TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰብዓዊነት⁉️

ለ30 ደቂቃ በየቤታችሁ ተወያዩ!!
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ በየዶርማችሁ!!

#ሰብዓዊነት ከምንም ነገር ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። ሰው ሲሞት፣ ሲደበደብ፣ ሲጎዳ፣ ሲሰደድ ስናይ ልባችን ሊደማ የሚገባው የኛ ወገን እና ብሄር ተወላጅ ስለሆነ ብቻ መሆን የለበትም። የሰው #ስቃይ እና #መከራ እንደሰውነቱ ካልተሰማን በህይወት መኖራችን ትርጉም አልባ ነው። ሰው ሲኖር ነው ሀገር፣ ብሄር፣ ዘር፣ ክልል፣ ባንዲራ የሚኖረው። ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርባትን ታላቅ ሀገር ለመፍጠር እኛ አስተዋፅኦ እያደረግን ነው???

3 እና ከዚያ በላይ ሆናችሁ በያላችሁበት ተወያዩ!! ውይይታቹ ላይ የተነሱ ሀሳቦችን ላኩልኝ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቅ ኮሚቴ አባላት ታፍነው ተወሰዱ‼️

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥትን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የግንባሩን ወታደሮች #ለመቀበል ወደ #ቄለም_ወለጋ አቅንተው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት #ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።

የእርቅ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ #በየነ_ሰንበቶ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የኮሚቴው አባላት የሆኑ ሁለት አባ ገዳዎች እና አንዲት ሴት በቄለም ወለጋ #አንፊሎ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ታፍነው እንደተወሰዱ ተናግረዋል።

አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ''ለማግባባት ወጣ እንዳሉ ነው ታፍነው የተወሰዱት፤ ክፉ ነገር #እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህንም ችግር በቅርቡ እንፈታዋለን'' ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

''ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖሩን እየወቅን ነው እርቅ ወደማውረዱ የገባነው። እርቅ ለማምጣት ነው እየሰራን ያለነው። ሰላምም ይሰፍናል። የሚያጋጥሙን ችግሮች ወደ ኋላ አያሰቀሩንም'' ሲሉም ጥረታቸውን በዚህ ምክንያት እንደማያቋርጡም ተናግረዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያነጋገረው የየኮሚቴው ፀሃፊ #ጀዋር_መሃመድም የእርቅ ኮሚቴ አባላት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ተናግሯል።

''የገጠመ ችግር አለ። በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ከኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለህዝቡ መግለጫ እንሰጣለን'' ሲል ጀዋር ገልጿል።

ጀዋር ሃሙስ ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን አራት ሰዎች ከስም ዝርዝራቸው ጋር አውጥቷል። ታፍነዋል ተወስደዋል የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል።

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡ ወረዳ የቴክኒክ አባላቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከነዋሪዎች ተሰምቷል። ተፈጸሟል ስለተባለው ድብደባ ግን ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት #ማረጋገጥ አልተቻለም።

የእርቅ ኮሚቴ አባላቱን ማን አፈናቸው?

የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶም ሆኑ የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድ የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ያፈነው ኃይል ይህ ነው በማለት በስም ከመጥቀስ #ተቆጥበዋል

ጀዋር የአባላቱን መታፈን ይፍ ባደረገበት ጽሁፍ ''እየደረሰብን ያለውን #ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን'' ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ደለሳ ቡልቻ ለሁለት ቀናት ታፍነው ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸው ይታወሳል። ዶ/ር ደለሳ የገጠማቸውንና ማን እንዳፈናቸው ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ባንኮች በተዘረፉበት ወቅትም የባንክ ሰራተኞችም ታፍነው ተወስደው እንደነበረ ይታወሳል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት~~ማንቡክ ለሚገኙ ዜጎች‼️

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ዳንጉር ወረዳ ማንቡክ ቀበሌ እየተፈፀመ ያለውን የዜጎች #ስቃይ እና #እንግልት የፌደራሉ መንግስት በአስቸኳይ ሊያስቆመው ይገባል፤ ወንጀለኞችንም ሳይውል ሳያድር ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል። ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ወጥተው ለመግባት #የሚሳቀቁበት እና #የሚፈሩበት ምክንያት ሊኖር አይገባም።

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት
ለፌደራል ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ

የሚወደውን ሰው፣ አምላክ ይፈትናል
ቃሉም እውነት አለው፣ ያንቺ #ስቃይ በዝቷል
ፈተናሽም ታይቷል፣ ስቃይሽም በዝቷል
ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ ምድራዊ ገነት
ለበጎ ይሆን ወይ፣ ያንቺ ስቃይ መብዛት
ያንቺ ስቃይ መብዛት
ያንቺስ ድህነት
ኋላ ቀርነት።

ታንፀን፣ በሰላም፣ #በተስፋ፣ በፍቅር፣ እምነት
ማለፍ እንድንችል ፣ ስንፍና ይውጣ ከቤት
እኛ ተቀምጠን ፣ ስለምን ወገኔ ይራባል
ጠንክረን ከሰራን ፣ ልመና ታሪክ ይሆናል
ያልተነካ ጉልበት ኦሆ ከቤት ተቀምጦ ኦሆ
ወገን ለምን ይለቅ ኦሆ በጠኔ ተውጦ ኦሆ
ልጅ አዋቂ ሳንል ኦሆ ሁላችን ባንድነት ኦሆ
እንውጣ ከችግር ኦሆ የሰው እጅ ከማየት ኦሆ
የያዝነውን ይዘን ኦሆ ተባብረን እንስራ ኦሆ
ስሟም ያገራችን ኦሆ በበጎ ይጠራ ኦሆ

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ

ቅድስት ሀገሬ፡ ኢትዮጵያ
የብሄር አምባ፡ መጠለያ
ታሪካዊት ናት፡ እናታችን
ሁሉም ሙሉ ነው፡ ከቤታችን
ዞር ብለን ለምን፡ እንይ ሌላ
እያለችን ዋርካ፡ መጠለያ
ይለወጥ ስሟ፡ ያገራችን
በስራ ጥረት፤ በክንዳችን

#MisikerAwol

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም…
#የአሜሪካ_አቋም!

" ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ?

- በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው።

- የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል።

- ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

- የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

- ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ።

- በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም።

- ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው።

- ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው።

- የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ።

- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው።

- በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።  

- ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል።

- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል።

- ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል።

- ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው።

- የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል።

- ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

- ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል።

#USEmbassyAddisAbaba
#VOA
#EthiopiaInsider

@tikvahethiopia