TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert የደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በፅ/ቤታቸው እንዲሁም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ እና የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ በተከታታይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።

Via #SMN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ #SMN

በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስብሰባ ተቀምጠው በነበረበት ሰዓት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው የኔትወርኩ የዜናና ፕሮግራሞች አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ብርሀኑ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌታሁን ደጉዬ እና ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ የሚባሉ ሲሆን ሌሎች የመገናኛ ብዙሀኑ ባልደረቦች ግን ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገልፀዋል።

ትናንት ጠዋት ወደ 6 ሰዓት አካባቢ ወደ ቢሯቸው የፀጥታ አካላት መምጣታቸውን እና ጥበቃ ሰራተኞቹ የቢሮውን ቁልፍ እንዲሰጧቸው መጠየቃቸውን ያስታወሱት አስተባባሪው፤ ነገር ግን የጥበቃ ሰራተኞቹ ቁልፍ እንደሌላቸው በመግለፅ እንዳሰናበቷቸው ተናግረዋል።

ማታ ወደ 4 ሰዓት የሲዳማ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ሽማግሌዎችና፣ ኤጀቶዎች በታቦር መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምርጫ ቦርድን ሃሳብ ለመቀበል በንግግር ላይ ባሉበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ተናግረዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ከወጣቶቹ ጋር የተሰበሰቡት #ኤጀቶ ውስጥ በነበሯቸው ተሳትፎ ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ሥራ የጀመረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ሲሆን እስካሁን የሚገኘው የሙከራ ስርጭት ላይ ነው።

የሚዲያ ተቋሙ ፕሮግራሞቹን የሚያስተላልፈው ሐዋሳ ከሚገኘው ቢሮውና ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ውስጥ ከሚገኘው ማሰራጫው እንደሆነ አስተባባሪው ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓትም ምንም ዓይነት ስርጭት #ከሐዋሳ የማይተላለፍ ሲሆን ነገር ግን ከጆሀንስበርግ የሚተላለፉ ዝግጅቶች ብቻ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ እንደሚታዩ ተናግረዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SMN የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች በሀዋሳ ከተማ ከተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። አመራሮቹ ስላሉበት ሁኔታ ከቤተሰቦቻቸው መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርጊያለሁ። ከታሳሪ ቤተሰቦች አንድ ሰው በስልክ አነጋግሬ ያገኘሁትን መረጃ ወደበኃላ ወደናተ የማደርስ ይሆነል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SMN

ከቀናት በፊት ከሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ የተቋሙ የቦርድ አባላት መታሰራቸው ይታወቃል። ለመሆኑ ታሳሪዎቹ በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?? ብዬ ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች መካከል አንድ ሰው አናግሪያለሁ...የታሰሩት በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንደሆነ የገለፁልኝ እኚህ ሰው ተከታዩን ብለዋል፦

"አሁንም ቢሆን #እየተሳቀቅን ነው ሄደን የምንጠይቃቸው፤ በር ላይ ያሉት የፀጥታ ኃይሎች ያሸማቅቁናል፣ ይሰድቡናል። በር ላይ ያሉት ሰዎች ለቤተሰቦች ተገቢውን ክብር እየሰጡ አይደለም፤ በስንት ልመና ነው ምግብ እንኳን የምናስገባላቸው። ከትላንት በስቲያ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስና የክልሉ ፖሊስ አነጋግረዋቸው ነበር ምርመራ እያደረግን ነው በ14 ቀን ውስጥ ዝርዝር ጉዳዩን እና በምን ምክንያት እንደታሰሩ እናሳውቃችኃለን ብለዋቸው የነበረ ሲሆን ቀኑ መብዛቱን ቅሬታ ያሰሙት የSMN አመራሮቹ ከ14 ቀን በፊት ዝርዝሩ እንዲነገራቸው ጠይቀው ተፈቅዶላቸዋል። ለምን እንደታሰሩ ምን እየተፈፀመ እንዳለ አያውቁም፤ ፖሊስም ካሰራቸው በኃላ ነው መረጃ እያፈላለገ የሚገኘው ይህ ፍፁም ተገቢ አይደለም። ምን አይነት ስራ እየተሰራ እንዳለ አናውቅም፤ ቤተሰብ ብዙ ጊዜ እንዲያገኛቸው አይፈቀድም ነገር ግን ባገኘናቸው ሰዓት የሚነግሩን አያያዛቸው ጥሩ እንዳልሆነ ነው።"

🏷በታሳሪዎቹ ላይ ድብደባ እና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው የሚል ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ አይቼ ነበር ምን ያህል እውነት ነው ብዬ ለጠየኳቸው ጥያቄ የሰጡኝ ምላሽ፦ "እኔ ይህን እርግጠኛ #አይደለሁም፤ እርግጠኛ የምሆንበትን ነገር ብቻ ደውዬ አሳውቅሃለሁ"

@tikvahethiopia @tsegabwolde
#SMN የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ አመራሮች ታሪኩ ለማና ጌታሁን ደጉዬን ጨምሮ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ በሐዋሳ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። በሲዳማ ዞን 935 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳኛቸው ደምሴ ተናግረዋል።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ #ጥራቱ_በየነ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል። #SMN #HAWASSA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ አተት መከሰቱ ተሰማ!

በሀዋሳ ከተማ አጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ/አተት መከሰቱን የሃዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ አስታወቀ። በሽታው የታየው በጥልቴ ቀበሌ ሲሆን በበሽታዉ የተጠቁ 2 ግለሰቦች የህክምና አግልግሎት እያገኙ መሆኑን የገለፁት የሐዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ #ቡሪሶ_ቡላሾ በሽታውን ወደ ሌሎች የከተማው ክፍሎች ሳይዛመት ከወዲሁ ለመግታት ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል። በሽታው ቶሎ ካልተገታ ከከተማው አልፎ ወደ ሲዳማ ዞን ሊዛመት እንደሚችል የጠቆሙት ሀላፊው ይህ እንዳይሆን ለማድረግ ከዘርፉ ባለሙያወች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በወንዶ ገነት ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

Via #SMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA ከሲዳማ ከስልጤ እና ጉራጌ ዞን የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ በሀዋሳ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። የጋራ መድረኩ አላማ የህዝቦቹን ለዘመናት አብሮ የኖረ በደም ተሳሰረ አንድነት ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏል። በመድረኩ ላይ የሶስቱም ዞን የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው ነበር።

Via #SMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫ፦

- ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ግለሰቦች መካከል በሜቴክ ውስጥ ከተፈፀመ ሙስናና ከሰኔ 15ቱ ክስተት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ይገኙበታል።

- በሲዳማ ዞን ተከስቶ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ግለሰቦች ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል።

- ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረጉ ግለሰቦች መካከል በሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በተለይም በሜቴክ ውስጥ ከተፈፀመ እና ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዞ ሆኖም የአመራርነት ሚና ያልነበራቸው ግለሰቦች ክሳቸው ተቋርጧል።

#FBC #SMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia