#Alert
በይርጋም ከተማ በተለይም "ገበያ አካባቢ" አለመረጋጋት እንዳለ እየተጠቆመ ይገኛል። የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግም ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 30 ይካሄዳል ተባለ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ፣ ለተማሪዎች ዩኒፎርም ለማቅረብ እና ይሰጥ የነበረውን የምገባ መርሃ-ግብር ቁጥር ከፍ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በመሆኑም ዩኒፎርምን ጨምሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እና የምገባ ፕሮግራም የሚደረግላቸው ተማሪዎችን ትክክለኛ ቁጥር እና መረጃ ለመሰብሠብ የምዝገባ መርሃ-ግብሩ ቀደም ብሎ ለማድረግ እንደታሰበ ነው የተሰማው፡፡
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከትምህርት ሴክተር ከመጡ አመራሮች እና ባለሞያዎች ጋር በክረምት ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህም በመንግስት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ምዘገባ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከተጠቀሰው ቀን በኃላ የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን እንደማያስተናግድ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

#ሃዋሳ
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑ ተሰምቷል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ግን አሁንም እንደ ቆሙ ነው። ነዋሪዎች ግን በከተማይቱ ይንቀሳቀሳሉ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማይቱን ሲዘዋወሩ እንደተመለከቱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በስልክ ገልፀዋል።

#ይርጋለም #ሞረቾ #አገረሰላም~የፀጥታ ሁኔታ!
ትናንት ግጭት እና ተቃውሞ በታየባት ሐዋሳ ከተማ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እንደሚታይ የጀርመን ራድዮ ገለፀ። የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ እንደገለፀዉ ከሐዋሳ ውጪ በሞሮቾ፣ ይርጋለም እና አገረሰላም በተባሉት ከተሞች #አሁንም ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እንዳሉ የዓይን እማኞች ሰቅሶ ዘግቧል። በሞሮቾ የሚገኝ አንድ የዓይን እማኝ እንዳለው ወጣቶች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በነበራቸው ግጭት «የሚያውቃቸው ወጣቶች #ሞተዋል። መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮች #ተዘግተዋል። ከሐዋሳ በዲላ በኩል ወደ ሞያሌ እና ኬንያ የሚወስደውም መንገድ ተዘግቷል።» አገረሠላም የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደገለፁት ደግሞ «ትናንትና ሰዎች ሞተዋል። ወጣቶች ቤት #አቃጥለዋል።» በከተማዋ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን ዛሬ ላይ መጠነኛ መረጋጋት ይታያል። «ሆኖም ከተማዋ ውስጥ ዛሬም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል።» የሲዳማ ዞን ፖሊስ በሐዋሳ አጎራባች አካባቢዎች አሁንም አለመረጋጋት መኖሩን ለ ጀርመን ራድዮ አረጋግጧል። በሲዳማ በተለያዩ አካባቢዎች የታዩትን አለመረጋጋቶች ተከትሎ ደረሰ ስለተባለዉ ጉዳት ግን ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
Via #DW

#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራን የሁት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ፡፡ የኤርትራን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡ የሁለቱ መመሪዎች ውይይትም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኑነቶችና ትብሮች በሚያጠናክሩ እና በቀጠናው ልማት ዙሪያ ያተኮሩ እንደነበረም ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ኢትዮጵያ ከማቅናታቸው በፊት በአስመራ ከተማ የችግኝ ተካላ ማካነዎናቸውም ነው የተገለጸው፡፡
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አሁንም እያጣራን ማሰሩም፤ መፍታቱም ይቀጥላል" ኮሚሽነር አበረ
ሰኔ 15 በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው 'መፈንቅለ መንግሥት' ጋር በተያያዘ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አስታውቋል።
ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል የክልሉ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች የነበሩትን ብርጋዲየር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ኮሎኔል ባምላኩ፣ ኮሎኔል አለባቸውና እና ሻለቃ እሸቱ ይገኙበታል።
ሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም አንስቶ በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎቹ ከሦስት ቀናት ፊት ጀምሮ 'ፍትህ እንሻለን' በማለት የርሃብ አድማ ላይ መቆታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Sene15-07-19

ተ.መ.ድ #የጥላቻ_ንግግር እንዲቆም ጥሪ አቀረበ!
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን ጥሪ ያቀረበው የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀን በተከበረበት ግዜ ነው፡፡ በዓሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ማሪያ ፈርናንዳ ኢስፒኖሳ ጋሬስ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግርን መታገል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የደርባን የድርጊት መረሃ ግብር በመተግበር እና በቅርቡ በተ.መድ በጥላች ንግግር ላይ ያወጣውን ስትራተጂ በመጠቀም “ ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ መስራት ይኖርብናል” ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ደርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የጥላቻ ንግግር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት የማዲባን የማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር እና የሰላም ባሕልን ማዳበር ጥሪ መተግበር ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡
ኔልሰን ማንዴላን ስናስታውስ በጋር ለሰላም እና መረጋጋት፣ዘላቂ ልማትና ሰብአዊ መብትን በማረጋገጥ ነው ብለዋል አንቶኒዮ ጉተሬዝ፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1918 የተወለዱት ኔልሰን ማንዴላን ለመዘከር በየዓመቱ ጁላይ 18 የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡
Via ዥንዋ/ENA

ጥንቃቄ!
በአዲስ አበባ ከተማ ከጣለው ዝናብ ጋር ተያዞ የዘነበ ወርቅ መንገድ በውሃ ተጥለቅልቋል በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ስለተፈጠረ ወደአካባቢው የምትሄዱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንላለን።
Via #TOM

#update በአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ ከሸፈ ከተባለው «የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ» ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች አያያዝ መሻሻል ማሳየቱን ጠበቃቸው ሄኖክ አክሊሉ ለ ጀርመን ራድዮ ተናገሩ። ጠበቃ ሄኖክ እንደገለፁት ታሳሪዎቹ በቤተሰብና በጓደኞቻቸው እየተጠየቁ ነው፣ የታሰሩበት ቤት #መብራት ገብቶለት ከጭለማ ብርኃን ወደ ማግኘት ተሻግረዋል። የሚነበቡ መጽሕፍት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦች እየገቡላቸውም ነው ብለዋል። ይህም ቢሆን ግን ጠበቃቸውም ይሁን ቤተሰቦቻቸው ሲጠይቋቸው ፖሊሶች መሃል ላይ በመሆን ይህን አታውሩ፣ እንዲህ አትበሉ በማለት ከታራሚዎች አያያዝ አሰራር በተጻረረ ረገድ የሚያደርጉት ቁጥጥሮች ተገቢ ያልሆነና መስተካከል ያለበት ነው ሲሉ ጠበቃው ሄኖክ አክለዋል። በሌላ በኩል እስረኞች እስካሁን ከታሰሩ ጀምሮ 1 ጊዜ ብቻ ገላቸውን እንደታጠቡና፤ የታሰሩበት ቦታ የራሱ የሆነ የመታጠቢያ ስፍራ ባለመኖሩ የደንበኞቼን ምቾት የነሳ ነው ብለዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2021 በካሜሮን ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች፡፡ በምድብ 11 የተደለደለችው ኢትዮጵያ ከኮትዲቯር፣ ኒጄር እና ማዳጋስካር ጋር ትጫወታለች።
በካሜሮን ለሚካሄደው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 12 ምድቦች የሚገኙ ሲሆን፥ የየምድቦቹ 1ኛ እና 2ኛ ቡድኖች በካሜሮን አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።
ምድብ 1 – ማሊ፣ ጊኒ፣ ናሚቢያ፣ ላይቤሪያ
ምድብ 2 – ቡርኪና ፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ማላዊ፣ ደቡብ ሱዳን/ሲሸልስ
ምድብ 3 – ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ሞሪሸስ/ሳኦቶሜ
ምድብ 4 – ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ጅቡቲ/ጋምቢያ
ምድብ 5 – ሞሮኮ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ቡሩንዲ፣ ሞሪታንያ
ምድብ 6 – ካሜሩን፣ ሞዛምቢክ፣ ሩዋንዳ፣ ኬፕ ቨርዲ
ምድብ 7 – ግብፅ፣ ኬንያ፣ ቶጎ፣ ኮሞሮስ
ምድብ 8 – አልጄሪያ፣ ዚምባብዌ፣ ቦትስዋና፣ ዛምቢያ
ምድብ 9 – ሴኔጋል፣ ኮንጎ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኢስዋቲኒ
ምድብ 10 – ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ታንዛኒያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ
ምድብ 11 – አይቮሪኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ኒጀር፣ ማዳጋስካር
ምድብ 12 – ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ቤኒን፣ ሌሶቶ
Via ኤፍ ቢ ሲ

#update በትላንትናው ዕለት ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ከተማ በተፈጠረ #ግጭት በትንሹ 3 ሰዎች #መሞታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
.
.
(#Reuters) - At least three people have died in Ethiopia's southern city of Hawassa, hospital authorities said on Friday, amid a showdown between state security forces and some local activists who want to declare a new region for their Sidama ethnic group.
የሮይተርስን ዘገባ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HAWSSA-07-19

#update በሐዋሳ ከተማ በጥይት ተመተው የተገደሉት ሰዎች አራት መድረሳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዛሬ ገለፀ። ሟቾቹም ሦስት ወንድ እና አንድ ሴት እንደሆኑ የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዝናው ሰርኒሶን ጠቅሶ ዜና ምንጩ ዘግቦአል። ከሟቾቹ መካከል አንዱ ጭንቅላቱ ላይ የተመታ ሲሆን ሌሎቹ ሆዳቸው ላይ በጥይት ተመተው እንደነበር ተገልጿል። አራቱም ትናንት ሆስፒታል ገብተው ህክምና የተደረገላቸው ቢሆንም ሦስቱ ሆስፒታል በገቡበት እለት ትናንት ህይወታቸው አልፏል። የሴቷ ህይወት ደግሞ ዛሬ ማለፉ ተገልፆአል።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በሱማሌ ክልል በህገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች እጅ የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ የግልና የቡድን የጦር መሳሪያዎች በአሰሳ መያዙን የክልሉ ልዩ ፖሊስ ገለፀ። የሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ኮማንደር ዘካሪያ አብዲ እንደገለፁት በህገ ወጥ መንገድ ተሰራጭተው በግለሰቦች እጅ በብዛት የነበሩት የቡድንና የግል የጦር መሳሪያዎች ለግጭትና ለበርካታ ሰዎች ህልፈት ምክንያት ሆነው ቆይተዋል። የክልሉ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ ተሰራጭቶ በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ እንዲሰበሰብ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ላለፉት ሦስት ወራት ተከታታይ አሰሳ ሲያደረግ ቆይቶ 3 ሺህ 40 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን መያዙን ኮማንደሩ ተናግረዋል። ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች መካከል በግለሰብ ደረጃ መያዝ የማይገባቸው መካከለኛ የጦር መሳሪያዎች፣ አውቶማቲክ ቀላል ጠብመንጃዎች፣ ሽጉጦችና ቦምቦች ይገኙበታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቶጎ ውጫሌ የልዩ ፖሊስ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መያዙንም ኮማንደሩ አክለው ገልፀዋል።
ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ላልይበላ
ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከ45 ሽህ በላይ የውጭ ሃገር ዜጎች ላልይበላን መጎብኘታቸውን የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የቅዱስ ላልይበላንና በዙሪው ያሉ ድንቅ ቅርሶችን 45,144 ጎብኝዎች መጎብኘታቸውን ከጽፈት ቤቱ የተገኘው መረጋጃ ያመለክታል፡፡ ጽ/ቤቱ እንዳመለከተው በየዓመቱ የጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀ ሲሆን የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜም ለማራዘም እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ለዚህም ደግሞ የሆቴሎችን አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሳደግ በተሰራው ስራ 5 ሆቴሎች በኮኮብ ደረጃ እንዲመደቡ የጎደላቸውን በሱፐርቪዥን ቡድን በተሰጠው ግበረ መልስ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም አስታውቋል፡፡
በተያያዘ መረጃ...
ባሳለፍነው 2011 በጀት ዓመት የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲናትና በዙሪው የሚገኑ ታሪካዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብለው በእቅድ ከተያዘው 48,3167 የሃገር ውስጥ ጎብኝዎች ውስጥ 211,909 የሃገር ውስጥ ጎብኝዎች መጎብኘታቸውን ከላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ መረጃው እንደሚመለክተው በየአመቱ የጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል፡፡ በበዓላትና በሌሎችም ቀናት ቅርሶችን የሚጎበኙ ዜጎችም መጨመራቸው ነው ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
Via Lalibela Government Communication Affairs Office

#NewsAlert በሰሜናዊ ግብፅ #ሲና አካባቢ በአንድ አጥፍቶ ጠፊ በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይዎት አለፈ። ጥቃቱ የደረሰው በአንድ የአገሪቱ የመከላከያ አባልና በሌላ አንድ ሲቪል ላይ መሆኑን ከአገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤትና ከሆስፒታሎች መረጃ አግኝቻለሁ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል። የአጥፍቶ ጠፊው ዋና ኢላማ በርካታ ወታደሮች የሚገኙበት የሲና ወታደራዊ ኬላ የነበር ቢሆንም ኢላማ አድርጎት ከነበረው ቦታ ሳይደርስ ታጥቆት የነበረው ቦንብ ሊፈነዳ መቻሉን የገለፁት የግብፅ መከላከያ ቃል አቀባይ ናቸው። በኢራቅ ራሱን እስላማዊ መንግስት እያለ የሚጠራው አሽባሪ ቡድን አማቅ በተባለ ድህረ ገፁ ላይ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጿል። ካለፈው ጥር ጀምሮ ግብፅ አሸባሪ ቡድኑ ይገኝበታል ተብሎ በሚጠረጠሩ ቦታዎች ላይ በርካታ ወታደሮችን አሰማርታ ጥቃት ጀምራ እንደነበር ይታወሳል።
Via አልጀዚራ/ENA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via አልጀዚራ/ENA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
የግብረ ሰዶም ጥቃት ያደረሰዉ ታዳጊ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ!
.
.
ተከሳሽ የ16 ዓመቴ ታዳጊ ወጣት #ናሆም_መሀሪ የተመሳሳይ ጸታ ግንኙነት ወንጀል በመፈጸሙ በዓቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 631/1/ለ/ ሥር የተደነገገዉን በመተላለፍ ተከሳሽ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ጾታ ካለዉ ወንድ ልጅ ጋር የግብረሰዶም ጥቃት ለመፈጸም በማሰብ ጥር 16 ቀን 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ካራ ስጋ መሸጫ አካባቢ በ8ዓመቱ ህፃን ላይ የፈጸመዉን የግብረሰዶም ጥቃት በማስረጃ በማረጋገጡ ነዉ ዓቃቤ ህግ ክሱን የመሰረተዉ፡፡
ተከሳሽ ህጻኑን አባብሎና አታሎ ድርጊቱን ፈጽሞል በግል ተበዳይ ላይም የአካል እና የስነልቦና ጉዳት እንዲደርስበት ምክንያት ሆኗል ሲል ዓቃቤ ህግ በክሱ አስረድቷል፡፡የግል ተበዳይም በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የህክምና ምርመራ ተደርጎለት ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈጸመበት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየዉ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ችሎትም የወንጀሉን መፈጸም በሰዉና ከጋንዲ ሆስፒታል በተገኘ የህክምና ማስረጃ አረጋግጦ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት ተከሳሹ #ጥፋተኛ የተባለበት የህግ ድንጋጌ ደረጃና እርከን ስላልወጣለት መነሻዉ ከ16 ዓመት ጀምሮ የሚያስቀጣ ቢሆንም የጥፋተኛዉን እድሜ ከግምት በማስገባት ሰኔ 25 ቀን 2011ዓ.ም በዋለዉ 5ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሹ በ13 ኣመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

#መከላከያ_ሰራዊት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገ-ወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታወቀ፡፡ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደዋል፡፡ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ አተኩሮ የተካሄደውን ውይይት ያስጀመሩት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሀመድ ናቸው፡፡ ከፍተኛ አመራሮቹ በቅርቡ በተቋሙና በአማራ ክልል አመራሮች ላይ የደረሰው አደጋ ታላቅ ቁጭት መፍጠሩን በመግለጽ በቀጣይ ድርጊቱ እንዳይደገም እንደሚሰሩ በውይይቱ ማጠቃለያ ባወጡት ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱና ለህዝቦች ሰላም መስዕዋትነት እየከፈለ የመጣ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው በቀጣይም የተለያዮ #ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገ-ወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፡ ሰራዊቱ ከምንጊዜም በላይ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት በሚያስችለው ቁመና ላይ እንደሚገኝና የተሰውት ጓዶች ህልፈት አባላቱን ለበለጠ #ጀግንነትና መስዋዕትነት የሚያነሳሳ እንጂ #የሚያዳክም እንዳልሆነ ገልጿል፡፡
ምንጭ፦ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት

#ሀዋሳ #SMN
በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስብሰባ ተቀምጠው በነበረበት ሰዓት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው የኔትወርኩ የዜናና ፕሮግራሞች አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ብርሀኑ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌታሁን ደጉዬ እና ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ የሚባሉ ሲሆን ሌሎች የመገናኛ ብዙሀኑ ባልደረቦች ግን ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገልፀዋል።
ትናንት ጠዋት ወደ 6 ሰዓት አካባቢ ወደ ቢሯቸው የፀጥታ አካላት መምጣታቸውን እና ጥበቃ ሰራተኞቹ የቢሮውን ቁልፍ እንዲሰጧቸው መጠየቃቸውን ያስታወሱት አስተባባሪው፤ ነገር ግን የጥበቃ ሰራተኞቹ ቁልፍ እንደሌላቸው በመግለፅ እንዳሰናበቷቸው ተናግረዋል።
ማታ ወደ 4 ሰዓት የሲዳማ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ሽማግሌዎችና፣ ኤጀቶዎች በታቦር መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምርጫ ቦርድን ሃሳብ ለመቀበል በንግግር ላይ ባሉበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ተናግረዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ከወጣቶቹ ጋር የተሰበሰቡት #ኤጀቶ ውስጥ በነበሯቸው ተሳትፎ ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ሥራ የጀመረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ሲሆን እስካሁን የሚገኘው የሙከራ ስርጭት ላይ ነው።
የሚዲያ ተቋሙ ፕሮግራሞቹን የሚያስተላልፈው ሐዋሳ ከሚገኘው ቢሮውና ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ውስጥ ከሚገኘው ማሰራጫው እንደሆነ አስተባባሪው ተናግረዋል።
በአሁን ሰዓትም ምንም ዓይነት ስርጭት #ከሐዋሳ የማይተላለፍ ሲሆን ነገር ግን ከጆሀንስበርግ የሚተላለፉ ዝግጅቶች ብቻ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ እንደሚታዩ ተናግረዋል።
Via #BBC

#update ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሙስና ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ በአምስት ዓመት ከአራት ወራት ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቀጣ፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጌታ ፈንታው ለኢዜአ እንዳስታወቁት ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ያስተላለፈው የወምበራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ደሞዝ ከፋይ በነበረው አቶ አየሩ ቀናው በተባለ ግለሰብ ላይ ነው፡፡ ግለሰቡ በጽህፈት ቤቱ በሚሰራበት ወቅት ከ80 ሺህ በላይ ብር በከባድ እምነት መጉደል የሙስና ወንጀል መከሰሱን ተናግረዋል፡፡ ግለሰቡ ወንጀሉን መፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት በእስራትና አምስት ሺህ ብር ቅጣት እንደወሰነበት ገልጸዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia