TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሁን2021

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከ xHub Addis (የጀማሪ ሥራ ፈጠሪዎች ማበልፀጊያ ማዕከል) ጋር በተለያዩ ዘርፎች የቢዝነስ ሃሳብ ያላቸው ጀማሪዎችን ለማሳደግ #አሁን2021 የውድድር መድረክ የተሳትፎ ጥሪ ቀርቧል።

#አሁን2021የአራት ወራት የስልጠና እና የማበልጸጊያ ፕሮግራም ሲሆን በፍጥነት የማደግ እምቅ አቅም ያላቸው የቢዝነስ ሃሳቦችን በማገዝ በማወዳደርና ለሥራ ማስጀመሪያ የሚሆን ዶላር የመሸለም ዓላማ ያለው ተብሏል።

ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በ https://xhubaddis.com/jcc/ መመዝገብ ትችላላችሁ።

አመልካቾቸ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፦

• ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው/ያላት
• ኢኖቬቲቭ የቢዝነስ ሀሳብ ያለው/ያላት

ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

#Share #ሼር

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT