TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹አሜሪካ የሁላችንም ናት፤ ታላቅ ሀገር የምትሆነው በብዝሃነት ስትደምቅ ነው፡፡›› ሚሼል ኦባማ

ሚሼል ኦባማ አሜሪካ የሁሉም ነዋሪዎቿ መሆኗን ተናገሩ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሰሞኑን #ስደተኞችን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ የቀደሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባለቤት ሚሼል ኦባማ ‹‹አሜሪካ የእኔም፣ የአንተም ሳትሆን የሁላችንም ናት›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞዋ ቀዳማዊ እመቤት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሰሞኑን በትዊተር ገፃቸው በአራቱ ሴት የፓርላማ አባላት ‹‹አሜሪካን ለቅቀው ወደ መጡበት አገራቸው መመለስ ይችላሉ›› ማለታቸውን ተከትሎ የሰጡት መልስ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

አሜሪካ ታላቅ ሀገር የምትሆነው በብዝሃነት ስትደምቅ ነው ሲሉም ሚሼል ኦባማ ጠቅሰዋል፡፡ በሀገሪቱ የተወለደም ይሁን በስደት የመጣ ሁሉም በእኩልነት እና በአንድነት የበኩሉን ድርሻ ማበርከት ከቻለ አሜሪካዊ ለመሆንም፣ ለመባልም በቂ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ዴይሊ ሜይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia