TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ አድርጉ‼️

#ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ። ወዳጆቻችን ሳታውቁት በወንጀል እንዳትጠየቁ ቅድመ ጥንቃቄ አድርጉ።

ለማሳያነት፦ ባለፈው ሳምንት አንዲት ኢትዮጵያዊ በኤርፖርት ስትፈተሽ ያልተገቡ ነገሮችን ይዛ በመገኘቷ ለእስር ተዳርጋለች (ሰው አድርሽልኝ ብሏት) እንዲሁም አንድ ኢትዮጵያዊ ከወራት በፊት በተመሳሳይ ለእስር ተዳርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኤርትራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 65 ደረሱ! በኣዲባራ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ከሚገኙ ከውጭ ተመላሾች መካከል ሃያ አራት (24) ሰዎች /ከሱዳን የተመለሱ/ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው መረጋገጡን የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ምሽት አሳውቋል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ ስልሳ አምስት (65) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሰላሳ ዘጠኝ (39) ሰዎች ከበሽታው…
በኤርትራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 96 ደርሰዋል!

የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጡ 31 ሰዎች ማግኘቱን በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን #BBC ዘግቧል።

ሚንስቴሩ እንዳስታወቀው 31ዱ ሰዎች የተገኙት የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 30 ሰዎች በቅርቡ ከሱዳን የተመለሱ ኤርትራውያን ሲሆን አንዱ (1) ደግሞ #ከኢትዮጵያ የተመለሰ ኤርትራዊ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Somalia #SW

ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ።

የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ።

ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው።

በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ ግድያውንና ጥቃቱን አውግዘው ከጥቃቱ ጀርባ የአልሸባብ የሽብር ቡድን መኖሩን አመልክተዋል።

ይህ ጥቃት በያዝነው ወር እኤአ በቀን 27 በታችኛው ሸበል ክልል የማርካ ወረዳ አስተዳዳሪ አብዱላሂ አሊ ዋፎውን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎችን ከገደለው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት እንዲሁም በአፍጎዬ ከተማ ፍንዳታ ተከስቶ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ከቆሰሉበት ጥቃት ከቀናት በኃላ የተፈፀመ ነው።

በሌላ በኩል፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ዛሬ #ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰነው የሶማሊያዋ የድንበር ከተማ " አቶ " ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልወደዱ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣን በሰጡት ቃል ፤ የሽብር ቡድኑ አቶ ላይ በ2 ሳምንት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ጥቃት መሰንዘሩን ይህን ተከትሎ ውጊያ መካሄዱን አመልክተዋል።

ዛሬ ወደ አቶ ዘልቆ ጥቃት የመፈጸም ዓላማ የነበረው የአልሻባብ ታጣቂ ኃይል፤ ያሰበው ሳይሳካ #ሽንፈት እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

በፀጥታ ኃይሎችም በኩል ጉዳት መድረሱን ያመለከቱት ባለስልጣኑ ለጊዜው ዝርዝር መናገር አልችልም ብለዋል።

አልሸባብ ከጥቂት ቀናት በፊት ኢትዮጵያን ለመዳፈር ሞክሮ በሶማሌ ልዩ ኃይል ክፉኛ መመታቱ አይዘነጋም። አሁንም በድንበር የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩን ለማወቅ ችለናል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

በትግራይ ክልል ጦርነት ሲቀሰቀስ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።

እነዚህ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ #የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃ እንዳለው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል አሳውቋል።

ተቋሙ ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ " ተአማኒ ሪፖርቶች "  ደርሶኛል ብሏል ለቢቢሲ በሰጠው ቃል።

ተቋሙ ይህን ካወቀ በኃላ ምን አደረገ ?

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን " ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘብኩኝ ጉዳዩን ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥትና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቴን ገልጫለሁ " ብሏል።  ይህንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ ነበር ሲል መልሷል።

ምልመላውን ማነው የሚያደርገው ?

ይኸው የተመድ ተቋም " ወታደራዊ ምልመላውን ለማካሄድ #ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች እንደነበሩ እና ይህንንም ከስደተኞች መረዳቱን ይገልጻል። ነገር ግን የትኛው ወገን ምልመላውን እንዳካሄድ " ማረጋገጥ አልቻልኩም"  ብሏል።

NB : ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ሰደተኛ ነን ብለው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ከህወሓት ጋር በመሆን ሲዋጉ እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-09-07

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UpdateAU #ETHIOPIA የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት…
#USA #ETHIOPIA

" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።

ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር " በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ "  ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።

ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።

ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።

" የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#AfricanDevelopmentBank

የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን በአስቸኳይ #ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ ነው።

ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአንድ ወር በፊት ዋና የኢትዮጵያ ተወካዩ እና ሌላ የባንኩ ሰራተኛ ላይ በፀጥታ አካላት ድብደባ መፈፀሙን ተከትሎ ነው።

በወቅቱ ባንኩ ቅሬታውን ለመንግስት አቅርቦ የነበረ ሲሆን መንግስትም አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር።

አሁን ባንኩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን " በአስቸኳይ " ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ሊያደርግ የወሰነው ድብደባውን ፈፅመዋል በተባሉት የፀጥታ አካላት ዙርያ ስለተደረገው ምርመራ የኢትዮጵያ መንግስት ለባንኩ መረጃ ባለማጋራቱ እንዲሁም በሰራተኞቹ ዘንድ በደህንነታቸው ዙርያ ሙሉ እምነት ሊያገኝ ባለመቻሉ እንደሆነ የባንኩ ፕሬዝደንት ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና አሳውቀዋል።

ምንም እንኳን ባንኩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ ለማስወጣት ውሳኔ ላይ ቢደርስም በኢትዮጵያ ያለው ቢሮው ክፍት ሆኖ እንደሚቆይና ውሳኔው ከኢትዮጵያ የተቀጠሩ ሰራተኞችን እንደማይመለከት ገልጿል።

እነዚህ ከኢትዮጵያ የተቀጠሩ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው እንደሚቀጥሉና በባንኩ ሙሉ የስራ ስምሪት ውስጥ / የባንኩ ሰራተኞች ሆነው እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ተሰጥቷል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮ ሰራተኛ ከኢትዮጵያ ባስቸኳይ እንዲወጡ የሚደረጉት ዓለም አቀፍ ሰራተኖች ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ሊዛወሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

እንደ ሬውተርስ ዘገባ የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ የ308 ሚልዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ስምንት ፕሮጀክቶች አሉት።

Credit - Journalist Elias Meseret

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ማንኛውንም ሰው #ከሀገር_እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለህ/ ተ/ ም/ ቤት  ቀርቧል።

የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ?

ማሻሻያው ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ይሰጣል።

ነባሩ ህግ ምን ይላል ?

" ማንኛውም ሰው #ከኢትዮጵያ_እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት #በፍርድቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው " ይላል።

ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ ላይ የተቀመጠውን የፍርድ ቤትን " #ብቸኛ_ስልጣን " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት #ያጋራ ነው።

ማሻሻያው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ፦

⚫️ ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት ፤

⚫️ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል ሲል ደንግጓል። 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍ/ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት "ም ይላል የአዋጅ ማሻሻያው። 

ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።

አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " ሲል የረቂቅ አዋጁ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ማሻሻያ አዋጁ " #አስተዳደራዊ_ቅጣት " አንቀጽ ይዟል።

" ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል።

በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል።

#የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል።

" ይህን አዋጅ አሊያ በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው።

Credit:
#EthiopiaInisider 
#JournalistTesfalemWoldeyes

@tikvahethiopia