምድብ_3

•አሸናፊ በቀለ
•መዝገቡ ተስፋዬ
•መሀመድ ሚፍታ
•አበበ በላቸው
•አብዱረዛቅ ኑርሰፋ
•አቤል እርቅ ይሁን
•አዳነ ለገሰ
•ናትናኤል ሰለሞን
•ዳዊት ፍቅሩ
•ፍሬው ጌታቸው
•ተምኪን ኑረዲን
•እሱባለው መረጃ
•ቃለአብ ዘበነ
•ደሳለኝ ንዳ
•እስከዳር ታደሰ
•ዮሴፍ ኃይሉ
•አስቻለው ጌቱ
•ይትባረክ አለባቸው
•ዮሃንስ አበራ
•ታዲዮስ ደጉ
•ብርሀኑ አወቀ
•ናትናኤል መርከቡ
•በእምት ሰሎሞን
•ታምራት በሻዳ
•ኑርሁሴን ከማል
•አላዛር ሲሳይ
•ሀናን በድሩ
•ማህሌት ተፈራ
•መቅደስ መሰለ
•ፌቨን ሻውል
•ሜሮን ረዳይ
•ምኞት ወርቁ
•ሰሚራ ሸረፍ
•ሀያት ሳቢር
•ፎዚያ መካ
•ፊሩዛ ሙሀበድ
•ራሄል በላቸው
•ራሄል ሰው መሆን
•ሲትሬላ ሙሀመድ
•ሰሚራ ሸረፋ
•ፈቲያ አሚን
•ሰሚራ ተሸመ
•ሰሚራ ከድር
•ሰዓዳ ሙሳ
•ግዛት ማሞ

√26 ወንድ
√19 ሴት

#WKU #StopHateSpeech
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH_ETH 🇪🇹 #StopHateSpeech

•ሚያዚያ 23
•ሚያዚያ 25 እና 26

√ረቡዕ - ወሎ ዩኒቨርሲቲ
√አርብ እና ቅዳሜ - መቀለ ዩኒቨርሲቲ

ወደ #ወሎ_ዩኒቨርሲቲ እና #መቀለ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙት፦

√የአርባምንጭ ዩንቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

ከ100 የሚበልጡ #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ይሰባሰባሉ!!

ኑ ኢትዮጵያን #በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዋጋ ጭማሪ...

በአዲስ አበባ ከተማ በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ የከተማው አስተዳደር ጥናት በማድረግ እርምጃ ሊወስድ መዘጋጀቱን ገለፀ። በተለይም በአትክልት ምርቶች ላይ የታየው ጭማሪ አሳሳቢ እንደሆነ በአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የንግድ ቁጥጥርና ክትትል የሥራ ሒደት መሪ ካሳሁን በየነ ገልጸዋል። በአገሪቱ በነበረው #የሰላም_መደፍረስ ምክንያት የአትክልት አቅራቢዎች በበልግ ወቅት በሙሉ አቅማቸው ያለማምረታቸው በክረምት ወቅት የሚያጋጥመውን የምርት እጥረት አባብሶታል ብለዋል። በተለይም መቂ ከተማን ጨምሮ በመስኖ ምርት የከተማዋን የአትክልት አቅርቦት በሚሸፍኑ አካባቢዎች ላይ የተፈጠረው ጫና የተወሰነ የምርት እጥረት አምጥቷል ቢባልም ላለፉት ኹለት ሳምንታት የታየው ጭማሪ ግን ሰው ሰራሽ ሊሆን እንደሚችል ካሳሁን ሥጋታቸውን ገልጸዋል።
.
.
“መንግሥት የገበያ ዋጋን ለማውጣት እና ለማስገደድ ሕጉ አይፈቅድለትም፣ ነገር ግን የሕዝብ ኑሮ ላይ ጫና ለመፍጠር እና ያለአግባብ ለመበልፀግ የሚደረግ አሻጥር ላይ ግን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ጥናታችን አጠናቀናል” አቶ ካሳሁን

Via አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሶሳ የሰላም አየር እየነፈሰ ነው!

አሁን በስራ ምክንያት ያለሁት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ #አሶሳ ነው። ሞቃት የአየር ንብረት የሚስተዋልባት፣ አረንጓዴ፣ እና ቀይ ለም አፈር ያለው መሬት ያላት። አሶሳ ከመጣሁ እነሆ ሶስተኛ ቀኔ አለፈ።

አንዳንድ ጓደኞቼ እንዲሁም ቤተሰቦቼ ጋር ተደዋውዬ በስልክ ሳወራ ከኔ ሁኔታ ይልቅ ስላለሁበት ቦታ #አሶሳ አብዝተው ይጠይቃሉ። ገና ለመምጣት በነበርኩበት ግዜ እራሱ ምነው ወደዛ መሄድህ... ? በሰላም ነው? እያሉ በጥያቄ ያጨናነቁኝ ቁጥራቸው ብዙ ነው። መጠየቃቸውን እንደ መጥፎ ነገር ባልቆጥረውም አንድ ነገር ግን በአእምሮዬ ብቅ እንዲል ሆኗል። እኔ ባለሁበት ሰዐት አሶሳ እጅግ #የተረጋጋች፣ ሰላማዊ እና የዕለተ ቀን እንቅስቃሴዋን የምትከውን ከተማ ነች።

ምናልባት የሰዎች ጥያቄ የመጣው ከጊዜያት በፊት በክልሉ በመተከል፣ ካማሺ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በነበረው አለመረጋጋት እና ግጭት ይመስለኛል። እስካሁን ድረስ ግን ብዙ ሰዎች በክልሉ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ሰላማዊ ሁኔታ ያለ #አይመስላቸውም

ሰላም እና መረጋጋትም የማይመቻቸው እና እንቅልፍ የሚነሳቸው አካላት በየማህበራዊ ሚዲያው በሚፈጥሩት ዉዥንብር ምክንያት እና በማይረቡ ተናፋሽ ወሬዎች ማለቴ ነው እና አሁን በአሶሳ ፍፁም #የሰላም አየር ነው እየነፈሰ ያለው ያለው። እንዲሁ በሌሎች ክልሎችም እንዳጣራሁት ከሆነ በብዛት የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የኢትዮጵያ ሰላም እየተመለሰ ነው። ይመለሳልም። ኢትዮጵያ በሰላም፣ እስከዘላለም ትኑር።

Y ነኝ ቤተሰባችሁ ከአሶሳ!

ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MALALA

"የ2019 #የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ ጠቅላይ ሚኒስተር #AbiyAhmedAli፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቅ እየሰራችሁ ላላችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።" -- ፓኪስታናዊቷ ወጣት ማላላ የሱፍዛይ/የ2014 የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ የ2014 የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

1. ዛሬ ህወሓት የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ሆነው በ4 አቅጣጫ ጥቃት ከፍተዋል ሲል ከሷል። ጥቃቱ ከፍቅያ ገብረ እስከ አደመይቲ፣ ከሰላሞ - ሽራሮ፣ ከጎቦ ፅንዓት ወደ እርዲ ማቲዎስና አዲ አሰር እና አዲ ጎሹ በከባድ መሳሪያ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ብሏል። እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት ሆነ ከኤርትራ በኩል ለዚህ ክስ ቀጥተኛ ምላሽ አልተሰጠም።

2. የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ፦

• ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሏል ብሏል። ህወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰውና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው ብሏል። ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ መውደቁን ገልጿል።

• በሕወሓት ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም ለሰላማዊ  አማራጭ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባቡለበት ሁኔታ ሕወሓትን መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ ስለሆነ ተቀባይነት የላቸውም ብሏል።

• ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገርን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይል በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል ብሏል።

3. የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በሕወሓት ላይ የትኛውንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዛሬ ለአምባሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በሰጡት ማብራሪያ ገልጽዋል። ከሚወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን አሁንም #የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Peace

የአፍሪካ ኅብረት #የሰላም_ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ኦፊሴላዊ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ይኸው በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ የቀረበው ጥሪ እንደሚያሳየው፦

- የውይይት ቦታ 👉 ደቡብ አፍሪካ

- የውይይቱ ቀን 👉 ከፊታችን ጥቅምት 8/2022 ጀምሮ

- የሰላም ውይይቱ የሚመራው 👉 በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ

- የሰላም ሂደቱ ፓናሊስት ሆነው የሚያገለግሉ 👉 የቀድሞ የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ ንጉካ ናቸው።

የአፍሪካ ኅብረት ግብዣውን ለኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እንዲሁም ለህወሓት ነው ያቀረበው።

የአፍሪካ ህብረትን ግብዣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት #መቀበሉን በይፋ አሳውቋል። ነገር ግን የውይይቱን መሪዎች፣ ቀንና ቦታ በዝርዝር አልገለፀም።

መንግስት " የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።

" ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆንና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጥ መቆይቷል " ሲልም አስታውሷል።

" ግጭቱን ለመፍታት ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ ርምጃዎች ለመውሰድ ስንቀሳቀስ ቆያቻለው " ያለው የፌዴራል መንግስት " ይህንኑ አጠናክሬ እቀጥላለሁ " ብሏል። 

እስካሁን ድረስ በህወሓት በኩል ለዚሁ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግር ግብዣ ይፋዊ ምላሽ አልተሰጠም።

NB. ከላይ የተያያዘው በሙሳ ፋኪ የተፈረመው ደብዳቤ ለፌዴራል መንግስት እና ለህወሓት የተላከ መሆኑን ሮይተርስ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች ማረጋገጡ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።

አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11 , 000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6000 እስከ 6500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

" ይህ የሚመጣው ከመኸኒና ከአካባቢው ብቻ ሲሆን አላማጣ ዝግ ነው፣ ጨርጨር ዝግ ነው። መንገድ በምዕራብ አቅጣጫ በሽረ በኩል ዝግ ነው ፤ ወቅቱ ጥቅምት እና ህዳር ቢሆንም በሁሉም አቅጣጫ መስመር ቢከፈት ይቀንሳል።

ሰላሙን ተከትሎ ከመሃል ሀገር ቢመጣ ደግሞ በደንብ ይቀንስ ነበር።

በተለይ ነዳጅ ቢገባ አሁን ውድ የሆነው ትራንስፖርት ይቀንስ ነበር። አንድ ሊትር ነዳጅ በጥቁር ገበያ 350 ብር እየተገዛ ሲሆን ከነዳጅ ማደያ የሚገዛ ነዳጅ ቢኖር ኖሮ በደንብ ይቀንስ ነበር " ብለዋል።

በመቐለ የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

ሰመሃል ኪዳኔ የተባለች የበርበሬ ነጋዴ ደግሞ ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል ይህ የሆነው በሰላሙ ስምምነት ተስፋ በማድረግ ነጋዴው ይቀንሳል ብሎ ስላመነ የያዘውን በቅናሽ እየሸጠ በመሆኑ ነው ብላለች።

" ህዝባችን ተጨቁኗል፣ በጣምም ተርቧል፣ አጥቷል #ሰላም በመሆኑ ተጠቃሚ ነን ፤ በጦርነት ኪሳራ እንጂ ልማት የለም ፤ ድርድርን ተከትሎ ባንክ ቢከፈት የቴሌኮም አገልግሎት ቢጀመር እንዲሁም ነዳጅ እንዲገባ ነው #ተስፋችን " ብላለች።

ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ሩፋኤል የተባሉ ሸማች ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሸቀጦች ዋጋ በጣም ወርዶ ማግኘታቸውን ገልፀዋል። ሙሉ በሙሉ ቀንሷል ባይባልም ለውጦች እየታዩ መሆኑን አመልክተዋል።

ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ዝቅ ማለቱን ገልፀዋል። ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደየጥራቱ)።

ነጭ ጤፍ ከአንድ ወር በፊት 13,000 ብር እንደገዙ አሁን ግን 3,000 ብር ቀንሶ በ10,000 ብር እንደገዙ ገልፀዋል፤ ከዚህም ይቀንሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ሰርገኛ ጤፍ ፣ ቀይ ጤፍ ላይም መቀነስ እንዳሳየ አስረድተዋል።

በሩዝ ፣ በመኮሮኒ ዋጋዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ቅናሽ መመዝገቡን እኚሁ ሸማች ለሬድዮው ተናግረዋል።

#በአስቸኳይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በመክፈት ህዝቡ የመግዛት አቅም እንዲኖረው ቢደረግ ጥሩ መሆኑን የገለፁት ሸማቹ የመሰረታዊ አገልግሎት መከፈት ፣ የንግድ ቀጠናዎች ትራንስፖርት ቢከፈት አሁን ካለው ዋጋም እንዲቀንስና ገበያው  እንደሚረጋጋ ገልፀዋል።

መሀመድ ካህሳይ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮው በሰጡት ቃል ፥ " ሰላምን ምንም የሚወዳደረው ነገር የለም ፤ ጥፋት ጥፋት ነው ሁልጊዜ ሰላም ግን ሰላም ነው ፤ አሁን ሰላም ከተጀመረ ጀምሮ 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

የበለጠ መኪና/ትራንስፖርት ሲከፈት ባንኩ ሲከፈት በጣም ቆንጆ ነገር ይሆናል ።

ባንክ ሳይከፈት ዋጋው እንደዚህ የሆነ ባንክን ጨምሮ መሰረታዊ ነገር ሲከፈት ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል በጣም ደስ ይላል። ስኳርም አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል በጣም ደስ ይላል።

መድሃኒትም ይሁን ጥራጥሬ ከመጣ ሁሉም ነገር ወደቦታው እየተስተካከለ ይመጣል ሱቁም ይሞላል ፣ ትራንስፖርትም 24 ሰዓት የሚሰራ ከሆነ በጣም ቆንጆ ነው።

መንግሥት ቶሎ ብሎ አስተካክሎ ካደረገው በጣም ደስ ይለናል። "

በመቐለ ገበያ ፤ ከሳምንት በፊት 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ የ25 ኪሎግራም መኮሮኒ አሁን 1800 ብር እየተሸጠ ነው። አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል። 1 ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል። ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።

Credit : ጋዜጠኛ ሙልጌታ አፅብሃ (ቪኦኤ ፌድዮ)
የፅሁፍ ዝግጅት ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል። አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦ - ሰርገኛ…
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ የታየው ቅናሽ (በቀዳማይ ወያነ ገበያ) ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11,000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6,000 እስከ 6,500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

- የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

- ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል።

- ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ቀንሷል። 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

- ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደ የጥራቱ)።

- ስኳር አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል።

- 25 ኪሎግራም መኮሮኒ 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 1,800 ብር እየተሸጠ ነው።

- አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል።

- አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል።

(ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።)

@tikvahethiopia
#Tigray

ህወሓት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን #ሁሉን_አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት #ኃላፊነቱን_እንዲወጣ ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይና በህዝቡ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም እንዲያደርግ ፤ ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድዱ ፤ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል #ተጠያቂ እንዲሆን እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ህወሓት " በዛሬው መግለጫው ያነሳቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- በተፈረመው #የሰላም_ስምምነት መሰረት ጦርነት እንዲቆም ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እንዲከበር፣ የኤርትራና ሌሎችም ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ህወሓት ፤ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በሰላም ስምምነቱ #እንዳልተደሰቱ ገልጾ ፤ " ወታደሮቹን ያስወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተጨማሪ ክፍሎችን (ኃይሎቹ) ወደ ትግራይ እያመጣ ነው " ብሏል። ይኸው ጦር በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል ሲል ገልጿል።

- የኤርትራ ጦር በሴቶቻችን ላይ ጾታን መሰረት ያደረገ እጅግ አረመኔያዊ ጥቃት እየፈፀመ ፤ ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ፣ የህዝብና የግል ንብረት እየዘረፈ ወደ ኤርትራ እያጓጓዘ ፤ የተረፈውን ደግሞ #እያጠፋ እና እያቃጠለ ነው ፤ የትግራይ ቅርሶችም በከፍተኛ ደረጃ እየወደሙና እየተዘረፉ ነው ፤ በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ) የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

- ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ እና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል #በአስቸኳይ_እንዲያስቆም ፤ ከትግራይ እንዲወጣም እንዲያስገድደው እንዲሁም በትግራይ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን ማደረግ አለበት ብሏል።

- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢሳያስ አፈወርቂ " አምባገነን " ስርዓት ላይ ትክክለኛ ማዕቀብ እንዲጥልና ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን የህወሓት ክስ በተመለከተ ከ "ኤርትራ" በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ጦርነት እንዲያበቃ ፤ ያሉት ችግሮችም #በሰላም እንዲፈቱ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ለተቸገሩት ዜጎች ሁሉ እንዲደርስ ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ በደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ (የስምምነቱ ማስፈፀሚያ ላይ) ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

በናይሮቢ ስምምነት በትግራይ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት የውጭ ኃይሎችን እና ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ኃይሎችን ሁሉ ከክልሉ (ከትግራይ ክልል) ከማስወጣት ጋር #አብሮ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሰብሰባውን ያደረገ ሲሆን ስብሰባውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ባለ 10 ነጥብ ስምምነት ቤተክርስቲያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው…
#የሰላም_ጥሪ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ተከታዩን የሰላም ጥሪ አቅርቧል  ፦

1. ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣

2. ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያኗ ለሀገሪቱ ሰላም ካላት የጸና አቋም አንጻር አሁንም በድጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት በተደረሱት 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ከዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጽሑፍ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉና በቤተ ክርስቲያ ቀኖና መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀኖናቸውን ተቀብለው እንዲፈጽሙ፣

3. የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለሰላም ስምምነቱ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያኗ ምስጋናዋን ያቀረበች ሲሆን በቀጣይ በተደረሰው 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ሕገ-ወጦቹ ግለሰቦች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ የበኩላቸውን መንግሥታዊ ሚና እንዲወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን በድጋሚ አስተላልፋለች።

4. በተደረሰው ስምምነት መሠረት በሕገ-ወጥ መንገድ አህጉረ ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሰብረው የያዙ ግለሰቦችን በተመለከተ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ተገቢውን የሕግ ማስከበር ሥራ በመሥራት ከቤተ ክርስቲያን ይዞታ በማስወጣት ለቤተ ክርስቲያናኗ ሕጋዊ የሥራ ኃላፊዎች በማስረከብ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእለት ከእለት ተግባርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለምንም የጸጥታ ሥጋት እንዲከናወን እንዲሁም በተደረሰው ስምምነት መሠረት እስከአሁን መፈታት ሲገባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎችና ምእመናን እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን አስተላልፋለች።

5. ሃያ አምስቱን ግለሰቦች በሚመለከት ከኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይት ርእሰ መስተዳድሩ በተደረሰው 10ሩ ስምምነት ነጥቦች መሠረት " ሃያ አምስቱንም ግለሰቦች አጠቃልዬ ወደ አዲስ አበባ አመጣቸዋለሁ " በማለት በገቡት ቃል መሠረት በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦቹ በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ስለተሰማ የክልሉ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት ለፈጸመው አድራጐት ቤተ ክርስቲያኗ ያመሰገናች ሲሆን ያልገቡትን ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተገባው ቃል መሠረት እንዲገቡ እንዲደረግ ቤተክርስቲያኗ ጥሪ አስተላልፋለች።

6. ውግዘቱን በሚመለከት ውግዘቱን የማንሳት ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጠቃለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል።

ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77044?single

@tikvahethiopia
#ረመዷን

በመላው ዓለም ላይ የሚታወቁት የዝምባብዌ ዜግነት ያላቸው የእስልምና መሁር ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ስለ ቅዱሱ የረመዷን ወር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia