TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መልዕክት

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሁሉም አባላት ድምፅ የሚሰማባት ሰፊው ቤታችን ነው።

ትልቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስራም ከ1.1 ሚሊዮን በላይ አባላት መካከል የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማድረግ ነው።

ቲክቫህ ፦

- የሚዲያ ባለቤቶች እና የሚዲያ ሰዎች፣
- የጋዜጠኞች፣
- የጤና ባለሞያዎች፣
- የገበሬዎች፣ የአርሶና አርብቶ አደሮች
- የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ፣
- የገዢ ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች ፣
- የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች፣
- የተማሪዎች፣
- የንግድ ሰዎችና ባለሃብቶች የሌሎችም በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

ቲክቫህ ከመነሻው የሃሳብ ብዝሃነት ለሀገር እድገት ያለውን ከፍተኛ ሚና የሚረዱ ፣ ለሀገር የሚያስቡ፣ በሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚፅፉት እያንዳንዱ ቃል ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርጉ አባላትን ባለፉት ዓመታት ማፍራት ችሏል።

የእውነተኞቹ የቲክቫህ አባላት መገለጫ ብስለት፣ እርጋታ፣ መረጃ ማመዛዘን፣ የነገን የአብሮነትና ጉዞ ማሰብ፣ ለወገን መቆርቆር ነው።

ያለፈውን አንድ ወር የሀገራችን ማህበራዊ ሚዲያ የለየለት የውሸት እንዲሁም የጥላቻ መድረክ ሆኖ ማለፉን ሁሉም የቲክቫህ አባላት የሚያውቀው ነው።

እንዲህ ያሉ ወቅቶች በተደጋጋሚ ስለገጠሙ እና በእንዲህ ያለ የውጥረት ሰዓት ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዴት እንደሚዘወሩ ለቲክቫህ አባላት አዲስ አልነበረም።

ለዚህም ነው ከጥቂቶች / ከአዲስ አባላት ውጭ ሁሉም አባል በሚባል ደረጃ እያንዳንዱን ሁኔታ በፍፁም እርጋታ ሲከታተል የነበረው።

ያልሰሙትን ሰምተናል፣ ያላዩትን አይተናል ፣ ያልተደረገውን ተደርጓል እያሉ የተገኘውን ተባራሪ ወሬ ሁሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት በጊዜ ሂደት ምን ምን ጉዳዮችን ሲዋሹ እንደነበር ሁሉም አባላት በትዝብት ተመልክቷል።

ምንም ያለተረገጠና ውቅቱን ያልጠበቀ እንዲሁም ተባራሪ ወሬዎችን ለህዝብ ሲያሰራጩ የከረሙት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ብዙ የሀገራችን እናቶች ፣ ወላጆችን በሀሰት ዜና አስነብተዋል፣ ብዙ ቀናትንም ያለ እንቅልፍ በጭንቀት አሳድረዋል።

እውን እኛ ያለንባት #ኢትዮጵያ እንደ ማህበራዊ ሚዲያው ያለች ብትሆን ለአንድም ቀን እንኳን በሀገራችን ባላደርን ነበር።

ውድ አባላት የዛሬው መልዕክታችን ፦

• መረጃ ለቲክቫህ 1.1 ሚሊዮን አባላት ለማሳወቅ ስትልኩ ስለምታውቁት /ስላረጋገጣችሁት/ ጊዜውን እና ወቅቱ ስለመጠበቁ ገምግማችሁ እንዲሆን፤
• ሁሉም ወገን ወገን ፈጥሮ በሚሰራው ዘመቻ ተጠልፋችሁ እንዳትወድቁ በመጠንቀቅ፤
• የአእምሮ ጤናችሁን ከሚያቃውስ የስድድብ፣ የጥላቻ አካባቢዎች በመራቅ፤
• የምትናፍቋችሁን የቲክቫህ ትግራይ ክልል አባላት በትዕግስት የመልዕክት ልውውጥ ማድረግ እስኪጀምሩ በመታገስ፤
• ያላረጋገጣችሁትን ጉዳይ ባለመናገር ፣
• በየማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚነገረው ሁሉ እውነት ነው እያላችሁ ለሰው ከማጋራት በመቆጠብ ፣
• በተለመደው እርጋታችሁን ፣ ትዕግስታችሁን ፣ መከባበራችሁን ፣ የነገ አብሮነታችሁን እና ሀገራችሁን በማሰብ ወደፊት ትቀጥሉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

ሌላው በትግራይ ክልል ያሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቲክቫህ አባላት ደህንነት ለማወቅ እየሰራን ነው፤ ስልክ የሚሰራባቸው አካባቢዎች ያሉ አባላቶችን እያገኘን ነው።

የትግራይ ክልል የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት #የኢንተርኔት ግንኙነት በሚያገኙበት ጊዜ ከዞን፣ ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ መረጃዎችን አዲስ በተዘረጋው የቲክቫህ አባላት የመረጃ ልውውጥ መድርክ www.tikvahethiopia.net ላይ ያሳውቃሉ ብለን እንጠብቃለን።

ሌሎችም የቲክቫህ አባላት www.tikvahethiopia.net በመመዝገብ ስለአካባቢያችሁ ጉዳይ ብቻ የምታውቁትን ማካፈል ትችላላችሁ። የአንድ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ መረጃ በሌሎች አባላት አይታይም!

Tikvah/Hope/ተስፋ
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopiaBOT
#መልዕክት

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት

- በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲኬድ የፀጥታ አካላት በየቦታው ፍተሻ ያደርጋሉ፤ ይህንንም ህዝበ ክርስትያኑ እንዲገነዘብ ተብሏል። ምናልባት ፍተሻው 2 እና 3 ቦታ ቢሆን እንኳን ፍተሻው ለራስ ደህንነት መሆኑን በመገንዘብ ህዝበ ክርስትያኑ ሳይሰላች ለፍተሻው እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

- ከባንዲራ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ - ወደበዓሉ ቦታ በሚኬድበት ጊዜ ፣ የወጣት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት እንዲሁም ሌሎች አካላት በሀገሪቱ ህገመንግስት የፀደቀውን የፌዴራል አርማ ያለበትን ባንዲራ ብቻ መጠቀም ይገባል ተብሏል፤ አላስፈላጊ ሎጎዎችን እና ህጋዊ ከሆነው ባንዲራ ውጪ መጠቀም አይቻልም፤ ለዚህም ለፀጥታ አካላት ትብብር ማድረግ ያስፈልጋል።

- ከኢትዮጵያ ብሄራዊው ባንዲራ ውጪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት «ነዋ ወንጌለ መንግሥት» የሚል አርማ ያለበትን ባንዲራ መጠቀም ይቻላል፤ ህዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ባንዲራ ሲጠቀም በስነስርስአቱ የታተመ፣ በሁለቱም በኩል ሎጎው እንዳለ የሚያሳይ መሆን አለበት።

- ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲሄድ የኮቪድ-19 መከላከያ ጥንቃቄዎችን መፈፀም እንዳለበት አደራ ተብሏል። ማስክ ያድርጉ፣ ሳኒታይዘር ያዙ ፤ ርቀታችሁንም ጠብቁ።

- የጤና ሚኒስቴር በመስቀል አደባባይ የኮቪድ-19 የክትባት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፤ በቦታው ላይ ክትባት ስለሚሰጥ ቀደም ብሎ በመገኘት የክትባቱ ስነሥርዓት ተሳታፊ መሆን እንደሚቻል ተገልጿል።

- ከመስቀል አደባባይ ውጭ የሚደረጉ የመስቀል ደመራ ስነስርዓቶች የፀጥታ ኃይሎችን በመተባበር እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

- ለበዓሉ ድምቀት በሚል ርችት መተኮስ አይፈቀድም።

@tikvahethiopia
#መልዕክት

ከሰዓታት በኃላ 2ኛው " የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ " መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ለታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር 2 ለመታደም ሲመጡ ፦

👉 የራሳችሁን መስገጃ ይዛችሁ ኑ።

👉 አዘጋጆች የሚዘጋጁት ምግብ ቢኖርም ሁሉም የቻለውን ያህል ለሰዎች ጭምር የሚሆን ምግብ ይዞ ይምጣ።

👉 ሁሉም የተመገበበትን እቃ የሚያነሳበትን ፌስታል መያዝ እንዳይዘነጋ።

👉 በመሃል ሌባ ሊኖር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

👉 አቅመ ዳካማዎችን፣ታላላቆችንና ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲያገኙ አድርጉ።

👉 ለአስተናጋጆች፣ ለኻዲሞችና ለፀጥታ አካላት ፍፁም ታዛዥ ይሁኑ።

👉 በጦርነትና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ለሚንቀሳቀሱ አስተባባሪዎች ድጋፍ ያድርጉ።

👉 እርስ በእርስ በመከባበር እና በመተዛዘን እጅግ የሰለጠነና ምስኪኖችን ታሳቢ ያደረገ ኢፍጣር እንዲሆን ሁላችንም ባለቤቶች እንደሆንን በማሰብ ተግባራዊ ያድርጉ።

📞 ማንኛውም አይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በቦታው ለሚገኙ የፀጥታ አካላትና አስተባባሪዎች ወይም በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111110111 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት ይተባበሩ።

(ከአዘጋጆች)

መልካም የኢፍጣር ስነስርዓት !

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድሩ በነገው እለት ጥዋት በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንዲካሔድ በመንግስት ፍቃድ መሠጠቱ ተሰምቷል። በዚህም መሠረት ነገ ሰኔ 6 ቀን 2014 ፕሮግራሙ እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#መልዕክት

ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦

" የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል።

ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መልዕክት ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦ " የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል። ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ " @tikvahethiopia
#መልዕክት_2

(ነገ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር)

- ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዐት ጀምሮ ስለሚካሄድ በጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም እንገኝ።

- በ500 ብር ትኬታ የቆረጠ ሁለት ሰው ሆኖ መግባት ይችላሉ። ትኬት ያልገዙ ሰዎች በ200 ብር በር ላይ እንዲገዙ ተመቻችቷል።

- ሴቶች ከወጋገን ባንክ ፊት ለፊት ያሉትን በር ቁጥር 8፣ 9 እና 11ን ብቻ ተጠቀሙ። የVIP እንግዶችም በVIP በኩል መግባት ትችላላችሁ።

- ሁሉም የራሱን መስገጃ ይዞ መገኘት አይዘንጋ

- የተጠቀምናቸውን ውሀና ብስኩቶች የምናነሳበትን ፌስታል መያዝ አይዘንጉ። በመሃል ሌባ ሊኖር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ።

- አቅመ ዳካማዎችን፣ታላላቆችንና ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲያገኙ አድርጉ

- ለአስተናጋጆች፣ ለኻዲሞችና ለፀጥታ አካላት ፍፁም ታዛዥ ይሁኑ።

ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር

Via ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

@tikvahethiopia
#መልዕክት

1. የፌስቡክ እና ዩትዩብ አድራሻ የለንም !

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚገናኙበት ወይም እርስ በእርስ መልዕክት የሚለዋወጡበት ምንም አይነት የፌስቡክ (Facebook) ሆነ ዩትዩብ-Youtube (አክቲክቭ) አድራሻ #የለም። በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም አይነት የፌስቡክ ገፆች እና ግሩፖች እንዲሁም አክቲቭ የሆኑ ዩትዩብ አካውንቶች ቤተሰቡን አይወክሉም።

2. ማስታወቂያ እንሰራል ከሚሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ !

ቲክቫህ የድርጅት ባለቤት፣ ለተቋማት አመራር፣ የማርኬቲንግ ባለሞያ ለሆኑ የቤተሰቡ አባላት መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ የሚያመቻች ቢሆንም በፕሮግራምና በተመጠነ መንገድ ብቻ ነው። የተለያዩ ግሩፕ በቲክቫህ ስም ከፍተው ማስታወቂያ እንሰራለን የሚሉ አጭበርባሪዎች ናቸው። (በዚሁ አጋጣሚ የዚህ ዓመት ማስታወቂያ ያበቃ ሲሆን ከመስከረም 20/2015 ጀምሮ በአዲስ መልክ ይጀምራል)

3. ገንዘብ ከሚሰበስቡ ተጠንቀቁ !

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ውስጥ በምንም ጉዳይ ገንዘብ አይሰበሰብም፤ ለሰዎች እገዛ ሲሆን የሚነገረው እገዛውን የሚሹ አካላት አድራሻ ብቻ ነው። በቲክቫህ ቤተሰብ ስም ገንዘብ የሚሰበስቡ አጭበርባሪዎች ናቸውና ተጠንቀቋቸው። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ከአባላት ጋር በተገናኘ በምንም ጉዳይ ገንዘብ አይጠየቅም አይሰበሰብም፤ ከገንዘብ ጋር የሚገናኝ ምንም ስራ የለም።

4. የመልዕክት መቀበያ አድራሻ !

ይህ መልዕክት መለዋወጫ @tikvahethiopiaBOT ስላስቸገረ በአዲሱ @officialtikvahethiopiaBOT መልዕክችሁን ላኩ። ባለፉት ሳምንታት መልዕክት ልካችሁ ያልታየም በአዲሱ መቀበያ አልያም (0919743630) አሳውቁ።

5. የመማሪ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (አዲስ አበባ) ለማበርከት 0919743630 ይደውሉ።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

የዘንድሮው ክረምት ተጠንክሮ በመቀጠሉ በሁሉም አካባቢ ያላችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ ማድረጋችሁን እንዳትዘነጉ።

በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያላችሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ለማስታወስ እንወዳለን።

የመኪና አሽከርካሪ የሆችሁ ቤተሰቦቻችንም በየአካባቢው እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ጉዞ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የራሳችሁን እና የሌሎችንም ወገኖች ደህንነት ልታስጠብቁ ይገባል።

ሌላው ልጆች ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ልጆቻሁን ጠብቁ ፤ በተቻለ መጠን ከባድ ዝናብ ሲጥል ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ በማድረግ ወቅቱን ማሳለፍ ይገባል። እጅግ አስፈላጊ ቦታ የሚሄዱ ከሆነም እንዲጠነቀቁ ማሳሰብ እንዳትዘነጉ።

#መልዕክት : ክረምት ሲመጣ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ወገኖቻችን ምን ያህል እንደሚሰቃዩ ይታወቃል ፤ በግለሰብ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ባንችልም አንዳንድ የሚለበሱ ለብርድ የሚሆኑ አልባሳትን በመስጠት እንደሁል ጊዜው በበጎ ስራችን እንቀጥል።

ቪድዮ : AN ከአዲስ አበባ (አዳዋ ድልድይ) ቲክቫህ ቤተሰብ

@tikvahethiopia
#መልዕክት

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ፤ ከዚህ ቀደም ይህ @tikvahethiopiaBOT መልዕክት መቀበያ አስቻገረ እንደሆነ መልዕክት ልከንላችሁ ነበር።

ይህ ችግር እስኪስተካከልም መልክት ለመለዋወጥ አማራጭ ይህን @OfficialTikvahethiopiaBOT እንድትጠቀሙ ገልፀንላችሁ ነበር።

አንዳንድ ቤተሰቦቻችን በ @tikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክቶቻችን እየታዩ እና እየተመለሱ አይደለም የሚል ቅሬት አቅርበዋል ችግሩ እስኪስተካከል በ @officialtikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክት እንድንለዋወጥ ከትልቅ ይቅርታ ጋር በድጋሚ እንገልፃለን።

ከዚህ ቀደም (ከሶስት ወር ወዲህ) ልካችሁ ያልታየም በድጋሚ መላክ ትችላላችሁ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቦቹ መልዕክት መለዋወጫ ነውና ከጥላቻ ንግግር፣ ከሀሰተኛ መረጃ፣ የሰዎችን እና የሀገርን ክብር ዝቅ ከሚያደርጉ መልዕክቶች ውጭ ማንኛውም ጥቆማ፣ ጠቃሚ መልዕክት ማጋራት እና መለዋወጥ ይቻላል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መልዕክት

የ " መስቀል ደመራ በዓል " አከባበርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት

- ሁከት ቀስሰቃሽ መልዕክቶችን በቲሸረሰቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ይዞ መገኘት በፍፁም አይፈቀድም።

- በበዓሉ ላይ ህገ መንግስቱ የደነገገውን የኢትዮጵያን የፌዴራል ሰንደቅ ዓላማ #ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የፀደቀውን የቤተክርስቲያን ዓርማን ብቻ መጠቀም ይገባል። ከዚህ ውጪ የሆነ ምንም ዓይነት አርማም ሆነ ሰንደቅ አላማ መያዝ በጥብቅ የተከለከለ ነው። የምንጠቀመው ሰንደቅ ዓላማ ሆነ የቤተክርስቲያን አርማ በግልፅ የሚታዩ በሁለቱም ፊት ዓርማዎቹ በትክክል የተቀመጡ መሆን አለባቸው።

- በቲሸርቶች ፣ በባነሮች እንዲሁም በትርኢቶች ላይ ሁሉ ሌሎች ወገኖችን የሚያስከፉ፣ መብትን የሚጋፉ ሁከት ቀስቃሽ የሆኑ ጥቅሶችን መጠቀም ከሥነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በላይ ለሁከትና ግርግር መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

- ወደ መስቀል አደባባይ በሚደረግ ጉዞ #ተደጋጋሚ ፍተሻ ይደረጋል፤ የሚደረገው ፍተሻ ለደህንነታችን ተብሎ የሚደረግ ፍተሻ መሆኑን በመገንዘብ መላው ህዝበ ክርሰቲያን ራሱን ለፍተሻ ዝግጁ ማድረግና ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ለፍተሻ መተባበር እንደሚገባው በመረዳት የጸጥታ አካላትን መተባበር አለበት።

- በመስቀል አደባባይ እንዲሁም ደብረ ዕንቁ ቅድስት ልደታ ማርያም ጉዳይ የሚመለከተውን አካል በሕግ አግባብ መጠየቅ የሚገባና እና በጉዳዩ ዙሪያ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ያከናውናሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ሊደረግ አይገባም።

- በቤተክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደርና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቶ ከሚሰራጨው መጽሔት እና ብሮሸር ውጪ ምንም ዓይነት የህትመት ውጤት ስለማይሰራጭ ከእነዚህ ውጪ የሆኑ የህትመት ውጤቶችንና በራሪ ወረቀቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይዞ የተገኘም በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

- ከመስቀል አደባባይ ውጪ በአድባራትና ገዳማት በሚከበሩ የመስቀል ደመራ በዓላት ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እና በመረዳዳት መሥራት የሚገባ ሲሆን ሁከት ቀስቃሽ ከሆኑ መልዕክቶች በመታቀብና ህጋዊ ያልሆኑ ሰንደቅ ዓላማዎችን ባለመጠቀም የበዓሉን ሰላማዊነትና የመስቀሉን ዓላማ መሰረት ያደረጉ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሱ እንቅስቃሴዎች ሊደረጉ ይገባል።

- ማንኛውም አጠራጣሪ እና ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች ሲያጋጥም በቦታው ለተመደቡ የሥነሥርዓትና የጸጥታ አስከባሪ አባላት / ለፖሊስ አካላት መጠቆም ይገባል።

(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን)

@tikvahethiopia
#መልዕክት🕊

አገራችን የደረሰችበትን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን መግለጫ የተላከልን ሲሆን ቤተክርስቲያኗ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ምእመናን አጥብቀው እንዲፀልዩ ጥሪ አቅርባለች።

ከተላከልን መግለጫ የተወሰደ ፦

" የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን በሁለቱ ወገኖች የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አጥብቃ ትደግፋለች።

የስምምነቱ መተግበር የዜጎችን ሞትና እንግልት የሚያስቀር፣ ጥላቻን ከወንድማማቾች መካከል የሚያርቅ እና በአምላክ አምሳል ለተፈጥሩ የሰው ልጆች ሰብአዊ ክብር ዋስትና የሚሰጥ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ የበኩሏን አስተዋጻኦ ታበረክታልች።

በመላ አገሪቷ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን ምዕመናንም ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት አጥብቀው እንዲጸልዩ እና የሚጠበቅባቸውንም በጎ ምላሽ እንዲሰጡ ታሳስባለች። "

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia