TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አና ጎሜዝ አዲስ አበባ ገቡ🔝

#አና_ጎሜዝ አዲስ አበባ ገብተዋል። አና ጎሜዝ #በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ነው ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገቡት። በሦስት ቀናት ቆይታቸው የመንግስት #ባለስልጣናትን፣ የፓርቲ #መሪዎችንና የበጎ አድራጎት አመራሮችን እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር እንዲገናኙ ፕሮግራም ተይዞላቸዋል፡፡

Via Getu Temsegn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት አባልና የፖርቹጋል ተወላጇ #አና_ጎሜዝ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል። በምርጫ 97 የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢ ልዑክ መሪ የነበሩት እና ጎሜዝ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎቻቸው የእርሳቸውን ምስል የታተመበት ቲሸርት ለብሰው ተቀብለዋቸዋል። አና ጎሜዝ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፤ በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አና ጎሜዝ🔝

ሁሉም #ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ አስተዋጽኦ ስላለው አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ነኝ ብሎ ማሰብ እንደሌለበት #አና_ጎሜዝ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በ1997 ዓ/ም በተደረገ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጎሜዝ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስለአንድነት እንጂ ስለመከፋፈል ማሰብ የለባቸውም ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት አባል የሆኑት ጎሜዝ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ መጥቷልም ብለዋል። ይሁንና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች ሚሊዮኖች #እንዲፈናቀሉ አድርገዋል ብለዋል። አና ጎሜዝ ኢትዮጵያውያን አንድነት ላይ ከሰሩ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ዕምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia