TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ ሰኔ 16ቱ ጥቃት ሪፖርተር እና EBC⬇️

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች ላይ #የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ በሽብር ወንጀል #ክስ መሰረተባቸው።

ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ጌቱ ግርማ ፣ብርሃኑ ጁፋር ፣ጥላሁን ጌታቸው ፣ባህሩ ቶላና ደሳለኝ ተስፋዬ ላይ ነው፡፡

ዓቃቢ ህግ ሁሉንም ተከሳሾች ሰኔ 16 በነበረው የድጋፍ ሰልፍ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ላይ ጥቃት ለማድረስ ብሎም በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመራ መንግስት መኖር የለበትም የሚል ዓለማ ይዘው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል።

እንደ ክሱ ገለፃ ከሆነ ይህ ዓለማ ቀድሞ በተደራጀ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱና የቦንብ ጥቃት ማድረስ በሚችሉ አባላት አማካኝነት መሆን እንዳለበትም የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተቀባይነት የሌላቸው በተለይም በኦሮሞ ብሔር ዘንድ አንደማይፈለጉ አድርጎ ለማሳየት በሚረዳ መልኩ ጥቃቱን ለመፈፀም ዐቅደው መንቀሳቀሳቸውም በክሱ ተጠቁሟል።

ለዚህ ደግሞ በኬንያ የምትኖር ገነት ታምሩ ወይንም በቅፅል ስም #ቶሎሺ ታምሩ በምትባል የቡድኑ አባል አማካኝነት ተልዕኮ እንደተሰጣቸው በክሱ ተገልጿል።

አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከዚች ሴት ጋር ሰኔ 2010 በስልክ በመገናኘት ' ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ መካሄድ የለበትም'፣' መሰረታዊ ለውጥ አልመጣም '፣ ' ሰልፉን የጠራው ገለልተኛ ወገን ሳይሆን ኢህአዲግ ነው '፣ ' HR128 የተባለውና በአሜሪካ ኮንግረንስ የተላለፈው ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል' በሚል ሰልፉ እንዲበተን አድርጉ የሚል ተልኮ እንደተቀበለም ክሱ አመልክቷል።

አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከሁለተኛ ተከሳሽ ብረሃኑ ጁፋር ጋር በሰኔ ሱሉልታ ላይ ስለ ተልኮው በመነጋገር ቦንብ እዲያዘጋጅ፣ ቦንቡን የሚወረውርን እንዲያፈላልግ ተነጋግረው ለሶስተኛ ተከሳሽ ጥላሁን ጌታቸው ደውሎ ቦንብ የሚወረውር ሰው እንዲፈልግ ተልኮ
መስጠቱም ክሱ ያሳያል።

ሁለተኛ ተከሳሽ ያዘጋጀውን ሁለት ኤፍ 1 ቦንብ እንዲሁም አንድ የጭስ ቦንብ በአንደኛ ተከሳሽ ቤት በማስቀመጥ ከሱሉልታ በመነሳት ሰልፉን በመቀላቀል በኛው ተከሳሽ አመካኝነት ቦንቡን በማፈንዳት ሙሳ ጋዲሰና ዬሴፍ አያለው የተበሉ ግለሰቦች ላይ የሞት 165 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድ ና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውም በክሱ ተጠቁሟል። በዘህም መሰረት ዓቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል

ምንጭ፦ EBC

ሪፖርተር፦

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች #የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) #ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡

በቦምብ ጥቃቱ ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች አቶ ጌቱ ግርማ፣ አቶ ብርሃኑ ጃፋር፣ አቶ ጥላሁን ጌታቸው፣ አቶ ባህሩ ቶሎሳና አቶ ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው፡፡

ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ እንደገለጸው፣ ተከሳሾቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ላይ ግድያ ለመፈጸም ያነሳሳቸው በእሳቸው የሚመራ መንግሥት #መኖር ስለሌለበት ነው፡፡ የአገሪቱ መንግሥት መመራት ያለበት ቀድሞ በተመሠረተው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው የሚል ዓላማ ተከሳሾቹ እንዳላቸው ዓቃቤ ሕግ በመሠረተው #ክስ ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም በማለትም፣ ተጠርጣሪዎቹ ለግድያ መነሳሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ ኮንግረስ የፀደቀውን ኤችአር 128 ለማስፈጸምና በስመ ሕዝበኝነት የራሳቸውን ዓላማ የሚያራምዱ መሆናቸውን፣ በዚህም ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ስለማያስፈጽሙ ተጠርጣሪዎቹ ጥቃቱን ለመፈጸም መነሳሳታቸቸውን ዓቃቤ ሕግ
በክሱ አክሏል፡፡

የሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል አደባባይ የወንጀል ድርጊት ያቀነባበረችው በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ ገነት ታምሩ (ቶለሺ ታምሩ) የምትባል መሆኗን፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አመልክቷል፡፡

በመስቀል አደባባይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍና ምሥጋና በተደረገ ሥነ ሥርዓት ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ሁለት ግለሰቦች ሲሞቱ፣ ከ150 በላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia