TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የጀግኖቻችን መስዋዕትነት ይበልጥ #ያጠነክረናል እንጂ አያንበረክከንም!!"

/የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የጸጥታ እና የሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል/

ምንጭ፦ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ለ2019 የቻታም ሃውስ ሸልማት መታጨታቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡ ዐቢይ ለሽልማቱ የታጩት በሀገራቸው የንግግር ነጻነት በማስፈናቸው፣ ሲቪክ አመራር በመስጠታቸው፣ የመድበለ ፖለቲካንና ጾታ እኩልነትን በማጠናከራቸው እና ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሰላምና ትብብር ጉልህ አስተዋጽዖ በማድረጋቸው ነው፡፡ ቻታም ተቀማጭነቱን ታዋቂ ዐለም ዐቀፍ የፖሊሲ ተቋም ነው፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፍሪካ ኅብረት የኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል የህክምና ቡድን ወደ ስፍራው ሊልክ መሆኑን በኅብረቱ የበሽታ መከላከል ማዕከል አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአለታ ወንዶ፣ ሀገረ ሰላም፣ ይርጋለም ከተሞች ዛሬም #ሁከት#ዘረፋ እና የንብረት #ውድመት መታየቱንና በርካቶችም መታሰራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ሀዋሳ ዛሬ ተረጋግታ ውላለች።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሐዋሳ ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰው ሁከት፦

ትናንት ሐዋሳ ውስጥ ከተቀሰቀሰው ግርግር ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት አብቅቶ ዛሬ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን BBC ያነጋገራሸው የከተማዋ ነዋሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ።

የቢቢሲን ዘገባ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HM11-07-19
#SLM ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ባለው አለመረጋጋት 17 ሰዎች መገደላቸውን አውቃለሁ ሲል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታውቋል። በመንግስት በኩል እስካሁን ስለሟቾች ቁጥር ምንም ይፋ የተደረገ መረጃ የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቐለ ከተማ ምክር ቤት አራተኛ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለ2012 በጀት ዓመት የሚውል ከ2 ቢሊዮን 766 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይርጋለም

በይርጋለም ከተማ የክልሉ ገዢ ፓርቲ/ደኢህዴን/ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ባጢሶ ባቲሶ በከተማው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አረጋግጠዋል። በዚህም አራዳ በሚባል አካባቢ የሰባት ግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች፣ በሌላ ስፍራ ደግሞ ሦስት ቤቶች #መቃጠላቸውን፣ የዱቄት ፋብሪካ መቃጠሉን፣ የከንቲባውና የድርጅት ጽህፈት ቤቱ መኪኖች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት መኪና፣ የአረጋሽ ሎጅ ሦስት መኪኖች መቃጠላቸውን ተናግረዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የሲዳማ ዞን ከተሞች የዛሬ ሃምሌ 12/2011 ዓ/ም ውሎ!
ከላይ ያለውን የድምፅ ፋይል ይክፈቱት🔝

የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ዘገባ~የሲዳማ ዞን ከተሞች!

የሲዳማን ክልል እንሁን ጥያቄ ተከትሎ በዞኑ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሁከት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ በሁከቱ እስከ አሁን የዘጠኝ ሰው ህይወት አልፋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፤ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል፡፡ የሁከቱ ሰለባ የሆኑ እንደሚናገሩት በአንዳንድ በሲዳማ ዞን ከተሞች ተቃውሞው ዛሬ መልኩን ቀይሮ ማንነትን በመለየት፣ የመኖሪያ ቤትና ንብረት ላይ ጥቃት ደርሷል፡፡ መንግሥት ተጨማሪ ኃይል በማስገባት ሰላማችንና ደኅንነታችንን ያረጋግጥ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፣ ዛሬ ሀዋሳ #የተረጋጋች መሆኑ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ሲአን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከአስር በላይ ሰዎች በመልጋ ወረዳና አካቢው ሞተዋል ብለዋል፡፡ በግጭቱ ማዘናቸውን የገለፁት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ህዝቡ #እንዲረጋጋ ጠይቀዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ችግሩን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፀጥታ ኃይል እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ያሳዝናል

ከትናንት ጀምሮ በሲዳማ ዞን በተፈጠረው #ግጭት በተለይ በሞርቾ እና በሃገረ ሰላም ከተሞች #ከሞቱት መካከል አብዛኛዎቹ #ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውን የጀርመን ራድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#congratulations የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ በተለያዩ ዘርፎች ያስተማራቸውንና ያሰለጠናቸውን 9750 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት 7425 ተማሪዎችን ያስመርቃል። ከተመራቂዎቹ ውስጥ 5146ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 2279 በማስተርስ እና ፒ ኤች ዲ የሚመረቁ ናቸው።

ከፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት የትዊተር ገፅ የወሰድኩት👇

"Tomorrow 7425 will graduate. 5146 in first degree & 2279 in masters & PhD! Come & join us at Adihaki Campus! Familes of graduates r invited for lunch in all the cafeterias of the campuses so that they feel the campus life experience of the graduates! Congratulations!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቹ! ቻይንኛ እና ቻይንኛ ብቻ የሚማሩበት የቋንቋ ት/ት ቤት! የአዋቂዎች እና የልጆች ከደረጃ 1-4 ት/ት ሐምሌ 1,2,8 እና 15 ላይ ይጀምራሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0947202020
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የመጋዘን አስተዳደር ስልጠና፦

•የስልጠና ጊዜ : ከሃምሌ 29-ነሃሴ 10/2011
•የስልጠና ሰኣት : የጥዋት ፈረቃ ከ2:30-6:30
: የከሰዓት ፈረቃ ከ7:30-11:30

የስልጠና ቦታ፡ ካዛንችስ ንግስት ታወርስ ሆቴል እና አፓርትመንት 4ኛ ፎቅ

ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ :
0115589045
0903182525
በሀዋሳ ከተማ እና ዙሪያዋ ውሃ #ተመርዟል ስለሚባለው ጉዳይ አንድ የመንግስት የስራ ሃላፊን በስልክ ጠይቄ ያገኘሁት ይህን መልስ ነው፦

"ሲጀምር ይህን ለማድረግም እድሉ አይገኝም! የሚናፈሰው ወሬ ህዝቡን #ለማሸበር ነው። ወሬው ሀሰት ነው!"

ተጨማሪ መረጃ ከደቂቃዎች በኃላ ይዤ እመለሳለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመጠጥ ውሃ ተመርዟል የተባለው ውሸት ነው!

በሀዋሳ ከተማ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየተናፈሰ ስለሚገኘው "የውሃ መመረዝ" ጉዳይ የሀዋሳ ከተማን የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ምክትል ስራ አስኪያጅ ክቡር አቶ ደምሴን በስልክ አነጋግሬያቸው ያገኘሁት ምላሽ ይህ ነው፦

"ምንም የተፈጠረ ነገር የለም! የከተማውን ህዝብ ለማሸበር የተደረገ ነገር ነው። ውሃው ለንደሱ አይነት ነገር/ለመመረዝ/ እድል የለውም። 24 ሙሉ በቂ ጥበቃ አለ። በውሃው #መስመር ላይም ለመመረዝ የሚሆን ምንም እድል የለም። እየተወራ የሚገኘው ሀዋሳ ብቻ አይደለም አለታ ወንዶ፣ ይርጋለም፣ ወንዶ ገነት፣ ...ምንም ነገር አልተፈጠረም የፈጠራ ወሬ ነው። ህዝቡም እንዲያውቀው በመገናኛ ብዙሃን ይገለፃል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኦዳ_ቡልቱም

"ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለመጀመርያ ጊዜ 558 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል የተለያዩ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል ከፌደራል የ ባህልና ቱሪዚም ሚኒስቴሩዋ ዶ/ር ሂሩት ካሳ ይገኙበታል።" F ከቦታው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 9 ሺህ 750 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው 9 ሺህ 750 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሀ ገብሮች እያስመረቀ ነው፡፡

በፕሬዝዳንቱ እንደተገለጸው ከተመራቂዎች መካከል 6 ሺህ 520 ያህሉ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 3 ሺህ 167 በሁለተኛ ዲግሪና 63 በሦስተኛ ዲግሪ የሚመረቁ ናቸው፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምሥራቅ አፍሪካ #ብቸኛ በሆነበት በማሪታይም አካዳሚ ጭምር በርካቶችን እያስመረቀ መሆኑን የገለጹት ዶክተር #ፍሬው_ተገኝ በትምህርት ጥራት ተወዳዳሪነቱ በየጊዜው እያደገ መምጣቱን አብራርተዋል። በሕግ ትምህርት ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1ኛ እና 3ኛ ደረጃ የያዙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሆናቸውንም በአብነት አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለሕይወት ዘመን የሚበጁ ዕውቀቶችን እንዳስታጠቃቸው በመግለጽ በምክንያታዊነት የሚያምኑ ሀገር የሚገነቡ ዜጎች እንዲሆኑም ተመራቂዎቹን አሳስበዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ336 ፕሮግራሞች እያስተማረ እንደሚገኝ ያመለከቱት ፕሬዝዳንቱ ተመራቂዎችን የሕይወት ዘመን ተማሪዎች እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የድህረ ዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በልዩ ልዩ የሙያ መስክ ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
#Congratulations የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 7425 ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ ውስጥ 5146ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 2279ኙ በማስተርስ እና ፒ ኤች ዲ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia