TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዕለቱ መልዕላክት፦

መከባበር፣ መዋደድ፣ መተሳሰብና አንድነት ካለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ #ለምለም_ምድር ናት።

መከባበር

ሰው በሰውነቱ ብቻ ሊከበር ይገባል፤ ሰውን ስናከበር እምነቱን፣ ባህሉን፣ ቋንቋውን፣ ብሄሩን፣ የኔ ነው የሚለው ነገር ሁሉ እናከብርለታለን። አመለካከቱን፣ አስተሳሰቡን እናከብርለታለን። ርቀን ሳይሆን ተጠግተን የሚጠቅመንን እንወስዳለን። የተሳሳተ መንግድ ላይ ካለም በመልካም ቀረቤታና በፍቅር በልዩ ክብር ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ ይቻላል። ሰው አመለካከቱ ምንም ይሁን ምንም በሰውነቱ ብቻ ሊወደድ እና ሊከበር የሚገባው ፍጡር ነው።

መዋደድ

እኛን የፈጠረን ፈጣሪ ይወደናል ብለን እንደምናስበው ሁሉ በምድር ላይ ያሉ የሰው ልጆችን በእኩል አይን ልንመለከትና ልንወድ ይገባል። ሰውን መውደድ የፈጠረንን ፈጣሪን መውደድ ነውና።

መተሳሰብ

እኛን የሚሰማን እያንዳንዱ ስሜት ሌሎች ሰዎችንም ይሰማቸዋል ብለን እናስብ። ሲርበን ሌሎችም ልክ እንደኔው ይራባሉ ብለን እናስብ፤ ሰው ሲጎዳ እኔ ነኝ የተጎዳሁት ብለን እናስብ፤ አንዳችን የለሌላኛችን ባዶ መሆናችንን እናስብ። ለኛ እንደምንስሳሳው ለሰው ልጅ ሁሉ ልንሳሳ ይገባል። አንዳችን ለሌላኛችን በችግራችን ጊዜ ልንደርስ ይገባል።

አንድነት

እኛን አንድ የሚያደርገን ከኢትዮጵያዊ ዜግነታችን በፊት ሰውነት ነው። አንድነታችን ሊጠነክር የሚገባው በሰውነት መሰረት ላይ ነው። ዜግነት ይቀየር ይሆናል ሰው መሆን ግን በፍፁም! ከምንም በፊት ሰውነት ይቅደም። ከሰውነት በኃላ እንደ አንድ ሀገር ዜጎች አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ላይ ልንሰራ ይገባል።

እስከዛሬ #ስለሰብዓዊነት በአግባቡ ተሰርቶ ቢሆን ኖሮ የሰማናቸውና አየሰማናቸው ያሉ የሞት፣ የመፈናቀል፣ የስቃይ ዜናዎች ባልኖሩ ነበር። ሰው መሆን ማለት እኔ የሚሰማኝን ሰዎች ይሰማቸዋል ብሎ ማሰብ ነው።

#መሰድብ እንደማልፈልገው ሌሎችም #ክብራቸው እንዲነካ አይፈልጉም፤ በሰላም መኖርን እንደምፈልገው ሁሉ ሌሎችም በሰላም መኖር ይፈልጋሉ፤ ስቃይ እንደማልፈልግ ሁሉ ሌሎችም መሰቃየትን ፈፅሞ አይፈልጉም።

ኢትዮጵያን በመከባበር፣ በመዋደድ፣ በመተሳሰብና በአንድነት እንገንባ!! አሁን ካለንበት አስከፊ የድህነት ኑሯችን ውስጥም እንውጣ!!

#TIKVAH_ETH
🗓ሀምሌ 27/11/2011 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia